ከምግብ በኋላ ልናደርጋቸው የማይገቡ ሰባት ነገሮች!

ምግብ ከወሰዳችሁ በኋላ ወዲያው ልታደርጓቸው ስለማይገቡ ነገሮች ዛሬ ልንነግራችሁ ወደናል።
ከዚህ በታች የተጠቀሱት ነጥቦች ምግብ ከወሰድን በኋላ ብናደርጋቸው ከጥቅማቸው ይልቅ ጉዳታቸው ስለሚያመዝን መጠንቀቅ ይበጃል ሲል ዘክሬዚ ፋክትስ የተባለ ድረ ገፅ ያወጣውን ፅሁፍ ነው ልናጋራችሁ የወደድነው።
አንዳንዶቹ እንደ ሲጋራ ማጨስ ያሉት ደግሞ ፈፅሞም ባይደረጉ ነው የሚመከረው።
1.  ሲጋራ ማጨስ
ሲጋራ ማጨስ ምን ያህል ለጤና አደገኛ መሆኑ ቢታወቅም ከምግብ በኋላ ሲሆን ደግሞ እጅግ አደገኛ እንደሚሆን ጥናቶች ይጠቁማሉ። ቢቻል ቀንም፣ ማታም፣ በስራ ስዓትም ሆነ በእረፍት ጊዜ ሲጋራን ከማጨስ መቆጠብ ለራስ ጤና ዋስትና መግባት ነውና ቢታቀቡ ሲጋራ አጫሽ ከሆኑ ግን ከምግብ በኋላ ባያደርጉት ይላል ዘገባው።
2.  ፍራፍሬዎችን መመገብ
በየእለቱ ከምንወስዳቸው ምግቦች ውስጥ ፍራፍሬዎችን ማካተት ቢመከርም ከምግብ በኋላ እንደ ሙዝ አይነት ፍራፍሬዎችን መውሰድ የምግብ ዝውውር እንዲስተጓጎል ያደርጋል። ፍራፍሬዎች በፍጥነት የመዋሃድ ባህሪ ስላላቸውም ከምግብ ነክ ነገሮች ጋር በመጣበቅ ምግብን የማበላሸት እድል አላቸው።
3.  ሻይ ወይም ቡና
ከምግብ በኋላ ቡና ወይም ሻይ መጠጣት ምንም እንኳን የማነቃቃትና ከድብርት ለመውጣት ቢያስችልም በተለይ ሻይ ከምግብ በኋላ መውሰድ ምግብ በፍጥነት እንዲቃጠል ያደርጋል። ስለሆነም ከምግብ በኋላ ቢያንስ ከአንድ ስአት በኋላ ነው ሻይ መጠጣት የሚመከረው።
4.  ሻወር
የምግብ ውህደት የተስተካከለ እንዲሆን በቂ ጉልበትና የደም ዝውውር ወሳኝ ናቸው። 
በሞቀ ውሃ ሻወር በምንወስድበት ስዓት ወደ ቆዳችን የሚሰራጨው ደም ሙቀት ያዘለ ስለሚሆን፥ ለምግብ ፍጭት አስቸጋሪ ይሆናል።
ስለሆነም ሻወር ለመውሰድ ከምግብ በኋላ ቢያንስ 30 ደቂቃ መቆየት እንደሚገባ ነው ጥናቶች የሚጠቁሙት።
5.    ቀበቶ መፍታት
በርካቶች ከምግብ በኋላ ቀበቶ መፍታት አይገባም ይላሉ። በአንጀታችን አልያም በሆዳችን ላይ የሚያስከትለው ጉዳት ስላለ ግን አይደለም፤ ከምግብ በኋላ ቀበቶ መፍታት ከአስፈላጊው መጠን አልፈን በልተናል የሚለውን ስለሚያሳይ እንጂ።
6.    እንቅስቃሴ ወይም ሩጫ
ከምግብ በኋላ የተለያዩ ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎችን ማድረግ አልያም መሮጥ ሰውነታችን ጎጂ አሲዶችን እንዲረጭ በማድረግ የሆድ ቁርጠትን የመሰሉ ህመሞችን ያስከትላል።
ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎችን የማድረግ ፍላጎት ሲኖረንም የምንመገባቸውን ምግቦች መምረጥ አስፈላጊ ነው።
ቀለል ያሉ ምግቦችን ከወሰድን ከ30 ደቂቃ በኋላ ወክ ብናደርግ አልያም ሩጫ ብንሮጥም ያን ያህል ጉዳት አይኖረውም፤ እንቅስቃሴ በሯሱ ጤናማ ነውና።
7.    እንቅልፍ
ምንም ይሁን ምንም ከምግብ በኋላ መተኛት የሚመከር አይደለም። በምንተኛበት ጊዜ በርካታ የምግብ መፈጨትን የሚያፋጥኑ ፈሳሾች በተቃራኒ አቅጣጫ ይጓዛሉ።
ይህም የምግብ መስመሮች ወይም ቱቦዎች እንዲበሰብሱ ያደርጋል። ስለሆነም ከምግብ በኋላ ለተወሰነ ደቂቃ የተለያዩ የመዝናኛ መንገዶችን በመጠቀም ከመተኛት መቆጠብ ይገባል።
ምንጭ፦ኤፍ.ቢ.ሲ

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር