Posts

Sidamu sumuda

Image
New

የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ዘመናዊ የመስኖ አጠቃቀም ዘዴዎችን ለአርሶ አደሮች እያስተዋወቀ ነው

Image
ሀዋሳ፤ ህዳር 30/2004/ዋኢማ/  - ዘመናዊ የመስኖ አጠቃቀም ዘዴዎችን ለአርሶ አደሩ ለማስተዋወቅ የሚያስችለውን ፕሮጀክት ተግባራዊ ማድረግ መጀመሩን የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ አስታወቀ። የዩኒቨርሲቲው የመስኖ ልማትና ውሃ አጠቃቀም ምህንድስና ትምህርት ክፍል ኃላፊ አቶ ወሰኑ ለማ ለዋልታ ኢንፎርሜሽን ማዕከል እንደገለፁት፤ ፕሮጀክቱ ካለፈው ጥቅምት ጀምሮ በደቡብ ክልል በተመረጡ ዝናብ አጠር አካባቢዎች ተግባራዊ እየሆነ ይገኛል። ዘመናዊ የመስኖ አጠቃቀም ዘዴ ፕሮጀክቱን ለአርሶ አደሩ የማስተዋወቅ ሥራ የሚሰራው ከኢትዮጵያ የውሃ ሀብት አጠቃቀም ኢንስቲትዩት ጋር በመተባበር መሆኑ ተገልጿል። ፕሮጀክቱ አርሶ አደሩ የጎርፍ ውሃን በማሰባሰብና የከርሰ ምድር ውሃን በቀላሉ በማውጣት ለእርሻ ሥራዎች ሊያውል የሚችልባቸውን ዘዴዎች እንደሚያስተዋውቅ የትምህርት ክፍል ኃላፊው አመልክተዋል። ፕሮጀክቱ እየተካሄደ የሚገኘው ዩኒቨርሲቲው በክልሉ የተለያዩ አካባቢዎች በሥሩ ባቋቋማቸው ስድስት የቴክኖሎጂ መንደሮች አማካኝነት መሆኑን የገለፁት ኃላፊው ይህም አርሶ አደሩ በፕሮጀክቱ አማካኝነት በንድፈ ሀሳብና በተግባር የሚሰጡ ሥልጠናዎች በቅርበት ለመከታተል እንደሚያስችለው ተናግረዋል።  ለሦስት ዓመት የሚቆየው ይኼው ፕሮጀክት በ14 የገበሬዎች የሕብረት ሥራ ማህበራት ሥር የተደራጁ ከ8ሺ በላይ አባወራ አርሶ አደሮችን የመስኖ ተጠቃሚ እንደሚያደርግ የትምህርት ክፍሉ ኃላፊ አስረድተዋል።  ፕሮጀክቱ በዝናብ አጠር አካባቢዎች የሚገኙ አርሶ አደሮች የመስኖ አማራጮችን ተጠቅመው፤ በዓመት ከሁለት እስከ ሦስት ጊዜ በማምረት በተደጋጋሚ የሚያጋጥማቸው የምግብ እጥረት ለመቅረፍ እንደሚያስችላቸው ኃላፊው አመልክተዋል። ዩኒቨርሲቲው ከመደበኛ የመማር ማስተማር ሥራዎቹ በተጨማሪ ከተለያዩ ተቋማት ጋር በመተባበር ችግ

ንግድ ሚኒስቴር የአራት ወራት የቡና ኤክስፖርት አሳስቦኛል አለ

-    ቡና ላኪዎች ይሻሻልልን ያሉትን መመርያ ሳይቀበለው ቀረ ‹‹በብትን ብትልኩ አንቀበልም ብለውናል›› ቡና ላኪዎች ‹‹በብትን የሚላከው በጃፓን ገበያ የደረሰብንን ካየን በኋላ ነው›› አቶ ያዕቆብ ያላ  ንግድ ሚኒስቴር ባለፉት አራት ወራት የቡና ኤክስፖርት አፈጻጸምን በተመለከተ ከላኪዎች ጋር ባካሄደው ስብሰባ፣ ሊላክ ከሚገባው ቡና በታች በመላኩ እንዳሳሰበው አስታወቀ፡፡ ሚኒስትር ዴኤታው አቶ ያዕቆብ ያላ ላኪዎችን ጠርተው እንመካከር ባሉበት ህዳር 28 ቀን 2004 ዓ.ም. ስብሰባ ላይ እንዳስታወቁት፣ በአራት ወራት ውስጥ ሊላክ የሚገባው ቡና ባለመላኩ ሰባት ወራት ብቻ ለቀረው የበጀት ዓመቱ ኤክስፖርት አፈጻጸም አሳሳቢ ነው፡፡ ‹‹የቀረን ሰባት ወር ነው፡፡ በዚህ ዓመት ከቡና 1.1 ቢሊዮን ዶላር እየተጠበቀ ነው፡፡ ይህ የአገሪቱ ዕቅድ ነው፡፡ ችግሮቹ በዚህ ሁኔታ ከቀጠሉ ይህንን ሁኔታ ይጐዳሉ፤›› በማለት አቶ ያዕቆብ አሳስበዋል፡፡ ለዓለም ገበያ መቅረብ ይገባው የነበረው የቡና መጠን የቀነሰው በተለያዩ ችግሮች መሆኑን የገለጹት ነጋዴዎቹ፣ በተለይ ቡና በብትን እንዲላክ በወጣው መመርያ መሠረት ለመላክ ባለመቻላቸው መሆኑን አስታውቀዋል፡፡ ንግድ ሚኒስቴር ላለፉት አራት ወራት ለውጭ ገበያ ይላካል ያለው የቡና መጠን ከ66,400 ቶን በላይ ነበር፡፡ ነገር ግን የተላከው ቡና ከ44,029 ቶን በላይ ባለመሆኑ ከ22,371 ቶን በላይ ቡና ሳይላክ ቀርቷል፡፡ በጥቅምት ወር መላክ የነበረበት 75 ሺሕ ቶን ቢሆንም፣ ሊሰበሰብ የተቻለው 13 ሺሕ ቶን ነበር፡፡ ያም ሆኖ ግን ወደ ውጭ የተላከው አራት ሺሕ ቶን ብቻ ይሆናል፡፡ ቡናው እንደታሰበው ሊላክ ያልተቻለው ደግሞ ቡናው በውል ከተሸጠ በኋላ በወቅቱ ሊላክ ባለመቻሉ (የተሸጡ ኮንትራቶች ስላልተፈጸሙ)፣ በምርት ገበያና በኒው

Hawassa lost to Harer 2-0

Image
Hawassa, Ethiopia  – Harar Brewery scored the biggest upset of the week with a 2-0 victory over Hawassa City in Week 3 of the Ethiopia Premier League here today. Mugher Cement shared a point (0-0) on the road with newly promoted Arba Minch Kenema; EEPCO drew 2-2 with Commercial Bank of Ethiopia (CBE) and Defence Force was held to a 1-1 tie with the visiting Sidama Coffee in Addis Ababa. So after today’s matches, Harar Brewery, Mugher Cement & EEPCO share the top spot with 5 points each, but with the Harari side having a better goal difference (+2 goals). The league will continue on Tuesday, December 13 with the following matches: Bishoftu: Air Force vs Dedebit FC Dire Dawa: Dire Dawa City vs St. George FC Addis Ababa: Ethiopian Coffee vs Adama City FC

Ethiopian Washed Coffee Prices Fall as Much as 6.9%

Prices for unwashed arabica coffee from  Ethiopia  fell as much as to 6.9 percent last week on the Ethiopia Commodity Exchange. Volumes of both washed and unwashed coffee traded rose to 2,529 metric tons in the week ending Dec. 9 from 2,295 tons a week earlier, according to e-mailed statement from the Addis Ababa-based exchange on Dec. 9. The following are prices for the most heavily traded types of arabica in dollars per pound on the last day they were exchanged in the week. Week-on-week data may reflect changes in exchange rates. Volumes are in metric tons and the percentage change is measured from the previous week’s closing price. Unwashed Region Type Grade Volume Price % Change Forest A 9 232.54 $1.9058 -0.14% Forest A UG 80.78 $1.9211 3.59% Forest B 7 45.9 $1.998 n/a Jimma A 8 30.02 $1.9672 1.45% Jimma B 6 45.9 $1.9