Posts

Marriot International soon in Hawassa

Image
Following the continually rising interest of investing in Ethiopia in all aspects and the double digit economic growth it celebrated for the last decade, the country is becoming the conference hub of the continent. This has been making conference tourism, one of the investment area attracting foreign investors. In an attempt to reap the opportunity, thus, created the presence of international brand hotels in the nation's hospitality sector is expanding. Marriot International is not the exception. As part of a management deal sealed between Marriot and Sunshine Construction plc, Sunshine has laid a corner stone in Hawassa town on last Sunday, May 8, 2014. The CEO and owner of Sunshine, Samuel Tefese was accompanied by the President of Southern Region, Dessie Dalkie and the city mayor of Hawassa, Yonas Yosef (middle) during the laying of the corner stone. Source

የጉምሩክ አዋጅ ሊሻሻል ነው

-  ክስ የማይመሠረትባቸው የጉምሩክ ጥፋቶች ተዘርዝረዋል     -  የምርት ሒደታቸውን ባላጠናቀቁ ምርቶች ላይ የቀረጥ ነፃ አሠራር ይፈቅዳል      -   ዋና ዳይሬክተሩ ክስ አለመመሥረት የሚችልባቸው አሠራሮች ተቀምጠዋል በ2001 ዓ.ም. ፀድቆ ሥራ ላይ የዋለውን የጉምሩክ አዋጅ የሚያሻሽልና የአገሪቱን የማኑፋክቸሪንግ ዘመቻ የመደገፍ ግብ የያዘ የጉምሩክ ማሻሻያ አዋጅ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቀረበ፡፡ አዋጁ ለአገር ውስጥ ፍጆታ የሚውሉ የምርት ሒደታቸውን ያላጠናቀቁ ምርቶች ከቀረጥ ነፃ ገብተው በጉምሩክ ቁጥጥር ሥር የምርት ሒደታቸውን እንዲያጠናቅቁ ይፈቅዳል፡፡ ምንጭ በአገሪቱ እየታየ ያለው የኢኮኖሚ ዕድገት የሚጠይቀው የጉምሩክ አሠራርን ማካተት አስፈላጊ መሆኑን መንግሥት ስላመነበት ማሻሻያ ረቂቁ መዘጋጀቱን፣ ባለፈው ሐሙስ ለፓርላማ የቀረበው የአዋጁ ማብራርያ ይገልጻል፡፡ አዋጁን ለማሻሻል ምክንያት ከሆኑት መካከል የወጪና ገቢ ንግድ ዕድገት፣ በተለይም የማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪ ልማት የሚጠይቃቸውን ቀልጣፋ የጉምሩክ አገልግሎት ለመስጠትና የተመጣጠነ ቁጥጥር ለማድረግ የሚያስችሉ አሠራሮችን ሥራ ላይ ለማዋል፣ ዘመናዊና በዓለም አቀፍ ደረጃ ተቀባይነት ያገኙ የጉምሩክ አሠራሮችን ለማስፈጸም የሚያስችል ሕግ ማውጣት አስፈላጊ መሆኑ ይገኙበታል፡፡ አዋጁ ካካተታቸው ዋና ዋና ለውጦች መካከል የምርት ሒደታቸውን ሳያጠናቅቁ ወደ አገር የሚገቡ ዕቃዎች ያለቀረጥ የሚስተናገዱበትና በጉምሩክ ቁጥጥር ሥር የሚጠናቀቁበት አሠራር አንዱ ነው፡፡ ይህ አሠራር ከውጭ አገር የመጡ ዕቃዎች ለአገር ውስጥ ፍጆታ ከመለቀቃቸው በፊት አገር ውስጥ የምርት ሒደታቸውን የሚያጠናቅቁበትና ለአገር ውስጥ ፍጆታ ሲለቀቁ ቀረጥና ታክስ እንዲከፈልባቸው የሚደረግበት አሠራር መሆኑን የ

Ethiopia ranks second poorest country in the world - Oxford University Study

nazret.com - According to The Global Multidimensional Poverty Index (MPI), published by  Oxford University , Ethiopia ranks the second poorest country in the world just ahead of Niger. The study is based on analysis of acute poverty in 108 developing countries around the world. Despite making progress at reducing the percentage of destitute people, Ethiopia is still home to more than 76 million poor people, the fifth largest number in the world after India, China, Bangladesh and Pakistan. India has the world's largest number of poor people at more than 647 million. 87.3% of Ethiopians are classified as MPI poor, while 58.1% are considered destitute. A person is identified as multidimensionally poor (or 'MPI poor') if they are deprived in at least one third of the weighted MPI indicators. The destitute are deprived in at least one-third of the same weighted indicators, The Global MPI uses 10 indicators to measure poverty in three dimensions: education, health and living

የሃዋሳ ከተማ የወደፊት እጣፋንታ ከወዲሁ ለመገመት እንዲያስችሎት

Image
...  በአገሪቱ ያልተማከለና የተመጣጠነ የከተሞች ዕድገትን ለማረጋገጥ ዘጠኝ የከተማ ዕድገት መሰላሎችና ዞኖች በአዲስ አበባ፣ በመቐለ፣ በባህር ዳር፣ በነቀምቴ፣ በወልዲያ/ኰምቦልቻ፣ በጅማ፣ በድሬዳዋ፣ በሐዋሳና በጐዴ እንደሚፈጠሩና የአዲስ አበባና የኦሮሚያ ልዩ ዞን ስኬት ለእነዚህ ስምንት ከተሞች እንደ መልካም ተሞክሮም እንደሚያገለግል መረጃው ያመለክታል፡፡... የሃዋሳ ከተማ የወደፊት እጣፋንታ ከወዲሁ ለመገመት እንዲያስችሎት  የሚከተለውን ጽሑፍ ያንቡ፦ የተቀናጀው ማስተር ፕላን በልማትና በፖለቲካዊ ጥያቄዎች መካከል ባለፈው ሳምንት ግንቦት 30 ቀን 2006 ዓ.ም. የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የፌዴራሊዝም ጥናት ማዕከልና የደቡብ አፍሪካው ዌስተርን ኬፕ ዩኒቨርሲቲ በመተባበር ያዘጋጁት ሴሚናር በከተሞች አስተዳደር ላይ ያተኮረ ነበር፡፡ የሴሚናሩ ተሳታፊዎች ከምሁራን፣ ከመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች፣ ከኦሮሚያ፣ ከአዲስ አበባና ከፌዴራል የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት፣ ከፌዴሬሽን ምክር ቤት አባላት፣ ከተለያዩ የጥናትና ምርምር ተቋማት ተወካዮች፣ ከፌዴራሊዝም ተማሪዎችና ከሌሎች የሚመለከታቸው አካላት የተውጣጡ ነበሩ፡፡ ከላይ የተገለጸው ሴሚናር ከመካሄዱ ከሁለት ቀናት በፊት የአዲስ አበባና በአዲስ አበባ ዙሪያ የኦሮሚያ ልዩ ዞን የተቀናጀ ማስተር ፕላን ፕሮጀክት ጽሕፈት ቤት ለውጭ ሚዲያዎችና በእንግሊዝኛ ቋንቋ ለሚሠሩ ሚዲያዎች በማስተር ፕላኑ የዝግጅት ሒደት ላይ ጋዜጣዊ መግለጫ የሰጠ ሲሆን፣ በጽሕፈት ቤቱ ዳይሬክተር በአቶ ማቴዎስ አስፋው የተመራው ቡድን አዲስ አበባንና ኦሮሚያን የወከሉ ኃላፊዎችን አካቶ ለተለያዩ ጥያቄዎች ምላሽ ለመስጠት ሞክሯል፡፡ በሁለቱ ቀናት ዝግጅቶች ትኩረት የሳበው አጀንዳ የአዲስ አበባና የኦሮሚያ ክልል ግንኙነት ነው፡

ችግር ለሚፈጥሩ ቡና ላኪዎች የሥነ ምግባር ደንብ ተዘጋጀ

Image
ችግር የሚፈጥሩ የቡና ነጋዴዎች አደብ እንዲገዙ ያደርጋል የተባለ የሥነ ምግባር ደንብ ተዘጋጀ፡፡ ደንቡን ያዘጋጀው የኢትዮጵያ ኮፊ ኤክስፖርተርስ አሶሴሽን ሲሆን፣ ማኅበሩ በዚህ ሳምንት በጠራው ጠቅላላ ጉባዔ ደንቡን ያፀድቀዋል ተብሎ እንደሚጠበቅ ምንጮች ገልጸዋል፡፡  የተዘጋጀው የሥነ ምግባር ደንብ በተለይ ከውጭ አገር ገዥዎች ጋር የገቡትን የቡና ሽያጭ ስምምነት ውል የማያከብሩ ነጋዴዎች በአገሪቱ ቀጣይ የቡና ግብይት ላይ ሳንካ የሚፈጥሩ የቡና ኤክስፖርተሮችን ከጨዋታ ውጭ እንዲሆኑ ማድረግ የሚያስችል ዕርምጃ ለመውሰድ ከማስቻሉም በተጨማሪ፣ የሥነ ምግባር ችግር አለባቸው ተብለው የተፈረጁ ኤክስፖርተሮችን ጥቁር መዝገብ ውስጥ ያሳፍራል ተብሏል፡፡ የኢትዮጵያ ቡና ላኪዎች ማኅበር ከሌሎች አገሮች የቡና ላኪ ማኅበራት፣ በአፍሪካና በዓለም አቀፍ ደረጃ ከተቋቋሙ የቡና ማኅበራት ጋር ግንኙነት ያለው በመሆኑ፣ ኢትዮጵያ ውስጥ ጥቁር መዝገብ ውስጥ የገባ የቡና ኤክስፖርተር እነዚህ ተቋማት በሙሉ እንዲያውቁት ይደረጋል ተብሏል፡፡  ይህም አጥፊ ከተባለው ኤክስፖርተር ጋር ቀጣይ ግብይት ማድረግ አደጋ እንደሚመጣ ጠቋሚ በመሆኑ የተፈረጀው ላኪ ችግር ውስጥ ይወድቃል ተብሏል፡፡ ማኅበሩ ጥቁር መዝገብ ውስጥ ያሰፈረው ቡና ላኪ በመንግሥት በኩልም ምርመራ ተካሂዶበት ለቅጣት እንደሚዳረግም ተገልጿል፡፡ በማኅበሩ የተዘጋጀው የሥነ ምግባር ደንብ የንግድ ሚኒስቴር፣ ግብርና ሚኒስቴር፣ የኢትዮጵያ ምርት ገበያን ጨምሮ የተለያዩ የሚመለከታቸው አካላት አስተያየት እንዲሰጡበት ተደርጎ፣ የሰጧቸው አስተያየቶችም ተካተው የመጨረሻው ረቂቅ ተዘጋጅቷል፡፡  ነገር ግን የሥነ ምግባር ደንቡን በጥርጣሬ የሚመለከቱ ኤክስፖርተሮችም አሉ፡፡ እነዚህ ኤክስፖርተሮች እንደሚሉት፣ በሥነ ምግባር ደንቡ