POWr Social Media Icons

Friday, February 20, 2015

Photo: El & Marty
የሃዋሳ ከተማ በኢትዮጵያ ውስጥ በከፍተኛ ፍጥነት በማደግ ላይ ካሉ ከተሞች ግንባር ቀደም መሆኗን የተለያዩ ድርሳናት ይጠቅሳሉ። ከተማዋ ተፈጥሮ ባደለቻት መልካም ኣየር ንብረት፤ በእንግዳ ተቀባይ ህዝቧ፤ ለስራ፤ ለትምህርት እና ለኑሮ ምቹ በመሆኗ ብሎም ኣዲስ ኣበባ እና ለሌሎች ትላልቅ የኣገሪቷ ከተሞች በኣንጻሩ ቅርብ መሆኗ፤ ለእድገቷ እና ለተወዳጅነቷ ምክንያት ሆኗል።

ሃዋሳ ልክ እንደ ኣሜሪካዋ ላስቬጋስ ከተማ በኣገሪቱ የመዝናኛ ከተማ እየሆነች መጥታለች ይባላል።ምንም እንኳን የከተማዋ የመዝናኛ ከተማ መሆን ለነዋሪዎቿ ኣዎንታዊ እና ኣሉታዊ እድምታ ያለው ብሆንም። ኣሉታዊ ገጽታውን ለኣብነት ያህል ማንሳት ካስፈለገ፦ በሃዋሳ ከተማ ለማዝናናት የምመጡ ሰዎች ለምዝናኛ የምሆናቸውን ገንዘብ ኣስበው እና ቆጥበው ይዘው ስለምመጡ የተጠየቁትን ከፍሎ መዝናናት ስችሉ የከተማዋ ነዋሪ ግን ከጊዜ ወደ ጊዜ እየናረ ያለውን ኑሮ ለመቋቋም ኣዳጋች እየሆነባቸው ነው። በዚህ ጉዳይ ላይ እንመለስበታለን።

የከተማዋን እድገት ተከትሎ በከተማዋ መንገዶች ላይ የፈሰሱት ለምኖ ኣዳሪዎች ቁጥር በከፍታኛ ሁኔታ ጨምሯል። ከጥቂት ኣመታት በፊት በከተማይቱ ቤተክርስቲያናት ደጃፍ ብቻ ይታዩ የነበሩት ለምኖ ኣዳሪዎች በኣሁኑ ጊዜ በየትኛውን መንገድ እና ኣከባቢ ይታያሉ። ለምኖ ኣዳሪዎቹ በኣብዛኛው ከገጠር ወረዳዎች የመጡ ሲሆን፤ በኣብዛኛው ኣቅሜ ደካማ ኣረጋውያ፤ሴቶች እና ህጻናት ናቸው። የሃዋሳ ዙሪያ እና ቦሪቻ ወረዳ በኣብዘኛው በሃዋሳ ከተማ ያሉ ጎዳና ተዳዳሪዎች የመጡባቸው ወረዳዎች ሲሆኑ፤ የሁላን ወረዳ ጨምሮ ከሌሎች የሲዳማ ወረዳዎች የመጡ ይገኙበታል።

ከጎዳና ተዳዳሪዎች መካከል ከፍተኛውን ቁጥር የምይዙት ህጻናት እና ታዳጊዎች ሲሆኑ፤ እነዚህ ህጻናት እና ታዳጊዎች ለኣደገኛ ሱሶች እና ለተደራጀ ወንጀል የተጋለጡ ናቸው። በመሆኑም የሃዋሳ ከተማ ኣስተዳደር እና የሲዳማ ዞን መንግስት በተለይ ለህጻናቱ ቅርበት ያላቸው የህብረተሰብ ክፍሎች ችግር የደረሰባቸውን ህፃናት ማህበራዊናኢኮኖሚያዊ ችግሮች በመፍታት የዜግነት ግዴታቸውን መወጣት እንደሚጠበቅባቸዋል።

በተለይ ችግሮችን በዘላቂነት ለመፍታት ማህበረሰብ አቀፍ ድጋፍና ክብካቤ ጥምረት ምክር ቤቶችን በማጠናከር፣ በህፃናት ላይ የሚሰሩ መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማትን አሰራርና አደረጃጀቶች በማስተካካል ችግሩን ለመፍታት ጥረት ብያደርጉ መልካም ነው።


0 comments :