ዛሬ ሲዳማ ቡና ከ መብራት ኃይል በኣዲስ ኣበባ፤ ሃዋሳ ከነማ ከሙገር ስሚንቶ በሃዋሳ ይጫዋታሉ

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 13 ፣ 2006 (ኤፍ.ቢ.ሲ.) 21ኛው ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ በተለያዩ ጨዋታዎች ይቀጥላል። በዚህም መሰረት በዛሬው ዕለት በ9 ሰዓት መብራት ሃይል ከሲዳማ ቡና በአበበ በቂላ ስታዲየም ሲጋጠሙ ፥  ደደቢት ከዳሸን ቢራ ፣ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከሀረር ቢራ በተመሳሳይ ሰዓት በአዲስ አበባ ስታዲየም ይጫወታሉ።
በክልል ጨዋታዎችም ሃዋሳ ላይ  ሀዋሳ ከነማ ከሙገር ስሚንቶ እንዲሁም  ወላይታ ዲቻ ከአርባምንጭ ከነማ ይገናኛሉ።
አምስት ጨዋታዎች ብቻ በሚቀሩት ሻምፕዮናው ፥ የሊጉን ዋነጫ ለማንሳት ቅዱስ ጊዮርጊስ አንድ ነጥብ ብቻ ያስፈልገዋል።

Comments

Popular posts from this blog

ስለከሸፈው “መክሸፍ እንደ ኢትዮጵያ ታሪክ” ጥራዝ አንዳንድ ነጥቦች

SIDAMA Micro-Finance Institution

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት