የስኮትላንዱን Kilt/ ክሊትን እና የሲዳማውን ጎንፋ ምን ያመሳስላቸዋል?


ታላቋን ብርቲን UKን ከፈጠሩት አራት አገራት መካከል አንዷ የሆነችው ስኮትላንድ፤ ከሲዳማ ጋር የሚያመሳስላት አንድ ነገር አለ። ይሄውም ወንዶቻቸው የምለብሱት ባህላዊ ልብስ ነው። ልብሱ ከሲዳማዎቹ ጎንፋ ጋር መመሰሰሉ ብቻ ሳይሆን፤ ታርካዊ እና ባህላዊ ፋይዳው አንድ ነው።

Kilt ክሊት በስኮትላንድ ሴሊቲክ ህዝብ ዘንድ በባህላዊ ልብስነት በወንዶች የሚለበሰ ሲሆን፤ እስከ ጉልበት የሚረዥም የሴቶቹን ቀምስ የሚመስል አልባስ ነው። አመጣጡን ተመለከተ እንደ አእሮፓውያን ዘመን አቆጣጠር ከ16ተኛ ክፍለ ዘመን ጀምሮ፤ በተለይ በስኮቲሽ ሃይላንድ/ Scottish Higlands ይኖሩ በነበሩ የሴልቲክ አባል የሆነ ወንድ አዋቂዎች እና ወጣት ወንዶች ለብርድ መከላከያ እንደ ጋቢ ይለበስ የነበረ ሲሆን፤ ከ18ተኛው ክፍለዘመን ጀምሮ ግን ከወገብ በታች እስከ ጉልበት ድረሰ በማስረዘም መልበስ መጀመሩ ይነገራል።
 
ከ19ተኛው ክፍለዘመን ጀምሮ ክሊት በከፍታማ የአገሩቱ አከባቢዎች ብቻ ሳይሆን፤ በአጠቃላይ እንደየአገሪቱ ባህላዊ ልብስ በአብዘኛው በተለይ በወንዶች በተለያዩ ባህላዊ ክንውኖች እና ዝግጅቶች ላይ መዘወተር መጀመሩ ይነገራል።

ክሊት እንደ ጎንፋ ሁሉ ከተለያዩ ማይቴሪያሎች የሚሰራ ቢሆንም፤ በአብዘኛው ግን ከጥጥ ግብአት እንደሚመረት ተገልጿል።
በመላው አለም ታዋቂነትን ያተረፈው ክሊት፤ በስኮትላንዶች ዘንድ ከአርበኝነትና ከብሔራዊ ማንነት መገለጫነት አልፈው፤ ጥልቅ የሆነ ባህላዊ እና ታርካዊ ፋይዳ እንደለው ይነገራል። በዚህም ስኮትላንዶች በዚህ ባህላዊ ልብስ ከፍተኛ ኩራት እንደምሰማቸው ታውቋል።
በርግጥ እኛም በጎንፋችን ከፍተኛ ኩራት እንደምሰማን ይገባኛል። ለማንኛውም የእኛውን ጎንፋ በአለም አቀፍ ደረጃ ለማስተዋወቅ ከፊቼ በላይ ምን አማራጭ አለ?
 
በነገራችን ላይ የድሮው ባለ ጥቁር እና ነጭ ቀለም ጎንፋ የት ገባ?

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር