ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ በወርልድ ቴኳንዶ የመጀመሪያ የወርቅ ሜዳሊያ አገኘ

አዲስ አባበ፣ ጎንደርና ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲዎች በወርልድ ቴኳንዶ የመጀመሪያ የወርቅ ሜዳሊያቸውን አገኙእየተካሄደ ባለው የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች 8ኛው የስፖርት ፌስቲቫል ላይ የወርልድ ቴኳንዶ ውድድር ትናንት በመክፈቻው በሴቶችና በወንዶች በድምሩ 37 የዙርና የፍፃሜ ጨዋታዎች ተካሄዱ።             
በርካታ ተመልካች የነበረውና ብርቱ ፉክክር የተደረገበት የወርልድ ቴኳንዶ ውድድር በሦስት ምድብ የተወዳዳሪዎች የክብደት ልዩነት ተከፍሎ በሴቶች ከ46 እና 49 እንዲሁም በወንዶች ከ54 ኪሎ ግራም በታች የዙርና የፍፃሜ ጨዋታዎችን አስተናግዷል።
ለፍፃሜ በተደረጉት ውድድሮች ሦስት ዩኒቨርሲቲዎች የወርቅ ሜዳሊያ ማንሳት ችለዋል።
ከ46 ኪሎ ግራም በታች በተደረገው ውድድር ምህረት ከድር 5 ተጋጣሚዎቿን በማሸነፍ ለአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የወርቅ ሜዳሊያ ከማስገኘቷ ባለፈ የአምና የሻመፒዮንነት ክብሯን ማስጠበቅ ችላለች።
በዚህ ዘርፍ የአዳማ ሣይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ የብር እንዲሁም የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ የነሐስ ሜዳሊያ ተሸላሚ ሆነዋል።
በተመሳሳይ በሴቶች ከ49 ኪሎ ግራም በታች በተደረገ ውድድር ህይወት ተስፋ ለሀዋሳ ወርቅ ስታስገኝ ድሬዳዋና ወልዲያ ዩኒቨርሲቲዎች በቅደም ተከተላቸው የብርና የነሐስ ሜዳሊያ መሆን ችለዋል።
በወንዶች ከ54 ኪሎ ግራም በታች ደግሞ የጎንደር ዩኒቨርሲቲው ውብሸት ደስያለው ድንቅ ብቃት በማሳየት ጭምር የወርቅ ሜዳሊያውን አንስቷል።
የመቐለና የሀሮማያ ዩኒቨርስቲዎች ደግሞ በቅደም ተከተላቸው የብርና የነሐስ ሜዳሊያ ተሸላሚ ሆነዋል።
የወርልድ ቴኳንዶ ውድድር ዛሬም በወንዶች ከ58 ኪሎ ግራም በታች የሚጠበቅ ሲሆን ሌሎች የማጣሪያና የፍፃሜ ውድድሮች በመካሄድ ላይ ናቸው።
በአዳማ ሣይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ አስተናጋጅነት እየተካሄደ ያለው የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች 8ኛው የስፖርት ፌስቲቫል በመልካም ስፖርታዊ ጨዋነት ታጅቦ ፍፃሜው ለማግኘት ጥቂት ቀናት ቀርተውታል።
- See more at: http://www.ena.gov.et/index.php/sport/item/1837-2015-02-10-05-39-02#sthash.OUVbKa9h.dpuf

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር