በፕሪሚየር ሊጉ ሀዋሳ ከተማ ቅዱስ ጊዮርጊስን አሸነፈ

(ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ13ኛ ሳምንት ዛሬ በተደረጉ ሁለት ጨዋታዎች ተጀምሯል።
ሁለቱም ጨዋታዎች በክልል የተደረጉ ሲሆን፥ እነዚህም ሀዋሳ እና ይርጋለም ላይ የተካሄዱት።
በዚህም መሰረት ዛሬ በ09፡00 ሰዓት ሀዋሳ ላይ ሀዋሳ ከተማ ሊጉን በአንደኝነት የሚመራውን ቅዱስ ጊዮርጊስን በሜዳው አስተናግዷል።
ጨዋታውንም ሀዋሳ ከተማ 2ለ1 በሆነ ውጤት አሸንፏል።
Image result for hawassa fc'ለሀዋሳ ከተማ የማሸነፊያ ጎሎቹን ፍርደአወቅ ሲሳይ እና አስቻለው ግርማ ከመረብ ያሳረፉ ሲሆን፥ ቅዱስ ጊዮርጊስን በባዶ ከመውጣት የታደገችውን ጎል ደግሞ ደጉ ደበበ ከመረብ አሳርፏል።
በተመሳሳይ ዛሬ በ09፡00 ሰዓት ላይ በተደረገ ሌላ ጨዋታ ይርጋለም ላይ ሰዳማ ቡናን እና  ዳሽን ቢራን አገናኝቷል።
ጨዋታውም 1ለ1 በሆነ የአቻ ውጤት የተጠናቀቀ ሲሆን፥ ለሲዳማ ቡና ኤሪክ ሙራንዳ እንዲሁም የተሸ ግዛው ደግሞ ለዳሸን ቢራ የአቻነት ጎሎቹን ከመረብ አሳርፈዋል። 
የ13ኛ ሳምንት ቀሪ ጨዋታዎች እሁድ እና ማክሰኞ ቀጥሎ የሚደረጉ ሲሆን፥ እሁድ በ09፡00 ሰዓት በሚደረጉ ጨዋታዎች ድሬዳዋ ላይ ድሬዳዋ ከተማ ከአርባምንጭ ከተማን እንዲሁም  ሆሳዕና ላይ ሀድያ ሆሳዕና ከደደቢት ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።
እንዲሁም ማክሰኞ 09፡00 ሰዓት ላይ ወላይታ ድቻ ኢትዮጵያ ቡናን ቦዲቲ ላይ የሚያስተናግድ ሲሆን፥ በተመሳሳይ መከላከያ  አዳማ ከተማን አዲስ አበባ ስታድየም ያስተናግዳል።
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከኤሌክትሪክ  ደግሞ ጨዋታቸውን  በ11፡30 አዲስ አበባ ስታድየም ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።
ትናነት በተደረገ የኢትዮጵያ ፕሪምየርሊግ የ12ኛ ሳምንት የመጨረሻ ጨዋታ አዳማ ከተማ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክን ገጥሞ 3 ለ 2 በሆነ ውጤት ተሸንፏል።
በሌላ የፕሪሚየር ሊጉ መርሃ ግብር ኤሌክትሪክ ከወላይታ ድቻ በአዲስ አበባ ስታዲየም ያደረጉት ጨዋታ 1ለ1 በሆነ የአቻ ውጤት ተጠናቋል።
ፕሪምየር ሉጉን አንድ ቀሪ ጨዋታ የሚቀረው ቅዱስ ጊዮርጊስ በ23 ነጥብ ሲመራ፣ አዳማ ከተማ በተመሳሳይ 23 ነጥብ በግብ ልዩነት 2ኛ ደረጃን ላይ ተቀምጧል።
ደደቢት በ22 ነጥብ 3ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።
ዳሸን ቢራ በ13 ነጥብ እንዲሁም ሀዲያ ሆሳዕና በ5 ነጥብ የወራጅ ቀጠና ውስጥ ይገኛሉ።
በሙለታ መንገሻ 

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር