“ቡና ኃይለኛ የቆዳ ካንሰር ሊከላከል ይችላል”
ብሔራዊ የካንሰር ኢንስቲትዩት ይፋ ያደረገው ጥናት እንደሚለው ከሆነ ቡና ሜላኖማን የመከላከል ኃይል አለው፡፡
447ሺህ 357 ሰዎችን ያሳተፈውና በአማካይ ለ10 ዓመታት የዘለቀው ይህ ጥናት ቡና በብዛት የሚጠጡ ሰዎች ለበሽታው ያላቸው ተጋላጭነት አነስተኛ መሆኑን አመላክቷል።
ይሁንና የጥናቱ ውጤት ያንኑ ናሙናው የተወሰደበትን ማህበረሰብ እንጂ ሌሎችን እንደማይወክልና በጉዳዩ ላይ ተጨማሪ ጥናት እንደሚያስፈልግ ተመራማሪዎቹ አልሸሸጉም።
ምንጭ፡- ዘ ታይምስ ኦፍ ኢንዲያ
Comments
Post a Comment