ሲዳማ በሚቀጥሉት አሥር ቀናት መደበኛና ከመደበኛ በላይ ዝናብ ያገኛል ተባለ
በሚቀጥሉት አሥር ቀናት ለዝናብ መፈጠር ምቹ ሁኔታ መኖሩን ተከትሎ በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች ወቅቱን ያልጠበቀ ዝናብ ሊከሰት እንደሚችል ተገለጸ። ብሔራዊ የሚቲዎሮሎጂ ኤጀንሲ በኅዳር ወር ሊኖር የሚችለውን አገራዊ የአየር ሁኔታ አዝማሚያ ትንበያን ዛሬ ይፋ አድርጓል። በኤጀንሲው ትንበያ መሰረት በአብዛኛው የአገሪቱ ክፍል የበጋ ደረቅና ነፋሻማ የአየር ሁኔታ እንደሚያመዝን ይጠበቃል። በሌላ በኩል በግብርና እንቅስቃሴ ላይ የሰብል ጥፋትና የምርት ብክነት ሊያስከትል ስለሚችል የደረሱ ሰብሎችን በአፋጣኝ መሰብሰብ፤ የተሰበሰቡትም ዝናብ በማያስገባ ሁኔታ መከመር እንደሚገባ ኤጀንሲው አሳስቧል። በሌላ በኩል የወቅቱ ዝናብ በደቡብ ምዕራብ፣ በምዕራብ፣ በደቡብና በደቡብ ምሥራቅ የአገሪቱ ክፍል ቀጣይነት እንደሚኖረው ነው የተመለከተው። አልፎ አልፎ ባሉት ቀናትም ወቅታዊ ያልሆነ ዝናብ በአንዳንድ የሰሜን፣ የመካካለኛውና የምሥራቅ የአገሪቱ ክፍሎች ይከሰታል ተብሎ እንደሚጠበቅ ትንበያው ጠቁሟል። በአብዛኛው የትግራይ ዞኖች፣ ከአማራ ክልል አዊ ዞን፣ የባህር ዳር ዙሪያ፣ ምዕራብና ምሥራቅ ጎጃም፣ ሰሜንና ደቡብ ጎንደር፣ ዋግ ኽምራ፣ የሰሜን ደቡብ ወሎ አካባቢዎች መደበኛና ከመደበኛ በላይ ዝናብ እንደሚኖራቸው ይጠበቃል። በተመሳሳይም ከኦሮሚያ ሆሮ ጉድሩ፣ ምዕራብ ሸዋ፣ አርሲ፣ ባሌ፣ ቦረና እና ጉጂ መደበኛና ከመደበኛ በላይ ዝናብ እንደሚኖራቸው በትንበያው ተመልክቷል። በሌላ በኩል ደረቅ የአየር ሁኔታ እያመዘነ ቢሆንም በምዕራብና ምሥራቅ ሐረርጌ፣ ሀረሪ፣ ድሬደዋና በአዲስ አበባ ከመደበኛ በላይ ዝናብ እንደሚያገኙ ተገልጿል። በተጨማሪም የቤኒሻንጉል ጉምዝና የጋምቤላ ሁሉም ዞኖች በአብዛኛው ከመደበኛ ጋር በተቀራረበ የዝናብ መጠን እንደሚያገኙ ይጠበቃል። በአንፃሩ የአፋር 3 እና 5 ዞኖች በጥቂት