Posts

በሀዋሳ ከተማ የሚገኘው በተለምዶ አሞራ ገደል የሚገኘው የፍቅር ሀይቅ በቆሻሻ እየተበከለ ነው

Image
በሀዋሳ ከተማ የሚገኘው በተለምዶ አሞራ ገደል የሚገኘው የፍቅር ሀይቅ በቆሻሻ እየተበላሸ ሲሆን ሀይቁ በፌስታል፤ በጫት ገራባ፤ በብሰኩትና የመስቲካ ማሸጊዎች እየተጣለ ተቖጣጣሪ ባለቤት ያጣ ይመስላል፡፡ዛሬ እሁድ አፕሪል 15/2012 አካባቢውን የጎበኘሁ ሲሆን የመግቢያ ገንዘብ የሚስከፍሉ Sidama Development Association Hawassa Serial No.272892 ካርኒ ለሁለት ሰው 10 ብር የከፈልኩ ሲሆን ለምን በየተራ የተመደቡ ሰዎች ለምን እየተከታተሉ እነደማያፀዱ ጥይቄያቸው እናፀዳዋለን ከማለት በስተቀር የአንድ ቀን ቆሻሻ ስለማይመስል ትኩረት ሊሰጠው ይገባል፡፡እጅግ አሳዛኙ ነገር የከተማው ድሬኔጅ ኔትወርክ ከሐይቁ ጋር ሜያዙ እጅግ አሳፋሪ ስራ አየተሰራ መሆኑን የከተማው አካባቢ ተቆርቋሪዎች እየሞገቱ ሲሆን እስከአሁን ሰሚ ጆሮ ባለመገኘቱ የአካባቢ ተቆርቋሪዎች ድምፃቸውን ሳይሰለቹ በማሰማት ይህችን ውብ ከተማ ከብክለት ሊታደጓት ይገባል እያሉ ነው፡፡ በፎቶግራፉ ላይ የምትመለከቱት ቖሻሻ በአሞራ ገደል የፍቅር ሀይቅ በዚሁ ዕለት የተነሳ ነው፡፡  by Melaku Ayele from Hawassa

ለሁለት ቀናት በሀዋሣ ሲካሄድ የቆየው የሲዳማ ዞን ምክር ቤት 3ኛ ዙር 8ኛ መደበኛ ጉባኤ ሦስት የዞን ካቢኔዎችን ሹመትና ከ32 ነጥብ 8 በላይ ተጨማሪ በጀት በማፅደቅ ተጠናቀቀ፡፡

ለሁለት ቀናት በሀዋሣ ሲካሄድ የቆየው የሲዳማ ዞን ምክር ቤት 3ኛ ዙር 8ኛ መደበኛ ጉባኤ ሦስት የዞን ካቢኔዎችን ሹመትና ከ32 ነጥብ 8 በላይ ተጨማሪ በጀት በማፅደቅ ተጠናቀቀ፡፡የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ማሊዮን ማቴዎስ ለም/ቤቱ በእጩነት ያቀረቧቸው ካቢኔዎች የዞኑ ግብይትና ህብረት ስራ መምሪያ ኃላፊ የከተማ ልማት መምሪያ ኃላፊ እንዲሁም የሲቪል ሰርቪስ መምሪያ ኃላፊ በመሆን በም/ቤቱ ሙሉ ድምፅ መመረጣቸው ታውቋል፡፡ በተጨማሪም ም/ቤቱ ለቀጣይ ወራት የዞን ማዕከል፣ 19 ወረዳዎችና ሁለት የከተማ አስተዳደሮች ለልማትና ለመልካም አስተዳደር ስራዎች እንዲሁም ለሰራተኞች ደመወዝ ክፍያ የሚጠቀሙበትን ከ32 ነጥብ 8 ሚሊዮን በላይ በጀት ማፅደቁ ተመልክቷል፡፡ በም/ቤቱ የኢኮኖሚ ጉዳይ ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ ሲምቦ ሽብሩ የተጨማሪ በጀት ደንብ ሰነድ ለም/ቤቱ አባላት ሲያቀርቡ ከተመደበው ተጨማሪ በጀት ከ6 ነጥብ 9 በላይ ሚሊዮን በ2ዐዐ3 የበጀት አመት በተለያዩ ምክንያት ስራ ላይ ያልዋለ መሆኑን ገልፀዋል፡፡ ቀሪው ከ25 ነጥብ 9 በ ላይ ሚሊዮን በጀት ደግሞ የዞኑ ማዕከል፣ ወረዳዎችና ከተማ አስተዳደሮች ከእቅዳቸው በላይ የሰበሰቡት መሆኑን አቶ ሱምቦ መጠቆማቸውን የዘገበው የዞኑ ባህል ቱሪዝም የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ነው፡፡

የዳራ ወረዳ ውና፣ ማዕድንና ኢነርጂ ጽህፈት ቤት ከ2 ነጥብ 1 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ ህብረተሰቡን ንፁህ የመጠጥ ውሃ ተጠቃሚ ለማድረግ መንግስታዊ ካልሆነ ድርጅት ጋር በመቀናጀት እየሰራ መሆኑን ገለፀ፡

የዳራ ወረዳ ውና፣ ማዕድንና ኢነርጂ ጽህፈት ቤት ከ2 ነጥብ 1 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ ህብረተሰቡን ንፁህ የመጠጥ ውሃ ተጠቃሚ ለማድረግ መንግስታዊ ካልሆነ ድርጅት ጋር በመቀናጀት እየሰራ መሆኑን ገለፀ፡፡ የጽህፈት ቤቱ የመጠጥ ውሃ አቅርቦትና የተቋማት አስተዳደር ሥራ ሂደት አስተባባሪ ተወካይ አቶ ባንታየሁ ጉዲሳ አንደገለፁት በንፁህ የመጠጥ ውሃ አቅርቦትና ሳኒቴሽን ኘሮግራም እቅድ ከተያዙት 17 ምንጮች የ12ቱ ግንባታ 87 በመቶ ተጠናቋል፡፡ የግንባታው ወጪም 85 በመቶ ትንሳኤና ብርሃን በተሰኘ ግብረ ሰናይ ድርጅት የሚሸፈን ሲሆን 15 በመቶ በወረዳው በጀት ይሸፈናል፡፡ግንባታው ሲጠናቀቅ የወረዳው የንፁህ መጠጥ ውሃ ሽፋን 38 ነጥብ 8 በመቶ ይደርሳል ማለታቸውን የወረዳው የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጽህፈት ቤት ዘግቧል፡፡ Source: http://www.smm.gov.et/_Text/20MegTextN404.html

የእናቶችንና የህፃናትን ሞት ለመቀነስ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑን በሲዳማ ዞን የአለታ ወንዶ ወረዳ ጤና ጥበቃ ጽህፈት ቤት አስታወቀ፡፡

Image
የእናቶችንና የህፃናትን ሞት ለመቀነስ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑን በሲዳማ ዞን የአለታ ወንዶ ወረዳ ጤና ጥበቃ ጽህፈት ቤት አስታወቀ፡፡የጽህፈት ቤቱ ኃላፊ አቶ ታደሰ አነቦ ባለፉት ወራት የእናቶችን ሞት ለመቀነስ በተደረገው እንቅስቃሴ ለ2 ሺህ 985 እናቶች የቅድመ ወሊድና የድህረ ወሊድ ምርመራ እንዳደረገላቸውም ተናግረዋል፡፡ 14 ሺህ 49ዐ እናቶች የቤተሰብ ምጣኔ አገልግሎት ተጠቃሚ መሆናቸውን አብራርተው ቁጥራቸው በተጨማሪም እናቶች በባለሙያ የተደገፈ የወሊድ አገልግሎት እያገኙ መሆናቸውን ጠቁመዋል፡፡በአንፃሩ የህፃናትን ሞት ለመቀነስ በተደረገው ርብርብ 3 ሺህ 383 ህፃናት የተለያዩ በሽታዎችን የሚከላከል ክትባት ማግኘታቸው መለሰ ሱኩሌ ከበንሳ ቅርንጫፍ ጣቢያ ዘግቧል፡፡ ምንጭ:  http://www.smm.gov.et/_Text/16MegTextN304.html

ከ2 ነጥብ 5 ሚሊዮን በሚበልጥ ወጪ የንፁህ መጠጥ ውሃ ግንባታው ስራ እየተከናወነ መሆኑን በሲዳማ ዞን የአለታ ወንዶ ወረዳ ውሃ፣ ማዕድንና ኢነርጂ ጽህፈት ቤት አስታወቀ፡፡

ከ2 ነጥብ 5 ሚሊዮን በሚበልጥ ወጪ የንፁህ መጠጥ ውሃ ግንባታው ስራ እየተከናወነ መሆኑን በሲዳማ ዞን የአለታ ወንዶ ወረዳ ውሃ፣ ማዕድንና ኢነርጂ ጽህፈት ቤት አስታወቀ፡፡ የጽህፈት ቤቱ የመጠጥ ውሃ አቅርቦትና የተቋማት አስተዳደር ዋና የስራ ሂደት አስተባባሪ አቶ ዘለቀ በላይነህ እንደገለፁት ህብረተሰቡን ከውሃ ወሊድ በሽታ ለመታደግና የንፁህ መጠጥ ውሃ ተጠቃሚ ለማድረግ የዘጠኝ አነስተኛና መለስተኛ የውሃ ተቋማት ግንባታዎች እየተካሄደ ይገኛል ብለዋል፡፡በአሁኑ ጊዜ እየተገነቡ ከሚገኙ መካከልም 1 የጥልቅና 3 መለስተኛ የውሃ ጉድጓድ እንዲሁም 5 የአዳዲስ ምንጮች ግንባታ እንደሚገኝ አስተባባሪው አስረድተዋል፡፡ሲል መለሰ ሱኩሌ ከበንሳ ቅርንጫፍ ጣቢያ ዘግቧል፡፡