በደቡብ የአመራር አካላት ለስፖርት ትኩረት እንዲሰጡ ርዕሰ መስተዳድሩ አሳሰቡ፤ በኢትዮጵያ ፕሪሜዬር ሊግ የሲዳማ እግር ኳስ ክለቦች ነጥብ ኣልባ ጉዞ ቀጥሏል
የሲዳማ እግር ኳስ ክለቦች የሆኑት ሃዋሳ ከነማ እና ሲዳማ ቡና በሁለተኛው ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሜዬር ሊግ ጫዋታ በተገጣሚዎቻቸው በመሸነፋቸው በሊግ ያለ ምንም ነጥብ የመጨረሻ ደረጃዎችን ይዘው ይገኛሉ። በሌላ በኩል፤ የስፖርት ልማቱን በማጠናከር ጤናማና አምራች ዜጋ ለማፍራት የሚደረገው ጥረት ውጤታማ እንዲሆን በየደረጃው የሚገኙ የአመራር አካላት ትኩረት ሰጥቶ ሊሠሩ እንደሚገባ የደቡብ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አሳሰቡ። የደቡብ ክልል የስፖርት ምክር ቤት 17 ኛው መደበኛ ጉባዔ ከትናንት በስቲያ በሃዋሳ ተካሂዷል፡፡ ርዕሰ መስተዳድሩ አቶ ደሴ ዳልኬ ጉባዔውን ሲከፍቱ እንደተናገሩት፤ ጤናማና አምራች ዜጋ ለማፍራት ስፖርት ያለው ጠቀሜታ የጎላ በመሆኑ የክልሉ መንግሥት ለዘርፉ ዕድገት ትኩረት ሰጥቶ እየሠራ ይገኛል፡፡ « ውጤታማ የሆኑ ተተኪ ስፖርተኞችን የማፍራት፣ በጥናትና ምርምር ሥራዎች የክልሉን የስፖርት ዕድገት የመደገፍና ለኅብረተሰቡ አስፈላጊውን አገልግሎት የመስጠት ተልዕኮ ስኬታማ እንዲሆን የአመራሩ ድርሻ ከፍተኛ በመሆኑ ጠንክሮ መሥራት ይገባል » ብለዋል። በክልሉ የዘርፉን ዓላማ ለማስፈጸም በፋይናንስ፣ በአደረጃጀትና በአመራር የስፖርቱ ልማት ሕዝባዊ መሠረት እንዲኖረው የማድረግ፣ ከመንግሥት ድጎማ ተላቅቆ ራሱን እንዲችል ማድረግ ይጠበቃል። ኅብረተሰቡ በሚያመቸው ሁኔታ በስፖርታዊ እንቅስቃሴ ተሳታፊ እንዲሆን ማስቻል፣ እንዲሁም የሴቶችን እኩል ተሳትፎና ተጠቃሚነት የማረጋገጥ ሥራዎች በትኩረት ሊሠሩ እንደሚገባም አቶ ደሴ ጠቁመዋል፡፡ በክልሉ የስፖርት ልማት በማፋጠን የኅብረ ተሰቡን ተሳትፎና ተጠቃሚነት ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገርና ምርጥ ተተኪ ስፖርተኞችን በብዛትና በጥራት ለማፍራት የሚያግዙ የማስፈጸሚያ ስትራቴጂዎች፣ የሕግ ማዕቀፎች፣ የል