ዋሊያዎቹ በመጪው ዕሁድ ለቻን ዋንጫ ማጣሪያ ከሱዳን ጋር በሀዋሳ ይጫወታሉ

Image result for Hawassa Stadiumየኢትዮጵያ ብሔራዊ እግር ኳስ ቡድን ዋሊያዎቹ ለአፍሪካ አገራት ሻምፒዮና ቻን ለማለፍ የማጣሪያ ጨዋታውን ከሱዳን አቻው ጋር በመጪው እሁድ ያደርጋል።
2018 በኬንያ አስተናጋጅነት ለሚካሄደው ይኸው ሻምፒዮና የሚካፈሉ አገራት ለመለየት የመጨረሻ ማጣሪያ ጨዋታዎች ብቻ ይቀራሉ።  
ዋሊያዎቹም ከሱዳን አቻው ጋር በሐዋሳ ዓለም አቀፍ  ስታዲየም እሁድ 10 ሰዓት ላይ  ወደ ቻን ለማለፍ ይጫወታል።
በአሰልጣኝ አሸናፊ በቀለ የሚመራው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በሐዋሳ   ልምምዱን በማድረግ ላይ ነው።
አሰልጣኙ ከዛምቢያ ጋር ባደረጉት  የአቋም መለኪያ ጨዋታ በግራ የተከላካይ መስመር ያሰለፉትን የፋሲል ከነማ ክለብ ተጫዋች አምሳሉ ጥላሁንን መቀነሳቸው ታውቋል።
በምትኩም የአርባ ምንጭ ከነማው ተካልኝ ደጀኔን  ወደ ቡድኑ መልሰዋል።
በቅርቡ ከአርባ ምንጭ ከነማ ወደ ቅዱስ ጊዮርጊስ የተዛዋወረው ታደለ መንገሻ ከቡድኑ ጋር መቀላቀሉም የመሐል ክፍሉን እንደሚያጠናክረው ተገልጿል።
ዋሊያዎቹ ጅቡቲን ሱዳን ደግሞ ቡሩንዲን በማሸነፍ ነው የመጨረሻ የማጣሪያ ጨዋታቸው ላይ የደረሱት ።
የመልስ ጨዋታውንም ከአምስት ቀን በኋላ ወደ ሱዳን  አቅንቶ  የሚገጥም ይሆናል።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የደርሶ መልስ ጨዋታውን አጠቃላይ ውጤት ማሸነፍ ከቻለ በውድድሩ ተካፋይ ይሆናል።
የአፍሪካ አገራት ሻምፒዮና ( ቻን ) የአገር ውስጥ ተጫዋቾች ብቻ የሚካፈሉበት የውድድር መድረክ ነው።

ዋሊያዎቹ በሜዳቸው በቀድሞው አሰልጣኝ ሰውነት ቢሻው እየተመሩ  ሱዳንን በማሸነፍ ከ 31 ዓመት በኋላ ወደ አፍሪካ ዋንጫ መመለሳቸው ይታወሳል።  

ምንጭ

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር