የሃዋሳ ከተማ የእሳት ኣደጋ መከላከያ ብርጌድ ከፖላንድ መንግስት የስልጠናና የቁሳቁስ ድጋፍ ልደረግለት ነው

የወራንቻ ኢንፎርሜሽን ኔትዎርክ የኣውሮፓ ኮሮስፖንዳንት የፖላንድ ዓለም ኣቀፍ ተራድኦ ማዕከልን ጠቅሶ እንደዘጋበው፤ በእሳት ኣደጋ ቁጥጥር ልምድ ያላቸውን ባለሙያዎች ያቀፍ ኣንድ ቡድን በሃዋሳ ከተማ ለሚገኙ የእሳት ኣደጋ መከላከያ ብርጌድ የኣቅም ግንባታ እና የቁሳቁስ ድጋፍ ለማድረግ በመዘጋጀት ላይ ነው።

ለኣቅም ግንባታ እና ለቁሳቁስ ድጋፍ ስራ የሚውል ኣንድ ሚሊዮን የፖላንድ ዞልት የገንዘብ ድጋፍ ከኣገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የተገኘ ሲሆን፤ ገንዘቡ ከሃዋሳ ከተማ በተጨማሪ ለባህር ዳር ከተማ እና ለሌሎች የኬኒያ ከተሞች መስል ድጋፎችን ለማድረግ እንደምውል ታውቋል።

የፖላንድ መንግስት ለሃዋሳ ከተማ ይህንን ድጋፍ ለማድረግ የወሰነው የከተማዋ እሳት ኣደጋ መከላከያ ብርጌድ ከከተማዋ የህዝብ ብዛት እና እድገት ጋር በተያያዘ የሚከስቱትን የእሳት ኣደጋዎች የመከላከል ኣቅሙ ዝቅተኛ በመሆኑ መሆኑን የፖላንድ ኣለም ኣቀፍ ተራድኦ የስራ ሃላፊ የሆኑ ኣቶ ዎጅቺዬች ዊልክ ተናግረዋል።

"The Ethiopian town Hawass firefighters can not effectively extinguish fires without approaching a fire on a dangerous distance for them. They have specialized clothing or equipment of a professional firefighter. The only thing I have is a blank breathing apparatus, approx. 100 meters of hose and two generators . It must be sufficient for 300 thousand. residents "- emphasizes Wolf.
 

በቅርቡ በሃዋሳ ከተማ ኣዲሱ ገበያ በተነሳው እሳት በሰው እና በንብረት ላይ ከፍተኛ ጉዳት ማድረሱ የሚታወስ ሲሆን፤ የከተማዋ የእሳት ኣደጋ የመከላከል ኣቅም ውስንነት ለጉዳቱ መባባስ ምክንያት ሆኗል።

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር