በደቡብ ክልል ከሲዳማ ብሄረሰብ ውጪ ፕሬዚዳንት ለማድረግ ኣይሞከርም ተባለ፤ ኣቶ አባተ ኪሾን መልሶ ለመሾም ውስወሳ ተጀምሯል
ኢህአዴግ በፖለቲካ ወለምታ ውስጥ!! ኢህአዴግ በ“ፖለቲካ ወለምታ” ውስጥ እንደሚገኝ ስማቸው እንዳይጠቀስ የጠየቁ አንድ የኢህአዴግ ዲፕሎማት ለጎልጉል ተናገሩ። በከፊል ኢህአዴግን የተለዩ የሚስሉት ዲፕሎማት በጎልጉል የቅርብ ሰው አማካይነት ድምጻቸው ሳይቀረጽ ባደረጉት ቃለ ምልልስ እንዳሉት የተፈጠረው የፖለቲካ ወለምታ አደጋ ሊያስከትል እንደሚችል አመልክተዋል። የኢህአዴግ ከፍተኛ ባለስልጣናት በመካከለኛ አመራሩ ውስጥ የመጠራጠር ስሜት መፈጠሩን በፓርቲ ግምገማ ላይ በግልጽ መናገራቸው የዲፕሎማቱን አስተያየት የሚያጠናክር ሆኖ ተገኝቷል። የፓርቲው ከፍተኛ አመራሮች የአቶ መለስን ሞት ደብቀው በመያዝና ማስተባበያ በመስጠት ጊዜ የወሰዱት ይኸው የተባለው የፖለቲካ ወለምታ እንዳይፈጠር ለማድረግ በማሰብ እንደነበር ዲፕሎማቱ ያስታውሳሉ። ይሁን እንጂ አቶ መለስ ሁሉንም ጉዳይና ሃላፊነት ብቻቸውን ይዘውት ስለነበር በድንገት ማለፋቸው ፓርቲው ውስጥ አሁን በየደረጃው የሚታየው የመተርተር አደጋ መከላከል ግን አልተቻለም። የፖለቲካ ወለምታ ስለመከሰቱ ማንም ማስተባበያ ሊያቀርብ አይችልም የሚሉት ዲፕሎማት በእርሳቸው እይታና ባላቸው መረጃ መሰረት ድርጅትን መክዳት፣ ድርሻዬ በሚል ገንዘብ ማሰባሰብ፣ ቤተሰብን በተለያዩ ምክንያቶች ማሸሽ፣ በቁልፍ የመከላከያ ሃላፊዎች ላይ ማነጣጠር፣ በግምገማ ስም ካድሬውን ማመስ፣ በስልጠና ስም የበታች አመራሮችን መደለል፣ ከሁሉም በላይ ማንኛውም ውሳኔ ሲወሰን በተናጠል እንዳይሆን የሚከለክል አሰራር መከተል የመሳሰሉት ተፈጠረ ለተባለው “ወለምታ” ዋና መግለጫዎች ናቸው። ፓርቲያቸው ኢህአዴግ የመለሰን ምስል እየለጠፈ “የታላቁን መሪ ውርስ ሳይበረዝ እናስቀጥላለን” የሚለው ውሸት እንደሆነ በመግለጽ ተጨማሪ ማሳያ የሚ