ተመድ ዜግነት የሌላቸው ወገኖች መፍትሄ እንዲያገኙ ጥረት ላይ ነኝ አለ

በአለም ላይ ዜግነት አልባ የሆኑ ወገኖችን በ10 ዓመታት ውስጥ መፍትሄ እንዲያገኙ ለማድረግ እየሰራ መሆኑን የተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽን  አስታወቀ፡፡
እንደ ኮሚሽኑ መረጃ በአሁኑ ወቅት በአለም ላይ ቢያንስ 10 ሚሊዮን የሚሆኑ ፓስፖርትም ሆነ ዜግነት ሳይኖራቸው በጥገኝነት የሚኖሩ ሰዎች አሉ፡፡ በየ10 ሰከንዶቹም ዜግነት የሌላቸው ህፃናት ይህችን አለም ይቀላቀላሉ፡፡
በዚህም ምክንያት እነዚህ ስደተኞች የጤናና የትምህርት እንዲሁም እንደ መምረጥ ያሉ ፖለቲካዊ መብታቸውን ተነፍገው ይኖራሉ፡፡
የተመድ የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽን ታድያ ሀገራት ዜግነት የሌላቸውን ህፃናትና የማህበረሰብ ክፍሎች ዜግነት እንዲያገኙ ለማረግ  እንደሚንቀሳቀስ ነው ያስታወቀው፡፡     
በየተለያየ ምክንያት ሰዎች ዜግነት ላይኖራቸው አልያም ዜግነታቸውን ሊያጡ ይችላሉ፡፡
በተለይም በስደተኛ መጠለያ ጣቢያዎች ውስጥ የሚወለዱ ህፃናት የተወለዱበት ሀገር ዜግነትም ሆነ የወላጆቻቸውን ዜግነት የማግኘት እድላቸው ጠባብ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ ችግሩን እንደሚጎላ መረጃዎች የመለክታሉ፡፡
እንደ የማይናማሮቹ የሮሂጋ አናሳ ጎሳዎች የማንነት ጥያቄያቸው አሁንም መልስ አለማግኘትና የዜግነት መብቶቻቸውንም ተነፍገው የሚኖሩ ናቸው፡፡
በ27 ሀገራት እናቶች ለልጆቻቸው ዜግነታቸውን ማስተላለፍ የማይችሉ ሲሆን እንደ የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽን እነዚህ ምክንያቶች ዜግነት አልባ ትውልድ እየፈጠረ ይገኛል፡፡
ዜግነት አልባነትን ከአለም ላይ ጨርሶ ለማሶገድ እንደጎርጎሮሳዊያኑ አቆጣጠር  የ1954ቱን የዜግነት አልባ ሰዎች ሁኔታ ስምምነትና የ1961ዱን የዜግነት አልባነት ቅነሳ ስምምነቶች ተግባራዊነት ላይ ትኩረት አድርጎ እንደሚሰራኮሚሽኑ አስታውቋል፡፡  
ምንጭ፡- EBC

Comments

Popular posts from this blog

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር