በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የ‹‹አብዮታዊ ዴሞክራሲ›› ሰልጣኝ ተማሪዎች በፌደራል መደብደባቸው ታወቀ ፤ ተቃውሞ አስነስተዋል የተባሉት ተማሪዎች ታስረዋል

(Photo: Ken Opprann)

ሰልጣኝ ተማሪዎች በፌደራል መደብደባቸው ታወቀ * ተቃውሞ አስነስተዋል የተባሉት ተማሪዎች ታስረዋል


  • 364
     
    Share
በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የ‹‹አብዮታዊ ዴሞክራሲ›› ስልጠና ወስደው የውሎ አበል ያልተከፈላቸው የመጀመሪያ አመትና ነባር ሶስተኛ ዙር ሰልጣኞች ‹‹የውሎ አበላችን ይሰጠን›› በሚል ሰላማዊ ሰልፍ በመውጣታቸው በትናንትናው ዕለት በፌደራል ፖሊስ መደብደባቸውን ተማሪዎቹ ለነገረ ኢትዮጵያ ገለጹ፡፡ ሰላማዊ ሰልፉን አደራጅታችኋል የተባሉ በርከት ያሉ ተማሪዎች መታሰራቸውንም ታውቋል፡፡
ስልጠናውን አርብ መስከረም 30/2007 ዓ.ም የጨረሱ ሲሆን መጀመሪያ ላይ እንደሚከፈላቸው ቃል ተገብቶላቸው የነበረው የውሎ አበል አይከፈላችሁም በመባላቸው በትናንትናው ዕለት ሰላማዊ ሰልፍ ወጥተዋል፡፡ ተማሪዎቹ አበሉ አይከፈላችሁም ቢባሉም አሰልጣኞቻቸው ‹‹ገንዘቡ መጥቷል፡፡ አንከፍልም የሚሉት ዝም ብለው ነው›› ማለታቸው ተማሪዎቹ ሰላማዊ ሰልፍ እንዲወጡ ገፋፍቷል ተብሏል፡፡ የፌደራል ፖሊስ ሴት ተማሪዎች ከግቢው እንዳይወጡ የከለከለ ሲሆን ወንድ ተማሪዎች ከግቢው እንዲወጡ ከተደረጉ በኋላ መደብደባቸውንና መታሰራቸውን ተማሪዎቹ ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡
የደኢህዴን 22 አመት ምስረታን ተከትሎ በሀዋሳ በርከት ያለ ፌደራል ፖሊስ እንደነበርና ተማሪዎቹ አበላቸው እንዲከፈላቸው በጠየቁበት ወቅት ‹‹ከተማው ውስጥ ፌደራል ሞልቷል፡፡ እናስደበደባችኋለን›› እያሉ ያስፈራሯቸው እንደነበር ታውቋል፡፡
የወሬው ምንጭ www.zehabesha.com ነው።

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር