Posts

ደኢህዴን ሀገራዊ ግቦችን ለማሳካት ያመራር ሚናውን ከምንግዜውም በላቀ ቁርጠኝነት ለመወጣት መዘጋጀቱን አስታወቀ

Image
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 2/2005 (ዋኢማ) -  የደቡብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ደኢህዴን) ማዕከላዊ ኮሚቴ ሀገራዊ ግቦችን ለማሳካት ያመራር ሚናውን ከምንግዜውም በላቀ ቁርጠኝነት ለመወጣት መዘጋጀቱን አስታወቀ፡፡ ማዕከላዊ ኮሚቴው የእድገትና የትራንስፎርሜሸን እቅዱን የሁለተኛ አመት አፈጻጸም ግምገማውን ለታላቁ መሪ አቶ መለስ ዜናዊ የህሊና ጸሎት በማድረግ ጀምሯል፡፡ የደኢህዴን ማዕካላዊ ኮሚቴ በመደበኛ ስብሰባው በታላቁ መሪ የተቀየሱት፣ መላውን ህዝብ ተሳታፊና ተጠቃሚ እያደረጉ የሚገኙት ፖሊሲዎችና ስትራቴጂዎችን በላቀ ቁርጠኝነት በሚፈፀሙበት ሁኔታ ላይ በዝርዝር ተወያይቷል፡፡  በዚህም የጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊን ህልፈት ተከትሎ ህዝቡ ከጫፍ ጫፍ ያሳየውን ቁጭት በተደራጀ መንገድ ለመምራት፣ በየደረጃው የሚገኙ ድርጅታዊ፣ መንግስታዊና ህዝባዊ መዋቅሮችን ተቋማዊ በማድረግ የህዳሴውን ጉዞ ለማፋጠን የሚያስችሉ የአፈጻጻም ስልቶችን በመቀየስ ተግባራዊ እንዲሆኑ ወስኗል፡፡ በገጠር ስራዎች በተለይም በአካባቢ ልማት አና ጥበቃ የተሻለ አፈጻጸም መመዝገቡን የገመገመው ማዕከላዊ ኮሚቴው በበልግ እና በመኸር የግል ማሳ ስራዎች ረገድም በአንዳንድ አካባቢዎች መልካም ውጤት መመዘግቡን አረጋግጧል፡፡ ምርታማነትን ለማሳደግ የቴክኖሎጂ ግብአቶችን በመጠቀም ረገድ የነበሩ ክፍተቶችንም ለይቷል፡፡ ኢሬቴድ እንደዘገበው ማዕከላዊ ኮሚቴው በከተሞች፣ በቤቶች ልማትና በመሰረተ ልማት የተሻሉ ተግባራት ቢከናወኑም በመልካም አስተዳደር ረገድ የሚስተዋሉ ጉደለቶችን ማረም እንደሚገባ ነው ያስገነዘበው፡፡ መስከረም 30/2005 የተጀመረው የማዕከላዊ ኮሚቴው መደበኛ ስብሰባ በ2005 በሁሉም መስኮች የነበሩ ጥንካሬዎችንና ጉድለቶችን በጥልቀት በመገምገም የ2005 እ

ህገ-መንግስቱ ያገሪቱ የበላይ ህግ ነው የተባለው ድንጋጌ ይከበር!!

Image
Sidama times የዜና መጽሔት የተገኘ ህገ - መንግስቱ ያገሪቱ የበላይ ህግ ነው የተባለው ድንጋጌ ይከበር !! ውድ አንባቢዮቻችን እንደ ምን ሰነበታችሁ ? በባለፈው ፁሑፋችን የሲዳማ ህዝብ ክልል የመሆን ጥያቄ በህገ - መንግስቱ እይታ ሲፈተሸ ምን ገፅታ እንዳለው ባጭሩ ለማስቃኘት መመኮራችን ይታወሳል፡፡ በዛሬው አጭር ፁሑፋችን የሲዳማ ህዝብ ክልል ባለማግኘቱ የተጎዳባችሁን ሁኔታዎች እንቃኛለን፡፡ መልካም መቆይታ በቀደመው ፁሑፋችን ለማንሳት እንደሞከርነው የሲዳማ ህዝብ ክልል የመሆን ጥያቄ በቅርብ ጊዜ የተጀመረ እንዳልሆነና ለዘመናት ይህንን ጥያቄ ህዝባች ሲያነሳ የቆየ፡ ነገር ግን ህጋዊ ምላሽ ተነፍጎን እንደኖረ አይተናል፡፡ አንባገነኑ የደርግ ስርዓት እንዲዳከምና በኃላም እንዲንኮታኮት ከፍተኛ የሆነ የትጥቅ ትግል በማድረግ ለሀገሪቱ ነፃነትና ለዲሞክራሲ ማደግ ከፍተኛ ሚና የተጫወት ህዝብ ነው የሲዳማ ህዝብ፡፡ የሀገሪቱ የፖለለቲካ ምህዳር ሲቀየርና የፌደራሊዝም ስርዓት እንደብቸኛ አማራጫ ተደርጎ ሲወሰድ የሀገራችን ለየት ብሎ የጎሳ ፌደራላዊ ስርዓት ሆኖ ተዋቅሯል፡፡ ይህ የፌደራል ስርዓት ለአብዛኞዎቹ ብ / ብ / ሕ በወቅቱ አንግቦት ለነበረው ጥያቄ ምላሽ ለመስጠት ታስቦ የተወሰደ እርምጃ ይመስላል፡፡ ይህ በጎሳ የመከፋፈል እርምጃ ከሀገሪቷ አንድነት እይታ ትክክለኛ ነው አይደለም የሚለውን አሁን አንመለከተውም፡፡ የብ / ብ / ሕ ጥያቄው ምላሽ ማግኘት አለበት ሲባልም የተለያየ እንድምታ ያለው ይሆናል፡፡ ግማሾቱ የመገንጠል ጥያቄ፣ ግማሾቹ እራስን በራስ የማስተዳደር ጥያቄ፣ ለሎቹ ደግሞ ለፖለቲካ መንበረ ስልጣን ወዘተ ጥያቄዎችን አንግበው የሚንቀሳቀሱ ነበሩ፡፡ የሲዳማም ህዝብም ያለውን የቆየ የትግል ታሪክና እምቅ አቅሙን

ደኢህዴን መደበኛ ስብሰባውን እያካሄደ ነው

Image
አዲስ አበባ (ኢዜአ)፡- የደቡብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ /ደኢህዴን/ ማዕከላዊ ኮሚቴ የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዘመንን የሁለተኛ ዓመት መደበኛ አፈጻጸምና የታላቁ መሪን የመለስ ዜናዊን ራዕይ ለማሳካት እየተከናወኑ ያሉ ተግባራትን በዝርዝር ገመገመ፡፡ ለታላቁ መሪ ጓድ መለስ ዜናዊ የህሊና ጸሎት በማድረግ ማዕከላዊ ኮሚቴው ትናንት በጀመረው መደበኛ ስብሰባ ታላቁ መሪ ባወጡት ፖሊሲዎችና ስትራቴጂዎች በሚፈጸምበት ዝርዝር ሁኔታ ላይ ተዘጋጅተው በቀረቡ ሰነዶች ላይ በመወያየት አቋም ወስዷል። ድርጅቱ በላከው መግለጫ እንዳብራራው፤ በየደረጃው የሚገኙትን ድርጅታዊ፣ መንግሥታዊና ህዝባዊ አመራሮችንና አደረጃጀቶችን ተቋማዊ በማድረግ የህዳሴውን ጉዞ ለማሳካት በቀረበ ሰነድ ላይ በመወያየት የአፈጻጸም ሰልቶች ተቀይሶ በፍጥነት ተግባራዊ እንዲሆን ውሳኔ አሳልፏል። በገጠር ሥራዎች ረገድ ባለፈው ዓመት በአካባቢ ልማት ጥበቃ የነበረው የህዝብ አደረጃጀት ተሳትፎ ከቀዳሚዎቹ ዓመታት የተሻለ አፈጻጸም የታየበት ሲሆን፤ ወደ በልግ መኸር የግል ማሳ ሥራዎች በመሸጋገር ረገድም በአንዳንድ አካባቢዎች መልካም ውጤቶች መመዝገባቸውን የማዕከላዊ ኮሚቴ አረጋግጧል። ምርትንና ምርታማነትን ለማሳደግ ሁሉንም የቴክኖሎጂ ግብዓቶች እጅ በእጅ በመግዛት ጥመርታውን ጠብቆ ጥቅም ላይ በማዋል ረገድ የነበሩ ክፍተቶችን በዝርዝር መመልከታቸውን መግለጫው ጠቁሟል። በከተሞች በሥራ ፈጠራ፣በቤቶች ልማት፣በማህበራዊና በመሰረተ ልማት ዝርጋታ የታየው ለውጥ የተሻለ ሲሆን፤ በየደረጃው የሚቀርቡ ጥያቄዎችን በአግባቡ ተገንዝቦ ፈጣን ምላሽ በመስጠት ረገድ የሚታዩ የመልካም አስተዳደር ጉድለቶችን በቀጣይ ሊታረሙ እንደሚገባ የማዕከላዊ ኮሚቴው አስገንዝቧል፡፡  የኮሚቴው መደበኛ ስብሰባ

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የ45ኛ ዳኞችን ሹመት አፀደቀ

Image
አዲስ አበባ፦ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ያቀረቡትን የ45 ዳኞች ሹመት አፀደቀ። የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ግርማ ወልደጊዮርጊስን ዓመታዊ የመክፈቻ ንግግር ሞሽን ላይ በሚቀጥለው ሳምንት ለመነጋገር ወሰነ። ምክር ቤቱ ትናንት ባካሄደው ሦስተኛ የሥራ ዘመን በአንደኛ መደበኛ ስብሰባው ሹመታቸውን ካፀደቀላቸው 45 ዳኞች መካከል አምስቱ ለፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት፣ ዘጠኙ ለከፍተኛ ፍርድ ቤት እንዲሁም 31ዱ ለመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በእጩነት የቀረቡ ናቸው። በጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ስለቀረቡት እጩ ዳኞች ለምክር ቤቱ በዝርዝር ያስረዱት የመንግሥት ረዳት ተጠሪ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ መለስ ጥላሁን፤ ዳኞቹ የሕግ ምሩቃን፣ በሙያው በቂ ልምድ ያላቸው፣ ለሕገ መንግሥቱ ታማኝ፣ በሥነ ምግባራቸው መልካም ስም ያተረፉና በዳኝነት ሙያ ለመስራት ፍላጎት ያላቸው መሆናቸውን ለምክር ቤቱ አስረድተዋል። እጩ ዳኞቹ የተመረጡበትን መስፈርት በተመለከተ አንድ የምክር ቤቱ አባል የእጩዎቹ ምርጫ የብሔር ስብጥርን በተለይም የታዳጊ ክልሎችን ግምት ውስጥ ያስገባ እንዳልሆነ አስተያየት ሰጥተዋል። ሌላኛው የምክር ቤቱ አባል ደግሞ የዳኞቹ ሹመት የተረሱ ብሔረሰቦችን ሲያካትት በታሪክ የመጀመሪያው እንደሆነ በመግለጽ ሹመታቸው ከፀደቀላቸው ዳኞች መካከል የአርጎባ ብሔረሰብ አባል በመካተታቸው የተሰማቸውን ደስታ ገልጸዋል። የተቃዋሚ ፓርቲ አባል የሆኑት አቶ ግርማ ሰይፉ በበኩላቸው፤ ከዚህ ቀደም በነበረው የዳኞች ሹመት ከሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ ተመራቂዎች ብቻ እንደነበር አስታውሰው፣ በአሁኑ ግን ከግል የትምህርት ተቋማት የተመረቁትን ጨምሮ ከተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች የተካተቱበት መሆናቸውን በማድነቅ ይህ ሊለመድ እንደሚገባ አስተያየት ሰ

የተባበሩት የሲዳማ ፓርቲዎች ለቅንጅት ነጻነት እና ለፍትህ በወቅታዊ ጉዳይ ላይ መግለጫ ሰጠ፤ ኣዲሱ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ኣቶ ኃይለማሪያም ደሳሌኝ የሲዳማን ህዝብ ክልል የመሆን ህገ መንግስታዊ መብት እንዲያከብሩ ጠየቀ

Image
ፓርቲው ለወራንቻ ኢንፎርሜሽን ኔትዎርክ በላከው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ እንዳመለከተው የኢትዮጵያ መንግስት የሲዳማን ህዝብ በክልል ደረጃ ራስን በራስ የማስተዳደ መብት እንዲያከብር ጠይቀዋል። የጋዜጣዊ መግለጫው ሙሉ ቃል እንደምከተለው ቀርቧል፦ The New Ethiopian Prime Minster ‘Hailemariam Desalegn’ Must Respect Sidama people’s Constitutional Rights to Regional Self Administration!! Press Release By United Sidama Parties for Freedom and Justice (USPFJ), October 11, 2012 The Sidama nation endured various forms and shapes of injustices imposed on them by the successive Ethiopian rulers including the current TPLF/EPRDF’s regime. The injustices the Sidama nation is exposed to involve an economic and political marginalization, socio-cultural subjugation and gross violations of their fundamental rights. Even though the Sidama nation owns one of the richest regions in the country, its people are subjected to a persistent government induced poverty that had chronologically deepened from time to time. Sidama’s development institutions are dismantled or made to