ለመሆኑ ሲዳማ የኩሽና ሴም ውህድ ውጤት ነውን?

 ክፍል አንድ

ይህንን ጽሁፍ ለመጻፍ ምክኒያት የሆነኝን አጋጣሚ ልጥቀስ እና ወደ ጽሁፉ በቀጥታ አመራለሁኝ። ነገሩ እንዲህ ነው፤ ሰሞኑን በስራ ጉዳይ ከጀርመኑ የጎቲንጌን ዩኒቨርስቲ በነበርኩበት ወቅት፤ ከአጠገበ ተቀምጦ የነበረ አንድ ጀርመናዊ ኢትኖሎጂስት ethnologist ከኢትዮጵያ መምጣተን በመረዳቱ አንዳንድ ብሄር ነክ ጥያቄዎችን አቅርቦልኝ ነበር። በዚሁ ብሔር ነክ ውይይታችን፤ የእኔ ብሔር የትኛው እንደሆነ እና የት እንደሚገኝ ጠየቀኝ። እኔም ከሲዳማ ብሔር መሆነን ገልጨ፣ የሚገኘውም በደቡባዊ የአገሪቱ ክፍል መሆኑ ነገርኩት። እሱም ገና ሲዳማ የሚለውን ስም ከመስማቱ፤ ስለ ሲዳማ በ GÕttinger Studien zur Ethnologie በርካታ ጽሁፎች እንዳሉ እና እነዚህ ጽሁፎች የሲዳማ ህዝቦች ብያንስ የሚታወቅ ከአምስት መቶ አመታት በላይ የሚሆን ታርክ እንዳለው፣ የህዝቡም አሰፋፍርም ከምእራብ ኢትዮጵያ ጊቤ ሽለቆማ አከባቢ አንስተው እስከ ሐረር ጨርጨር ስንሰለታማ ተራሮች ድረስ ሰለ መሆኑ አወሳልኝ። እናም በዚህ ስፊ ግዛት፤ በሲዳማነታቸው የሚጠቀሱ ከ30 በላይ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦች እና ህዝቦች እንደነበሩ ዘረዘረልኝ። እናም ይህ አጋጣሚ ሁሌም በአእምሮዬ የሚመላለሰውን አንድ ወሳኝ ጥያቄ እራሴን እንዲጠይቅ አደረገኝ ... ።

ከበርካታ አመታት በፊት ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የመጀመሪያ አመት ተማሪ በነበርኩት ወቅት፤ እንደ የመጀመሪያ አመት ማህበራዊ ሳይንስ / የ6 ኪሎ ካምፓስ ተማሪ፤ የኢትዮጵያን ታርክ የሚዳስስ ኮርስ፤ A History of Modern Ethiopia,1855-1974 በፕሮፌሰር Bahru Zewde መውሰድ ነበርብኝ፤ እናም በዚህ የኢትዮጵያ ታርክ ስለሲዳማ ህዝብ ታርክ የተጻፈው ከአንድ ገጽ በላይ አለመሆኑ ብቻ ሳይሆን፤ ስለ ዘመኑ፣ ስለ አሁኑ የሲዳማ ህዝብ ይሁን ወይስ ከዘመናት በፊት ስለነበረው የሲዳማ ኪንግዴም/ Sidama Kingdom ታርክ ስለመሆኑ በውል በማይታወቅ መልኩ የተጻፌው ታርክ፤ በወቅቱ ግራ አጋብቶኝ ነበር። በርግጥ ከእዛን በኋላ በትምህርት ዝግጅትም ሆነ በሙያ፣ ከታርክ ጋር የሚቀራረብ ዝግጅት ስላልነበረኝ ለበርካታ አመታት ምንም የረባ የምርምር ስራ ሳልሰራ ቆይቻለሁኝ።

ሆኖም የዚህ የጀርመኑ ተመራማሪ ሲዳማን በተመለከተ ያነሳቸው ቁም ነገሮች፤ ለዘመናት በውስጤ ለሚመላለሱ እና ምላሽ ላላገኘሃቸው በርካታ ሲዳማ ነክ ጥያቄዎች ምላሽ ለማግኘት፣ ትንሽ ጊዜ ቢጤ እንዲፈልግ እና አንዳንድ በፈረንሳይኛ፣ እንግሊዥኛ፣ጀርመንኛ እና በጣሊያኝኛ የተጻፉ እና ከ200 አመታት በላይ እድሜ ያስቆጠሩ መዛግብትን አንዳገላብጥ አድርጎኛል። እናም መዛግብቱን አገላብጬ ያገኘሁትን መረጃ ለእራሴ ብቻ ከሚሆን፤ መሰል ጥያቄ ለሚያነሱ ከሌሎች ሲዳማውያን ጋር ለመጋራት እና እነዚሁ ሲዳማውያን በጉዳዩ ላይ ሰፋ ያለ ምርምር እንዲያደርጉ ለማበረታታት ያህል ይህንን ጽሁፍ ለመጻፍ ወድጃለሁ።

ማሳሰቢያ:- ይህንን ጽሁፍ ለጠቅላላ እውቀታችሁ እንጂ ለፖለቲካችሁ አታውሉት!!

ለመሆኑ ሲዳማ ማነው?

ይህ ጥያቄ በተለይ ሲዳማ የሚለውን ስያሜ ለበርካታ ኩሽ ቋንቋ ተናጋሪ ለሆነ ብሔር፣ ብሔረሰቦች እና ህዝቦች መጠሪያነት ይውል እንደነበር በተለያዩ የታርክ መዛግብት ላይ ለተመለከትን በርካታ ሰዎች በአእምራችን ውስጥ የዛሬው ሲዳማ እንዴት ብለው ነው፤ ይህንን ሲያሜ ልያገኝ የቻለው በምል በአእምራችን ውስጥ የሚመላለስ ጥያቄ ያለ ይመሰለኛል።

ስለ ሲዳማ ህዝብ ማንነትን በተመለከተ፣ በተለይ የዛሬው የሲዳማ ህዝብ “ሲዳማ” የሚለውን ስም እንዴት ልወርስ እንደቻለ የተለያዩ መላምቶች በተለያዩ የታርክ ጸሃፊት ቀርበዋል። እኔ ደግሞ እነዚሁ የውጭ አገር ጸሃፍት ባለፉት 200 አመታት የጻፏቸውን እና ሲዳማን የተመለከቱ ጽሁፎችን አገላብጨ እንደምከተለው አቅርብያለሁኝ።

በመጀመሪያ እስቲ Ethiopia through Russian eyes, Country in Transition 1896-1898 በተባለው እና በAlexander Bulatovich ተጽፎ በRichard Seltzer በተተረጎመው መጽሃፍ ውስጥ፤ ሲዳማን በተመለከተ የተቀመጠውን መረጃ እንመልከት[1]

አሌክሳንዴር በመጻፋቸው ውስጥ ሰለ ሲዳማ ሲጠቅሱ የሚከተለውን አስቀምጠዋል። እሳቸው “ሲዳማ” ብለው የጠሩቸው ህዝቦች ከሞላ ጎደል በአቢሲኒያ እና በኦሮሞ የተከበቡ ሲሆኑ፤ ከእነዚህ ህዝቦች መካከል ካፋ፣ሞካ፣ኩሎ፣ሲዳማ፣አማሮ እና ጉራጌን ይገኙባቸዋል። ይህ ህዝብ እስከ 16ተኛው ክፍለ ዘመን የኦሮሞ መስፋፋት ድረስ፤ ልክ እንደ ሰሜኑ የአቢሲኒያ አካባቢ ሁሉ የተረጋጋ ኑሮ ይመራ የነበረ ህዝብ መሆኑ ይጠቀሳል። ይሁንና የኦሮሞን መስፋፋት ተከትሎ ብሎም፤ በግራኝ አህመድ ወረራ የተነሳ በነበረው ጦርነት በእነዚህ ከላይ በተጠቀሱ አከባቢዎች ይኖሩ የነበሩ የሲዳማ ህዝቦች ወደ ተለያዩ አከባቢዎች መስደዳቸው የሚነገር ሲሆን፤ ኦሮሞ በሚስፋፋበት ወቅት እግሬ መንገዱን ያገኛቸው የነበሩትን እንዚህን ህዝቦች በጅምላ “ሲዳማ” በሚል ጥቅል ስም ይጠራቸው እንደነበረ ተጽፏል[2]

ይህንን ኣባባል የሚያጠናክሩ ሌሎችም ምንጮች ያሉ ሲሆን፤ ለአብነት ያህል በኡልሪቺ ብራውካምፔር በተባሉ ጀርመናዊ በተጻፈው Islamic History and Culture in Souther Ethiopa: Colleted Essay በገጽ 85 ላይ ኦሮሞ ሌሎች ኦሮሞ ያልሆኑትን እንደ ሶማሊ እና ሐረርን ጨምሮ በሲዳማነት እንደሚጠራቸው ገልጸዋል[3]

በ1942 በታተመው አንድ የጀርመን አገር የምርምር መጽሔት ውስጥ ሰለሲዳማ ህዝብ Sidama-Völker in Abessinien” በሚል ርእስ ስር በታተመው ጽሁፍ፤ ደግሞ በሲዳማነት ከ30 በላይ ብሔር፣ ብሔረሰቦች እና ህዝቦችን የጠቀስ ሲሆን፤ የህዝቡንም መኖሪያ አከባቢ ከታች በካርታው ላይ እንደሚታየው በምእራብ ኢትዮጵያ አስቀምጦት ይታያል።

ጠቅለል ባለ መልኩ የዛሬው የሲዳማ ህዝብ ለበርካታ ህዝቦች መጠረያ የነበረውን ስም እንዴት ልወርስ እንደቻለ በኦልትሪቺ ብራውኬምፔር እንደሚከተለው ያብራራል።

የታርክ መዛግብት እንደሚያመለክቱት በ13ኛው ክፍለ ዘመን በህንድ ውቃኖስ እና በኦሞ ወንዝ ሸለቆ መካከል ባለው አከባቢ ይኖሩ ከነበሩት የኩሽ እና የሴም ቋናቋ ተናጋሪ ከሆኑ ህዝቦች መካከል አንዱ ሲዳማ ሲሆን፤ እንደበርካታ ጸሃፊያን አገላለጽ ሲዳማ አመጣጡ ከሰሜን አፍሪካ ነው። ከዚህም በተጨማሪ ምናልባትም ይህ በሲዳማነት ይታወቅ የነበረው የኩሽ ቋንቋ ተናጋሪ ህዝብ ግዛት ወደ ሰሜን ኢትዮጵያ የተሰፋፋና በሰሜን በኩል እስከ ቤግምድር እና ወሎ የደረሰ እንደነበር ይነገራል። ይህም አገውን ለመሳሰሉ ኩሽ ቋናቋ ተናጋሪ ህዝቦች በሰሜን ኢትዮጵያ መኖር እንደምክኒያት ይነሳል። ከዚም በተጨማሪ በርካታ የቋንቋ ልቃን እንደሚስማሙት ከሆነ፤ የሲዳማ ህዝቦች ወደ ሰሜን እና ምስራቅ መስፋፋት፤ የኩሽ ቋንቋ በሌሎች እንደ ሐረሪ እና ጉራጊኛ በመሳሰሉ ሴምቲክ ቋንቋዎች ላይ ከፍተኛ ተጽእኖ ለማሳደር አስችሎታል።

ወጣም ወረደም ስለ ሲዳማ ብሔር ማንነት በተመለከተ ያሉት መረጃዎች በአፌ ታርክ ላይ የተመሰረቱ ከመሆናቸው የተነሳ በእርግጠኝነት መናገር ባይቻልም፤ እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ ሲዳማ የሚለው መጠረያ፤ በባህል፣ቋንቋ፣ እና ታርክ አንድነት የሌላቸው ነገር ግን በደቡብ ኢትዮጵያ ነዋሪ ለሆኑት እና የኩሽ ቋንቋ ተናጋሪ ለሆኑ ህዝቦች በሙሉ እንደመጠረያነት አገልግሏል።

ብራውኬምፔር ደግም እንዳረጋገጠው፤ሲዳማ የሚለውን ይህንን ስያሜ ለዚህ ሁሉ ህዝቦች መጠሪያነት ቀድሞ መገልገልን የጀመረው የኦሮሞ ህዝብ ነው። ይህ አይነቱ ለዘመናት የቆየ የሲዳማ ሲያሜ አጠቃቀም አሁኑ ካለው የሲዳማ ብሔር ሲያሜ ጋር እንደት እንደምገናኝ በግልጽ የተቀመጠ ነገር ባይኖርም፤ በተለያዩ ጊዚያት በደቡብ ኢትዮጵያ እና በባሌ ኦሮሚያ አከባቢዎች ጥናት ያደረጉት የታርክ ተመራማሪዎች፣ ካደረጓቸው የቃል ምልልሶች ተንሰተው እንደሚያብራሩት ከሆነ፤ የዛሬው ሲዳማ ወደ ዛሬዋ የሲዳማ አከባቢ ከመምጣቱ በፊት በሲዳማነት እንደማይታወቅ እና ሁለቱም የሲዳማ አባቶች ወደ አሁኗ የሲዳማ ምድር ከደረሱ በኋላ በወቅቱ በአከባቢው ይኖር ከነበረው እና የኩሽ ቋንቋ ተናጋሪ ህዝብ ማንነት እንደወረሱ እና እንደሌሎች ህዝቦች በኦሮሞ በሲዳማነት እንደሚጠሩ ህዝቦች ሁሉ ይህንን ስም ልወርስ ችሏል የሚል መላ ምት ተቀምጧል።

የእኔ የግሌ አመለካከትም ብሆን፤ የዛሬ የሲዳማ ህዝብ ሲዳማ” የሚለውን መጠሪያ ከላይ በተጠቀሰው መልኩ ስለማግኘቱ ምንም ጥርጥር የሌለኝ ሲሆን፤ በተለይ በተለያዩ ጊዚያት በደቡብ እና ምእራብ  ኢትዮጵያ ይኖሩ የነበሩትን ብሔር፣ ብሄረሰቦች እና ህዝቦችን በተመለከተ ጥናት ልያደርጉ ይመጡ የነበሩ እና በርካታ መረጃ በእነዚህ ህዝቦች ላይ የከተቡ የአውሮፓ ጻሃፊት በአብዘኛው ጥናታቸውን ይጀምሩ የነበሩት ከሰሜን ኢትዮጵያ ህዝቦች ቀጥለው ከመሆኑ ጋር ተያይዞ፤ ወደ እነዚህ አከባቢዎች በሚያደርጉት ጉዞ አሮሚያን ማቋረጥ የግድ ሰለነበር፤ ኦሮሞ እነዚህ ህዝቦች ለመጥራት ይጠቀም የነበረውን ሲያሜ ለመጠቀም ሳይገደዱ እንዳልቀሩ አስባለሁኝ።

ይቀጥላል



[1] ETHIOPIA THROUGH RUSSIAN EYES, COUNTRY IN TRANSITION 1896-1898.Second edition, revised and expanded, with the original photographs, 2020.Two books by Alexander Bulatovich, translated by Richard Seltzer. Translation copyright 1993 Richard Seltzer. Print edition published 2000 by The Red Sea Press, 11-D Princess Road, Lawrenceville, NJ 08648, PO Box 48, Asmara, Eritrea

 

[3] ttps://books.google.de/books?id=HGnyk8Pg9NgC&pg=PA187&lpg=PA187&dq=Banu+al+Hamuyyah&source=bl&ots=s_FqLakq0I&sig=ACfU3U1hD0-Ef_e-R3zUYDtVvxSUh21IkA&hl=am&sa=X&ved=2ahUKEwjqtqWCwZ3rAhUNwKQKHZCzAwsQ6AEwCnoECAcQAQ#v=onepage&q=Sidama&f=false

Comments

  1. Dhagge nabbawoommo. Kaayyu massinohe baychinni egenno hasanno mannira kaajjare abbootto. Albinkunnino addi addi handaarinni fultanni keeshshitto qeecha naadeemmo. Guuttono hooggono ka'ni darga qaange, "Daga'yati tini xe'u," yaa mannimmatena maassami.

    Dhaggenkewa higeemmo woyte, xaa geeshsha ragunni ofollitinoti baca dino. Borreessitannori daafurte borreessitannori giddonni guma xinqi'rantenni sao polotiku fiche tidhinannire xinqe borreessaminore jimilunni bushiishate widooganna mannu borreessate kakka"annohu dibashilaho.

    Konninni kainohunni, hattoo bude afidhino daga, hatoota wolaphote sharro sharrantino daga, hatoo kalaqamira teessino daga, hakkeeshshi kiiro afidhino daga, hakko buna, hakko waasa, hatte caatenna bacare afidhino daga ajjukkinni ajje heedhanni no.

    Konnira, ate borro konni gedensa mitore qaqqasanno mannira buusahona unte fushshite afisiisinkella. Baalu nabbawa hoogiro, mitu nabbawannona mannu ita giwino yite huluullantootina borreessinkela.

    "Sidaamu dhagge guuta polotiku danqonni, boosonna boosaallunni, afi'raammunninna wole hasattonni wolaphitinota borreessate malu maati?" Heddanni keeshshinke.
    Keeruni,
    Samuel Belayneh Qaa'me
    Hawaasa, Sidaama|🇪🇹

    ReplyDelete
  2. Dhagge coommittannote.hala'laduy borreesse dagate iillishste kaima ikkannore worrotto gari danchaho.gobbate giddo dhagge Sidaamuyita mittonna lame qoola sa'inokkita borreessansannino aleenni halaalaanchimateno diduushshitawotena afrootto kaayyonni assootto danchu loosikki danchaho.galateemmohe.

    ReplyDelete
  3. Naaxemohe rodii'ya naaxisisano dhagete gola hadhdhe daato yoomonte gedeni hadhe daatona wodaniyi galaxeemohe.dhage goodgano sidaamantora jawa hanafootina anekiwe yoomo.

    ReplyDelete
  4. Angakki Qadhito! Gattinotano rahinke. Fakkana ilama nabbabbanno gede Fb xalliniro yitanno hedono nooe!

    ReplyDelete
  5. Loworeetinka loworeno ikkineemmo!! dhaggete fullahaano dhaggenke wolu dhagge ledo taashate olammenkella. baalunku goli golinkenni Sidaamanna gobbanke lossate murci'ne ka'no.

    ReplyDelete

Post a Comment

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር