በስምንት ምድብ የተከፈሉ 32 ዩኒቨርስቲዎች በሚፎካከሩበት የእግር ኳስ ውድድር ሀዋሳ ከምድቡ አምስት ነጥብ በመያዝ በቀዳሚነት አላፊ ሆነ

8ኛው የመንግሥት ዩኒቨርስቲዎች የስፖርት ፌስቲቫል በማጣሪያና በፍጻሜ ውድድሮች ቀጥሏል
ሰባተኛ ቀኑን የያዘው የመንግሥት ዩኒቨርስቲዎች 8ኛው የስፖርት ፌስቲቫል በዙር የማጣሪያና የፍፃሜ ውድድሮች በአጓጊነቱ እንደቀጠለ ነው።
በ13 የስፖርት ዓይነቶች ከ7 ሺህ በላይ ተወዳዳሪዎች የታደሙበት ፌስቲቫሉ ያሳየው ስፖርታዊ ጨዋነት አሁንም እንደተጠበቀ ይገኛል።
ትናንት የተጀመረው የውኃ ዋና ስፖርት በወንጂ የመከላከያ ሠራዊት የአዳማ ጋርመንት ፋውንዴሽን መዋኛ ሥፍራ ተጀምሯል።
የ1 ሺህ 500 ሜትር የነፃ ቀዘፋ የመክፈቻ የፍጻሜ ውድድር ሆኖ ድሬዳዋና አክሱም የመጀመሪያውን የወርቅ ሜዳሊያ አግኝተውበታል።
መቐለ በወንድ የብር፣ አክሱም ደግሞ የነሐስ ሜዳሊያ አሸናፊ ሲሆኑ፥ ባህርዳርና ወሎ ዩኒቨርስቲዎች የብርና የነሐስ ሜዳሊያ በቅደም ተከተል ለግላቸው አድርገዋል።
በስምንት ምድብ የተከፈሉ 32 ዩኒቨርስቲዎች የሚፎካከሩበት የእግር ኳስ ውድድርም ሀዋሳ ከምድቡ አምስት ነጥብ በመያዝ በቀዳሚነት አላፊ መሆኑን አረጋግጧል።
የመምና የሜዳ ውድድሮች እንደሚደረጉበት በሚጠበቀው አትሌቲክስም ዛሬ በሴቶች የጦር ውርወራ የፍጻሜ ውድድር ይካሄዳል።
የ1 ሺህ 500፣ የ400 እና የ100 ሜትር የአጭር ርቀት የማጣሪያ ውድድሮች ዛሬ በሁለቱም ጾታዎች ይከናወናሉ።
የቅርጫት፣ የመረብና እጅ ኳስ እንዲሁም ባድሜንተን፣ ቴኒስና ቼዝ በማጣሪያ የዙር ውድድሮች ቀጥለዋል።
ምንጭ፦ፋና 

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር