Posts

ሁለት የሃዋሳ ከተማ ተጫዋቾችን የያዘው የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ከቱርክ አቻው ጋር የወዳጅነት ግጥሚያ እንዲያደርግ መታቀዱን ተሰማ

Image
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 19፣ 2006 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ከቱርክ አቻው ጋር የወዳጅነት ግጥሚያ እንዲያደርግ መታቀዱን አሰልጣኝ ማሪያኖ ባሬቶ አስታወቁ። አሰልጣኝ ማሪያኖ ባሬቶ በዛሬው እለት ስለቡድኑ አጠቃላይ እንቅስቃሴ መግለጫ በሰጡበት ወቅት ነው ይህን ያሉት። አሰልጣኙ መግለጫ ከሰጡባቸው ዋነኛ ሀሳቦች መካከል ፥ የመረጧቸው 38 ተጨዋቾች የዝግጅት ሂደት ምን ይመስላል የሚለው ይጠቀሳል። በተጨማሪም ዋነኛ አላማቸው በ2015 በሞሮኮው የአፍሪካ ዋንጫ መሳተፍ እንደሆነ በመግለፅ፥ አልጄሪያን ከመግጠማቸው በፊትም የወዳጅነት ጨዋታ ወደ ቱርክ አቅንተው ለመጫወት እንደታሰበ አስረድተዋል። አብዛኛውን ተጨዋቾች በደንብ ስለሚያውቋቸው ም/አሰልጣኝ ፋሲል ተካልኝ እና ዳንኤል  ፀሀዬን እኔው እራሴ ምክትሎቼ አድርጌ መርጫቸዋለው ብለዋል በመግለጫቸው ላይ። ከ20 አመት በታች የሚገኙ ተጨዋቾች የሚሳተፉበት  ክለቦች ሊግ በአገር ውስጥ ሊኖር እንደሚገባ እና  ተተኪዎችን ለማፍራት ከ14  ፣ 17 እና ከ20 አመት በታች ተጨዋቾች ላይ መሰራት እንደሚኖርበትም ነው የገለፁት። ዜናው የፋና ነው

በስነ ምግባር የታነጸ ዜጋ በመፍጠር ፆታዊ ጥቃትን ለመከላከል የሃይማኖት ተቋማት መከሩ

Image
በስነ ምግባር የታነጸ ዜጋ በመፍጠር ፆታዊ ጥቃትን ለመከላከል በሃይማኖት ተቋማት ሚና ላይ የተዘጋጀ ክልል አቀፍ የሃይማኖት ተቋም የሁለት ቀን የምክክር ጉባኤ የአቋም መግለጫ በማውጣት ትናንት ማምሻውን ተጠናቋል፡፡ ከተሳታፊዎቹ መከካል የደቡብ ክልል የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ሰብሳቢ የሲዳማ፣ የቡርጂና ጌድኦ ሀገር ስብከት ስራ አስኪያጅ ሊቀ ጉባኤ አባ ሀብተማርያም ገብረመስቀል እንደተናገሩት ያለስነ ምግባር የሚካሄድ ማንኛውም ስራ ሂደቱ አስቸጋሪ ውጤቱም አስከፊ በመሆኑ በስነ ምግባር የተገነባ ዜጋ ለመፍጠር ከሃይማኖት ተቋም አባቶች ብዙ ይጠበቃል፡፡ የአከባቢን ስነ ምህዳር በመጠበቅ ለሰው ልጆች ምቹና ተስማሚ የመኖሪያ ስፍራ ለመፍጠር፣ልማትን ከሙስና ማጽዳት፣ ስራን ከስህተትና ከጉዳት ለመከላከል በሚደረገው ጥረት ሁሉ የሃይማኖት አባቶችና ተከታዮቻቸው የበኩላቸውን አስተዋጽኦ ሊያደርጉ እንደሚገባም አሳስበዋል፡፡ ጉባኤው በስነ ምግባር የታነፁ ዜጎችን ለማፍራትና በሴቶች ላይ የሚደርሰውን ፆታዊ ጥቃት እንዲሁም ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶችን ለማስወገድ ሁሉም የሃይማኖት ተቋማት ሚና ምን መሆን እንዳለበት ግልፅ አቅጣጫ ያሳየ ነው ብለዋል፡፡ የደቡብ ክልል የእስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ፕሬዜዳንትና የሃይማኖት ተቋማት ምክትል ሰብሳቢ ሀጂ ሚፍታህ ሰኢድ በመከባበርና በሰላም አብሮ በመኖር የሚያምኑ፣በልማትና ዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ሂደት ሀገራዊ ሃላፊነት መሸከም የሚችሉ ዜጎችን የማፍራት ጉዳይ ልዩ ትኩረት ሊሰጠው ይገባል ብለዋል፡፡ ጠንካራ የስራ ባህል ያላቸው፣ በራሳቸው የሚተማመኑና ከማንኛውም ጥገኛ ልማድ ነፃ የሆኑ ፣ ኃላቀር አስተሳሰቦችን በመዋጋት እውቀትን የመሻት ዝንባሌ የተላበሱ ወጣቶችን ለማፍራት ከሃይማኖት ተቋማት ብዙ የሚጠበቅ በመሆኑ ጠንክረው

የሻምበል አበበ ብቂላ ማራቶን በሐዋሳ ተካሄደ

Image
ዜናው የሪፖርተር ጋዜጣ ነው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን በየዓመቱ የሚያዘጋጀው የሻምበል አበበ ብቂላ ማራቶን ባለፈው እሑድ በሐዋሳ ከተማ ሲካሄድ በወንዶች የፌዴራል ፖሊስ ስንታየሁ ለገሰ፣ በሴቶች ደግሞ የመከላከያዋ አፀደ ባይሳ አሸናፊ ሆነዋል፡፡ በ1956 በሮም፣ እንዲሁም በ1960 ዓ.ም. በቶኪዮ በተዘጋጁት የኦሊምፒክ ውድድሮች በማራቶን የወርቅ ሜዳሊያዎችን በማስመዝገብ ከአገሩ አልፎ አፍሪካን እንዳኮራ የሚነገርለት ሻምበል አበበ ብቂላ አሁንም ድረስ በስመ ገናናነቱ ይጠቀሳል፡፡ በተለይ ደግሞ በሮም አውራ ጎዳናዎች 42 ኪሎ ሜትር ከ195 ሜትር የሚሸፍነውን ማራቶን በባዶ እግሩ ሮጦ የወርቅ ሜዳሊያ ያስመዘገበበት ታሪኩ በአራት ዓመት አንድ ጊዜ እየተዘጋጀ ዛሬ ላይ ለደረሰው ዘመናዊ ኦሊምፒክ ተምሳሌት እንደሆነም ይገኛል፡፡ ‹‹ኢትዮጵያና አትሌቲክስ የአንድ ሳንቲም ሁለት ገጽታ›› ሆነው እንዲቀጥሉ ፈር ቀዳጅ መሆኑ ለሚመገርለት ሕያው አትሌት፣ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን በስሙ የማራቶን ውድድር ማዘጋጀት ከጀመረ ሦስት አሠርታት አስቆጥሯል፡፡ በዚሁ መሠረት ባለፈው እሑድ ሰኔ 15 ቀን 2006 ዓ.ም. በሐዋሳ ባከናወነው ማራቶን በወንዶች ከፌዴራል ፖሊስ ስንታየሁ ለገሰ ርቀቱን 2 ሰዓት፣ 13 ደቂቃ፣ 28 ሰከንድ፣ በሆነ ጊዜ አጠናቆ አንደኛ ሲወጣ፣ ረጋሳ ምንዳዬ ከኦሮሚያ 2 ሰዓት፣ 13 ደቂቃ፣ 30 ሰከንድ ከፌዴራል ፖሊስ ገዛኸኝ አበራ 2 ሰዓት፣ 13 ደቂቃ፣ 32 ሰከንድ በመግባት ሁለተኛና ሦስተኛ ሆነዋል፡፡ በሴቶች ከመከላከያ አፀደ ባይሳ 2 ሰዓት፣ 45 ደቂቃ፣ 60 ሰከንድ፣ እንዲሁም ከዚሁ ክለብ እመቤት ኢተአ 2 ሰዓት፣ 47 ደቂቃ፣ 25 ሰከንድ ስትወጣ፣ በግል የቀረበችው ሻሾ     2 ሰዓት፣ 47 ደቂቃ፣ 26 ሰከንድ ሦስተኛ በ

የደመወዝ ጭማሪው የዋጋ ንረት እንደማያስከትል ግልጽ መደረግ አለበት!

Image
የዋጋ ንረትን በተመለከተ ሰሞኑን ሁለት ተቀራራቢ የሆኑ ክስተቶች ተሰምተዋል፡፡ የመጀመሪያው የማዕከላዊ ስታትስቲክስ ባለሥልጣን የግንቦት ወር 2006 ዓ.ም. የዋጋ ንረትን በማስመልከት ያወጣው ሪፖርት ሲሆን፣ ሁለተኛው መንግሥት የዋጋ ንረትን በማይቀሰቅስ ሁኔታ ለመንግሥት ሠራተኞች የደመወዝ ጭማሪ ለማድረግ መወሰኑ ነው፡፡ ይህ ውሳኔ ለሠራተኛው ሕዝብ መልካም ብሥራት ነው፡፡ ነገር ግን የተጠና መሆን አለበት፡፡ የማዕከላዊ ስታትስቲክስ ባለሥልጣን ሪፖርት እንደሚያሳየው በግንቦት ወር የአገሪቱ አጠቃላይ የዋጋ ንረት 8.70 በመቶ በማስመዝገብ፣ በመላ አገሪቱ ባለፉት 15 ወራት የዋጋ ንረቱ በነጠላ አኃዝ እንደቀጠለ ነው፡፡ የዋጋ ንረቱ እ.ኤ.አ. ከማርች 2013 ጀምሮ በነጠላ አኃዝ መቀጠሉን ለመንግሥት እንደ ስኬት እንደሚታይ ሪፖርቱ ያብራራል፡፡ የዋጋ ንረቱ በነጠላ አኃዝ መቀጠሉ አዎንታዊ ገጽታ ነው፡፡ ይሁንና መንግሥት ከሐምሌ ወር ጀምሮ ለመንግሥት ሠራተኞች ደመወዝ እጨምራለሁ ሲል ያቀረበው ታሳቢ ጭማሪው የዋጋ ንረት የማያስከትል መሆኑን ነው፡፡ ጥያቄ የሚነሳውም እዚህ ላይ ነው፡፡ የደመወዝ ጭማሪ ሲደረግ የዋጋ ንረት እንደማይባባስ የሚደረገው ምን ዓይነት ዕርምጃዎችን ወይም መለኪያዎችን በማሰብ ነው? ለመንግሥት ሠራተኞች የሚደረገው የደመወዝ ጭማሪ ኢኮኖሚው ተረጋግቶ መቀጠል በሚችልበት ሁኔታ ተጠንቶ ተግባራዊ እንደሚደረግ መንግሥት መወሰኑ ተገልጿል፡፡ ይህ እንዴት ተግባራዊ ይሆናል የሚለው ጥያቄ ደግሞ መነሳቱ የግድ ነው፡፡ ከዚህ ቀደም በአገሪቱ ተከስቶ የነበረው አጠቃላይ የዋጋ ንረት እስከ 40 በመቶ ደርሶ እንደነበር የሚታወስ ሲሆን፣ የኅብረተሰቡን ኑሮ በምን ያህል ደረጃ አመሰቃቅሎት እንደነበርም አይዘነጋም፡፡ የዋጋ ንረቱ አሁን በነጠላ አኃዝ ላይ

በኢትዮጵያ የኣሜሪካን ኤምባሲ ባዘጋጀው የጆርናሊዝም ተማሪዎች ውድድር የሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ የሶሰተኛነት ደረጃ ኣገኘ

Image
Cover caption:  Public Affairs Officer Robert Post (second from left) with winning students (left to right): Feven Abreham, Etsubdink Hailu and Endalekachew Abebe  Photo: US Embassy በኢትዮጵያ የኣሜሪካን ኤምባሲ ባዘጋጀው የጆርናሊዝም ተማሪዎች ውድድር የሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ የሶሰተኛነት ደረጃ  ከማግኘቱ በላይ ከኤምባሲው የጆርናሊዝም እና የኮሙኒኬሽን መጽሐፍት ተለግሶለታል። ዝርዝር ዜናው የኣዲስ ስታንዳርድ ነው፦ The U.S. Embassy in Addis Ababa presented awards to three university students as part of the Embassy’s second Student Journalism Competition. The objective of the competition is to encourage students to gain practical experience in journalism that can be applied to their future careers.A panel of judges, including practicing journalists, reviewed the entries and judged them based on content, presentation, use of resources and research materials.  The competition was conducted among university and college students throughout the country. Students submitted stories that were published or broadcast in public or private media outlets.  The event w