POWr Social Media Icons

Friday, October 24, 2014

አንድ ሚሊየን የኢቦላ መከላከያ ክትባት በፈረንጆቹ 2015 ለማሰራጨት መዘጋጀቱን የአለም የጤና ድርጅት አስታወቀ።
በቀጣይ አመት አጋማሽ ብቻ በብዙ መቶ ሺህ የሚቆጠሩ ክትባቶች በቫይረሱ ክፉኛ በተጠቁት ጊኒ፣ ላይቤሪያ እና ሴራሊዮን በተያዘው ዓመት ነሃሴ ወር ላይ እንደሚሰራጩም ነው የገለፀው።
ይሁንና ክትባቱ የኢቦላን ስርጭትን ለመግታት ከሚደረገው ህሉን አቀፍ ጥረት በላይ ተዓምር መፍጠር የሚችል መሳሪያ ተደርጎ እንዳይወሰድም አሳስቧል።
የኢቦላ ቫይረስ እስካሁን የ4 ሺህ 500 ሰዎችን ህይወት ቀጥፏል።
በኢቦላ ቫይረስ ተይዞ ካገገመ በሽተኛ የተወሰደን ደም በመጠቀም የኢቦላ ቫይረስን ለመከላከል የሚያስችል ክትባት ለመስራት መዘጋጀቱንና በፈረንጆቹ 2015 ተግባራዊ እንደሚደረግ የአለም የጤና ድርጅት ምክትል ዳይሬክተር ዶክተር ፓውል ኬኒ ቀደም ብለው መናገራቸው ይታወሳል።
ምንጭ፦ ኤፍ.ቢ.ሲ

0 comments :