Posts

THE DEFINITIVE TOP 10 COFFEE-GROWING COUNTRIES IN THE WORLD, RANKED BY EXPERTS

Image
If coffee growing was an Olympic event, it'd be a marathon not a sprint. And not just because Africa totally dominates. Being a coffee superpower requires years of economic, infrastructural, and government investment. Plus a bean-friendly terrior, farmers dedicated to quality control, and a trust in industry buyers to bring the beans to the masses. So, which countries shell out the best beans? To get an idea, we asked a group of 11 roasters and writers to weigh in. Obviously, with all of the variables involved,  naming favorite countries is not an easy task . Almost all of our contributors expressed hesitation about throwing their hat into the ring (too much  Deadly Grounds ,  perhaps), and one roaster even pulled their choices for fear of upsetting their farmers. Naturally, personal bias in taste, education, and life experience influence one's picks, but by polling a diverse cross-section of the coffee world, we feel like this is an honest pulse of the industry,

በቡና ዘርፍ ማሻሻያ ሳይደረግ ከፍተኛ ገቢ ለማግኘት ታቀደ

•  ንግድ ሚኒስትር ሕገወጥ የቡና ንግድ ለመግታት ከነጋዴዎች ጋር መወያየት ጀመረ     • የቡና ላኪዎች ማኅበር የመፍትሔ ሐሳቦችን አቀረበ በቡና ወጪ ንግድ ዘርፍ የማሻሻያ ዕርምጃ ሳይወሰድ በ2007 በጀት ዓመት ከዘርፉ 900 ሚሊዮን ዶላር ለማግኘት ታቀደ፡፡ የንግድ ሚኒስቴር በበጀት ዓመቱ 235,000 ሜትሪክ ቶን ቡና ወደ ውጭ በመላክ 900 ሚሊዮን ዶላር ለማግኘት የተያዘውን ዕቅድ፣ በጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ የሚመራው ብሔራዊ የኤክስፖርት ምክር ቤት ማፅደቁ ታውቋል፡፡ ይኼንን ዕቅድ ለማሳካት ንግድ ሚኒስቴር በቅርቡ ዋነኛ ከሚላቸው 195 ቡና ላኪዎች ጋር ለመምከር እንደተዘጋጀ የሚናገሩት ምንጮች፣ ሚኒስቴሩ በቡና የወጪ ንግድ ዘርፍ ያሉትን መሠረታዊ ችግሮች እስካልፈታ ድረስ በታቀደው ዕቅድ ስኬት ላይ ጥርጣሬ እንዳላቸው እየገለጹ ነው፡፡ ‹‹በሕገወጥ ነጋዴዎች ምክንያት ሥራችን ለማካሄድ ተቸግረናል፤›› የሚሉ ቡና ላኪዎች ባይቀበሉትም፣ ንግድ ሚኒስቴር ሕገወጥ የቡና ንግድን ለማስቀረት ያስችላል ያለውን ሥራ ጀምሯል፡፡ ሚኒስቴሩ ደረስኩበት ያለው መረጃ እንደሚያመለክተው፣ በተለይ በአዲስ አበባ ከተማ በኤክስፖርት ደረጃ የተዘጋጀ ቡና በየሱፐር ማርኬቱና በየገበያው በብዛት ይገኛል፡፡ የዚህ ቡና ምንጩ አዲስ አበባ ውስጥ መፈልፈያ ጣቢያ ካላቸው ነጋዴዎች እንደሆነ የሚያስረዳው የሚኒስቴሩ መረጃ፣ እነዚህን ነጋዴዎች ማወያየት ያስፈልጋል የሚል ዕምነት እንዳሳደረ አመልክቷል፡፡ በዚህ መሠረት ካለፈው ሳምንት ጀምሮ የቡና መፈልፈያ ባለቤቶች ሚኒስቴሩ አንድ በአንድ እየጠራ በማነጋገር ላይ እንደሚገኝም ምንጮች ገልጸዋል፡፡ ነገር ግን ሕጋዊ ነኝ የሚሉ ነጋዴዎች በዚህ የሚኒስቴር ተግባር ዕምነት እንደሌላቸው ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡ ምክንያታቸው

ኢትዮጵያን ጨምሮ በአለማችን ከ800 ሚ. በላይ ህዝብ የምግብ እጥረት ተጠቂ ነው ተባለ

Image
ኢትዮጵያ ችግሩ ከተስፋፋባቸው አገራት አንዷ ናት ተብሏል          የአለማችን ህዝብ በአሁኑ ወቅት ከሚያስፈልገው የምግብ እህል ከሁለት እጥፍ በላይ ማምረት ቢቻልም፣ አሁንም ድረስ በተለያዩ የአለም አገራት የሚገኙ ከ800 ሚሊዮን በላይ ሰዎች በቂ ምግብ እንደማያገኙ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አስታወቀ፡፡ባለፉት አስርት አመታት በአለማችን የርሃብ ችግር በተወሰነ መልኩ ቢቀንስም ባለፉት ሁለት አመታት 11 ነጥብ 3 በመቶ የሚሆነው የአለማችን ህዝብ የምግብ እጥረት ተጠቂ እንደነበረ የጠቆመው ዘገባው፣ የምግብ እጥረቱ በከፍተኛ ሁኔታ ከሚታይባቸው አገራት መካከልም፣ ቻድ፣ መካከለኛው አፍሪካ ሪፐብሊክ እና ኢትዮጵያ እንደሚገኙበት ገልጿ ል፡፡ በቂ ምግብ የማያገኙ በርካታ ዜጎች ካሏቸው አገራት አንዷ በሆነችው ኢራቅ፤ ከአራት ኢራቃውያን አንዱ የምግብ እጥረት ችግር ሰለባ መሆኑንም፣ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በሳምንቱ መጀመሪያ ያወጣውን መረጃ በመጥቀስ ዘገባው ጠቁሟል ፡፡ የአለም የምግብና የእርሻ ድርጅት እንዳለው፣ ምንም እንኳን በአለማችን በአሁኑ ወቅት ከሚያስፈልገው የምግብ እህል ከሁለት እጥፍ በላይ ማምረት ቢቻልም፣ ምርቱን ለተመጋቢዎች በማድረስ ረገድ ክፍተቶች በመኖራቸው የምግብ እጥረት ችግሩ ሊቀረፍ አልቻለም፡፡ ምርታማነት ቢያድግም የተመረተውን የምግብ እህል ለሸማቾችና የችግር ተጋላጭ ለሆኑ የማህበረሰብ ክፍሎች ማድረስ ካልተቻለ፣ የምግብ እጥረቱ እንደማይቀረፍ የገለጸው ድርጅቱ፣ ለዚህም ሴፍቲ ኔትና ሌሎች የማህበራዊ ዋስትና አሰራሮችን ማጠናከር እንደሚገባ አስታውቋል፡፡ ከሚሊኒየሙ የልማት ግቦች አንዱ በታዳጊ አገራት የምግብ እጥረት የሚያጋጥማቸውን ዜጎች ቁጥር እስከ 2015 ድረስ በግማሽ መቀነስ መሆኑን ያስታወሰው ዘገባው፤ የተመድ ሪፖር

የሲዳማ ቡና በሲዳሞ ቡናነት መጠራቱን ዛሬም ቀጥሏል

Image
ከመቶ ኣመታት በላይ በኢትዮጵያ የነበረው የነፍጠኛው ስርዓት የህዝቦችን እና የኣከባቢዎቻቸውን መጠሪያ ሰሞች በመሰለኝ እና በደሳሌኝ በመቀየር የሚታወቅ ሲሆን፤ በዘፈቀደ የተለወጡት እነዚሁ መጠሪያ ስሞች በተለይ በዛሬው የህዝቦች ማንነት ላይ ተጽዕኖ በመፈጠር ላይ ናቸው። ሲዳማ የመጠረያ የስያሜ ሞድፊኬሽን ከተደረገባቸው ህዝቦች መካከል ኣንዱ ነው። በሲዳማ የነበረው የነፍጠኛው ስርዓት የሲዳማ ኣከባቢዎች መጠረያ ሰሞችን ላይ ብቻ ሳይሆን በህዝቡ መጠረያ ስም ላይም ለውጦችን እስከማድረግ ደርሷል። ለኣብነት ያህል በሲዳማ ብሔር መጠረያ ስም ላይ ከተደረገው ለውጥ በተጨማሪ በሲዳማ ከተሞች እና ወረዳዎች ላይ መሰል ሞድፊኬሽን ተደርጓባቸዋል፦ሐዋሳን ወደ ኣዋሳ፤ ሐርቤጎናን ወደ ኣርቤጎና፤ ሐሮሬሳን ወደ ኣሮሬሳ፤ ወዘተ ይገኙበታል። እነዚህ በዘፈቀደ የተደረጉት ለውጧች በብሔሩ ማንነት ላይ ኣሉታዊ ተጽዕኖ ከመፍጠራቸው በላይ ብሔሩ እና ክልሉ በሁለት ስያሜ እንድጠራ የግድ ብሎታል። ኣንድን ብሔር ወይም ህዝብ ያለኣግባብ በሁለት ስም መጥራት ባለው ኣሉታዎ የፖለቲካ እና ማህበራዊ እንድምታ ላይ በሌላ ጊዜ የምመለስበት ሲሆን፤ ለዛሬ ግን ይህ በነፍጠኛው የተተዎው የመጠረያ ስም ለውጥ ኣሻራ በሲዳማ ምርቶች ላይ መንጸባረቅ መቀጠሉን በተመለከተ ትንሽ ማለት እወዳለሁ። እንደምታወቀው በኣገሪቱ የመንግስት ለውጥ መደረጉን ተከትሎ በርካታ ኣከባቢዎች እና ህዝቦች በቀድሞው መጠረያ ሰሞቻቸው መጠራት ጀምረዋል። ሲዳማም ብሆን የዚህ እድል ተጠቃሚ መሆኑ እውን ነው። የመጠሪያ ሰሞችን ወደ ቀድሞ ስያሜዎቻቸው የመመለሱ ጉዳይ በብሔር እና በኣከባቢዎች ስያሜ ላይ ብቻ ሳይወሰን በብሔሩ እና በኣከባቢዎች ምርቶች ላይም ተግባራዊ በመደረግ ላይ ይገኛል። ለም