ቅዱስ ጊዮርጊስና ሲዳማ ቡና ተጋጣሚዎቻቸውን አሸነፉ

አዲስ አበባ የካቲት 12/2006 በኢትዮጵያ ፕሪሚዬር ሊግ በ11ኛው ሳምንት ጨዋታ ቅዱስ ጊዮርጊስ መሪነቱን አጠናከረ።
ቅዱስ ጊዮርጊስ  ትናንት ጨዋታውን  ከሐዋሳ ከነማን ጋር አድርጎ  1ለ 0 በሆነ ውጤት በማሸነፉ ከሌሎች ቡድኖች ጋር ያለውን የነጥብ ልዩነት ይበልጥ እያሰፋ ነው።
በኃይሉ አሰፋ ለቅዱስ ጊዮርጊስ ብቸኛዋንና ለአሸናፊነት ያበቃቻቸውን ግብ አስቆጥሯል።
ቅዱስ ጊዮርጊስ  ዘጠኝ ጨዋታዎችን አድርጎ በ 27 ነጥብ አንዱንም ሳይሸነፍ የሊጉን መሪነት እንደያዘ ነው።
በሌላ በኩል  ሲዳማ ቡናና  ሙገር ሲሚንቶን በይርጋለም ላይ ባካሄዱት ጨዋታ ሲዳማ ቡና  2 ለ1 በሆነ ውጤት አሸንፏል።አሁን ላይ  ሲዳማ ቡና 9 ነጥቦች ያሉት ሲሆን ይህን  ጨዋታ በማሸነፉ  ከወራጅ ቀጠና ለመውጣት ችሏል።
የቅዱስ ጊዮርጊሱ ኡመድ ኡክሪ በ9 ጨዋታዋች 9 ጎሎች በማስቆጠር የፕሪሚሪ ሊጉን የኮከብ ግብ አግቢነቱን እየመራ ይገኛል።

Comments

Popular posts from this blog

ስለከሸፈው “መክሸፍ እንደ ኢትዮጵያ ታሪክ” ጥራዝ አንዳንድ ነጥቦች

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

SIDAMA Micro-Finance Institution