በናይጀሪያ በተካሔደው የብየዳ ክህሎት ውድድር ከሀዋሳ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ መምህርት የሆነችው ወለላ ሰኢድ ኢትዮጵያን ወክላ ልዩ ተሸላሚ ሆነች


ወለላ ሰዒድ ተሸላሚ የሆነችው ናይጀሪያ በተሰናዳው የአፍሪካ ብየዳ ፌደሬሽን ጉባኤ እና የጥናትና ምርምር ሴሚናር ላይ በኢፌዲሪ ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት ወክለው ከተሳተፉ ባለሙያዎች መካከል አንዷ ናት።
በዚህ እየተካሄደ በሚገኘው የብየዳ ክህሎት ውድድር በብየዳ ልህቀት ማዕከል ስልጠና ዓለምአቀፍ ሰርቲፊኬት ባለቤት የሆነችው እና በአሁኑ ጊዜ በክረምት ወራት ቴክኖሎጂ ማበልጸጊያ ፕሮግራም (summer camp) ተሳታፊ የሆነችው ወለላ ሰኢድ ልዩ ተሸላሚ ሆናለች።
በዚህ አህጉር አቀፍ የብየዳ ክህሎት ውድድር አለም አቀፍ የደረጃ 6 የብየዳ ሰርተፊኬት ባለቤት የሆኑት ስንታየሁ አብና አግርሶ ሀሪሶ ከሀዋሳ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ኢትዮጵያን ወክለው ጠንካራ ተፎካካሪ ሆነው ታይተዋል።
ኢትዮጵያ በኢንስቲትዩታችን እየተመራች የአፍሪካ ብየዳ ፌደሬሽን መስራች አገር መሆኗ ይታወቃል።
ምንጭ:- 

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር