ሁለት የኢንተለጀንስ ሠራተኞች ጉቦ ሲቀበሉ እጅ ከፍንጅ ተያዙ


በአዲስ አበባ ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ሁለት የኢንተለጀንስ ሠራተኞች ጉቦ ሲቀበሉ እጅ ከፍንጅ መያዛቸውን የፌዴራል ሥነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን አስታወቀ፡፡

የኮሚሽኑ የክትትል ሠራተኞች እጅ ከፍንጅ የያዙት የገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን ፅህፈት ቤት የኢንተለጀንስ ክፍል ኃላፊ እና አንድ  ሠራተኛ ሰሞኑን  ከነጋዴ ጉቦ ሲቀበሉ ነው፡፡
የኢንተለጀንስ ኃላፊ እና ሠራተኛ የነበሩት ሁለቱ ግለሰቦች ወንጀሉን የፈፀሙት በመጀመሪያ ያለምንም የመስሪያ ቤት ደብዳቤ አንድ ነጋዴ ዘንድ ቀርበው የተለያዩ የንግድ ሰነዶችን በመቀበል ነው፡፡
ግለሰቦቹ ከነጋዴው የተቀበሏቸውን ሰነዶች ወደ መስሪያ ቤታቸው ሳይወስዱት ከአንድ በሒሳብ ስራ ላይ የተሰማራ የግል ድርጅት ዘንድ በማስቀመጥ ነጋዴውን ሀሰተኛ ሰነዶችን ይዘሃል፣ ለእኛ ጉቦ ከሰጠኸን አትቀጣም በሚል በመደራደር መሆኑን ታውቋል፡፡
መረጃው የደረሰው ኮሚሽኑ ተገቢውን ክትትል በማድረግ የክፍለ ከተማው የየገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን ጽህፈት ቤት የኢንተለጀንስ ኃላፊ እና ሠራተኛው ባለፈው ሰኞ ከነጋዴው ግለሰብ 20 ሺህ ብር ጉቦ ሲቀበሉ እጅ ከፍንጅ መያዛቸውን ለማወቅ ተችሏል፡፡
በአሁኑ ጊዜ ኮሚሽኑ በሁለቱ ተከሳሾች ላይ ተጨማሪ የምርመራ ማስረጃዎችን አሰባስቦ ፍርድ ቤት ለማቅረብ በሂደት ላይ እንደሚገኝ  ለኢዜአ በላከው መግለጫ ጠቁሟል፡

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር