Posts

Sidama Worancha Information Network

Image
Sidama Revolutionary Song

Chinese company helps New Hawassa senior center

Image
“ZTE has invested over four million birr on social development projects in Ethiopia,” said Yang Rongxue, Representative of ZTE at a donation ceremony of food and clothing to Mary Joy Development Association on Friday October 5, 2012. The donation was provided from ZTE employees from China as well as Ethiopia. “ZTE has been operating in Ethiopia for 12 years now, as a company we have been participating actively in the society to fulfill our social responsibility,” Yang stated. The company that had its revenue grow by 29pct to USD 13.7 billion and overseas revenue increased by 30pct to USD 7.42 billion in 2011 stated that it is interested in giving more donations in the future. Working with less fortunate persons since 1995, Mary Joy also announced that it has started building a recreational center for older persons only. “In this country there are many places where young people can go to spend time, but there wasn’t a single place where older  people could go to. We wanted

ለምርጫው ስኬት የፍትህ አካላት ቅንጅታዊ ጥረት ተጠየቀ

Image
ሐዋሳ (ኢዜአ)፡- ዘንድሮ የሚካሄደው የአካባቢ ምርጫ ሰላማዊ፣ ነፃና ዲሞክራሲያዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ የፍትህ አካላትን ቅንጅታዊ ጥረት እንደሚሻ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ገለጸ፡፡ የቦርዱ ሰብሳቢ ፕሮፌሰር መርጋ በቃና በደቡብ ክልል ለሚገኙ የፍትህ አካላት ኃላፊዎችና ባለሙያዎች በተዘጋጀው የአቅም ግንባታ ስልጠና ላይ እንደተናገሩት የሀገሪቱ ምርጫ አፈጻጸም ዓለም አቀፍ መርሆዎችን በተከተለና የህዝቡን ተጠቃሚነት ባረጋገጠ መልኩ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተጠናከረ መጥቷል፡፡ ባለፉት ሁለት አስርት ዓመታት የሀገሪቱ ብሔር፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች በማንኛውም ሁኔታ ልዩነት ሳይደረግባቸው በቀጥታ በነፃነት በመረጧቸው ተወካዮቻቸው አማካይኝነት ራሳቸውን በራሳቸው የማስተዳደር ህገመንግስታዊ መብታቸውን መጠቀም ችለዋል ብለዋል፡፡ በአገሪቱ በምርጫው በኩል የታዩ መልካም ውጤቶችን የበለጠ ለማጠናከር መንግሥት ለነፃና ፍትሃዊ ምርጫ አፈጻጸም ዓለምአቀፍ መስፈርቶችን ያካተቱ አዋጆችን በማውጣትና ምርጫውን የሚያስፈጽሙ ገለልተኛ የምርጫ ቦርድ በማቋቋም በርካታ ለውጦች እንዲመዘገቡ ማድረጉንም ተናግረዋል፡፡ የፍትህ አካላት በተወዳዳሪ የፖለቲካ ፓርቲዎችና በግል ዕጩዎች መካከል ለሚከሰቱ አለመግባባቶች መፍትሄ በመስጠት እንዲሁም ለነፃ፣ ፍትሃዊ፣ ሠላማዊና ዴሞክራሲያዊ ምርጫ አፈፃፀም ሥርዓት መስፈን ገንቢ አስተዋጽኦ በማበርከት ለሀገሪቱ ዴሞክራሲያዊ ስርዓት መጎልበት የበኩላቸውን እንዲወጡ አሳስበዋል፡፡ በሀገሪቱ በአሁኑ ወቅት ምርጫው ሠላማዊና ዲሞክራሲያዊ በሆነ መልኩ ለማስፈፀም የተዘጋጁ የህግ ማዕቀፎችን መሰረት በማድረግ በቦርዱ ዕውቅና ያገኙ 75 የፖለቲካ ፓረቲዎች እንዳሉ የገለጹት ሰብሳቢው እነዚህ የፖለቲካ ፓርቲዎች ለመልካም አስተዳደር መስፈንና ለዴሞክራሲ ሥርዓት መ

በሀዋሳ ከተማ ህዝበ ሙስሊሙ በቀበሌ ደረጃ ያካሄደው ምርጫ ተጠናቀቀ

Image
አዋሳ መስከረም 28/2005 በሀዋሳ ከተማ ሙስሊሙ ህብረተሰብ ትናንት በቀበሌ ደረጃ የሚመሩትን ተወካዮች ነጻና ዴሞክራሲያዊ በሆነ መንገድ መምረጡን የከተማው እስልምና ጉዳዮች ምርጫ አስተባበሪና መራጮች ገለጹ፡፡ የከተማው እስልምና ጉዳዮች የምርጫ አስተባባሪ ዶክተር ሁሴን መሐመድ ዛሬ ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እንደገጹት በከተማው 19 ምርጫ ጣቢያዎች በተካሄደው ምርጫ ከ3 ሺህ የሚበልጡ ሙስሊሞች ድምጽ ሰጥተዋል፡፡ በህዝበ ሙስሊሙ ቀጥተኛ ተሳትፎና ባለቤትነት በተካሄደው ምርጫ በእያንዳንዱ ምርጫ ጣቢያ ከተጠቆሙት 25 ዕጩዎች መካከል 20ዎቹ በድምጽ ብልጫ ተመርጠው ቃለ መሃላ መፈጸማቸውን አስታውቀዋል፡፡ የተመረጡት ተወካዮች በህብረተሰቡ ዘንድ በሚገባ የሚታወቁ ፣በሀይማኖት ስነምግባራቸው የተመሰገኑና በህዝብ ዘንድ ተቀባይነት ያላቸው መሆናቸውን አመልክተው የምርጫው ሂደት ያለምንም ችግር መጠናቀቁን አስታውቀዋል፡፡ ከመራጮችም መካከል አንዳንዶቹ በሰጡት አስተያየት የሚበጃቸውን መሪዎች በራሳቸው ቀጥተኛ ተሳትፎ መምረጥ ሲችሉ የአሁኑ በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ በመሆኑ ከፍተኛ ደስታ እንደተሰማቸው ጠቁመው ምርጫው ነጻ፣ ሰላማዊና ዴሞክራሲያዊ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ http://www.ena.gov.et/Story.aspx?ID=2722&K=1

ፕሬዝዳንት ግርማ ሁለቱን ምክር ቤቶች በንግግር ከፈቱ

Image
አዲስ አበባ፣ መስከረም 28፣ 2005 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ግርማ ወልደጊዮርጊስ የህዝብ ተወካዮችና  እና የፌዴሬሽን ምክር ቤቶችን የጋራ መደበኛ ስብሰባን በንግግር ከፍተዋል። የኢፌዲሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤትና የፌዴሬሽን ምክር ቤቶች ሶስተኛ ዓመት የስራ ዘመናቸውን ዛሬ ጀምረዋል። በምክር ቤቶቹ የጋራ የመክፈቻ ስነ ስርዓት ላይ ፕሬዝዳንት ግርማ  ባቀረቡት የመክፈቻ የ2005 በጀት ዓመት የመንግስት ትኩረት የሰጠባቸውን  ጉዳዮች አንስተዋል ። ፕሬዝዳንት ግርማ በንግግራቸው በክቡር አቶ መለስ ዜናዊ ቀያሽነት ባለፉት ሁለት ዓመታት ተግባራዊ መደረግ የጀመረው የእድገትና የትራንስፎርሜሽን እቅድ አበረታች ውጤቶች እየተመዘገበበት ይገኛል ብለዋል። ባለፉት ተከታታይ ዓመታት ሃገሪቱ እያስመዘገበች ያለው ባለሁለት አሃዝ የኢኮኖሚ እድገትም በዘንድሮው ዓመት እንደሚደገም የሚያረጋግጡ ተግባራት በመንግስት እየተናወኑ እንደሚገኙም ነው የጠቆሙት። ግብርና አሁንም በከፍተኛ ደረጃ እድገት እያስመዘገበ የሚገኝ ሲሆን ይህንን ለማሰቀጠል የሚያግዙ ሰፋፊ የአፈርና ውሃ ጥበቃ ስራዎች በክረምቱ ወቅት በመላ ሃገሪቱ ተከናውኗል ብለዋል።           ከማዳበሪያና ምርጥ ዘር አቅርቦት አንስቶ የአርሶ አደሩ የዘመናዊ ቴክኖሎጂ ተጠቃሚነት እያደገ መምጣት ከዓምናው የተሻለ የምርት ጭማሪ እንደሚኖር የሚጠበቅ ነው ብለዋል ፕሬዝዳንቱ። ስራ አጥነትን ለመዋጋት በተሰሩ ስራዎችም ባለፈው ዓመት ለ1 ነጥብ 1 ሚሊየን ዜጎች ቋሚና ጊዜያዊ የስራ እድል መፍጠር መቻሉንም ተናግረዋል። በከተሞች የሚስተዋለውን የመኖሪያ ቤት ችግር ለመፍታት እየተከናወነ ያለው የጋራ መኖሪያ ቤቶች ግንባታም በ100 ሺዎች የሚቆጠሩ መካከለኛና ዝቅተኛ ገቢ ያላቸ