ነዳጅ ቀነሰ… ትራንስፖርትስ?
በዓለም አቀፍ ደረጃ የነዳጅ ዋጋ እየቀነሰ ነው፡፡ ካለፉት ሦስት ወራት ወዲህ የታየው የዋጋ ቅናሽ ያልተጠበቀ ነው ተብሏል፡፡ በአሜሪካ መሪነት ኢስላሚክ ስቴት (አይኤስ) ከተባለው ጽንፈኛ ቡድን ጋር እየተደረገ ያለው ፍልሚያ፣ የነዳጅ ዋጋን ያንራል ተብሎ ቢጠበቅም እውነታው ግን የተገላቢጦች ሆኗል፡፡ ከአይኤስ ጋር የሚደረገው ፍልሚያ የዓለም የነዳጅ ዋጋን ያንራል በማለት ከተለያዩ አቅጣጫዎች የተነሰነዘሩ ትንታኔዎች በግምት ቀርተዋል፡፡ አንቱ የተባሉ የኢኮኖሚ ባለሙያዎችና ተቋማት የነዳጅ ዋጋ ይሰቀላል በማለት ሰፊ ትንታኔ የሰጡትም ከዚህ ቀደም በተመሳሳይ መንገድ ያጋጠሙ ክስተቶችን በመተራስ መሆኑ ይነገራል፡፡ በተለይ ዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት ከወራት በፊት ይፋ እንዳደረገው፣ ከአይኤስ ጋር የሚደረገው ፍልሚያ በዚሁ ከቀጠለ የነዳጅ ዋጋ ጭማሪ አይቀሬ መሆኑን ነበር፡፡ ነገር ግን እንደተገመተው ሳይሆን የነዳጅ ዋጋ ያልተጠበቀ ቅናሽ አሳየና የብዙዎች ግምት እንዳይሰምር አደረገ፡፡ የነዳጅ ዋጋ ሊጨምር ይችላል ሲባል ሊቀንስ የቻለው ደግሞ አሜሪካ ከፍተኛ ነዳጅ በማምረት ወደ ገበያው ማስገባትዋ ስለመሆኑ አንዳንድ መረጃዎች ያለመክታሉ፡፡ ከአይኤስ ጋር በሚደረገው ፍልሚያ ምርታቸውን ይቀንሳሉ የተባሉ አንዳንድ ነዳጅ አምራች አገሮች እንደተጠበቀው ሳይቀንሱ በመቅረታቸውና አሜሪካ ባልተጠበቀ መንገድ ምርቷን መጨመሯ ለነዳጅ ዋጋ መውረድ አንኳር ምክንያት ሆነው ይቀርባሉ፡፡ የነዳጅ ገበያ ተለዋዋጭ ባህሪይ ያለው ነው፡፡ ከጥቂት ወራት በፊት የታየው ቅናሽ እስከመቼ ይቀጥል ይሆን? የሚለውን ጥያቄ ለመመለስ ቢያስቸግርም፣ ሰሞናዊው የነዳጅ ዋጋ ቅናሽ በተለይ ለነዳጅ ግዥ ከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ ለሚያወጡ አገሮች መጠነኛ እፎይታ የሰጠ ነው፡፡ የነዳጅ ዋጋ መጨመርና መ