ኢሕአዴግ ቆራጥና ደፋር የውስጥ ትግል ያስፈልገዋል
ኢሕአዴግ በሕዝብ ተከብሮና ተደግፎ ጠንካራ መሠረት ይዞ ለመቀጠል ከፈለገ ይችላል፡፡ የሚችለው ግን ራሱን ሲያጠናክር ነው፡፡ ራሱን ማጠናከር የሚችለው ደግሞ ውስጡን ሲያፀዳ ነው፡፡ ውስጡን ማፅዳት የሚችለው ደግሞ ቆራጥና ደፋር የውስጥ ትግል ሲያካሂድ ነው፡፡ ደፋርና ቆራጥ የውስጥ ትግል ካካሄደ ፀድቶና ተጠናክሮ ይወጣል፣ ይቀጥላል፣ ይጓዛል፡፡ የለም አላደርግም፣ አልታገልም፣ አልቆርጥም፣ አልደፍርም ካለ ደግሞ ውስጥ ለውስጥ እየተሰነጣጠቀ፣ እየበሰበሰና እየተደረመሰ ይሄዳል፡፡ ይደክማል ከሕዝብ ይርቃል፡፡ የነበረው እንዳልነበረ ይሆናል፡፡ ኢሕአዴግ ቆራጥና ደፋር የውስጥ ትግል የሚያስፈልገው ለምንድን ነው? 1. ከላይ እስከታች በሙስና የተጨማለቁ በዝተዋል! አዎን ንፁኃን የሕዝብ አገልጋይ፣ ለልማትና ለለውጥ የቆሙና የሚታገሉ አባላትም አመራርም በኢሕአዴግ ውስጥ አሉ፡፡ በዚያው አንፃር ደግሞ ከሕዝባዊ መስመር እየራቁና እየሸሹ ለግል ገንዘብ፣ ንብረት፣ ክብርና ኔትዎርክ የሚሯሯጡ፣ በጉቦ የተጨማለቁና በሙስና የተነከሩ አሉ፡፡ እነዚህ በውስጥ ትግል፣ በደፋርና በቆራጥ ትግል ካልተገለሉና ድርጅቱ ካልፀዳ ድርጅቱን እያበሰበሱ የሚገድሉት ናቸው፡፡ 2. አቅም አልባ… ምላስ ብዙ በዙ! በብቃት መመደብ እየቀረ ደጋፊ እስከሆነ ችግር የለም እየተባለ የተሾመው ሁሉ የድርጅቱን ዓላማ ማራመድ አልቻለም፡፡ ሕዝቡንም ማገልገል አልቻለም፡፡ ባለአቅም እየጠፋ ባለምላስ በዛ፡፡ ተንዛዛ በጣም በዙ፡፡ ሕዝብ ይህንን እያየና እያስተዋለ ምንድን ነው ነገሩ? እያለ ነው፡፡ አይወስኑም፣ ቢሮ አይገቡም፣ አያሳምኑም፡፡ አንዳንዶቹም ይህን እያወቁ ሀቅን ከመጋፈጥ ይልቅ ሽሽትና ድብብቆሽ እየመረጡ ናቸው፡፡ ሕዝብ በድርጅቱ ላይ አመኔታ እንዲያጣ እያደረጉ ናቸው፡፡ 3. ጠንካራ አን