የ2023ቱ የአፍሪካ ዋንጫ አዘጋጅ መረጣ ተገቢነት የለውም፡- ኢትዮጵያ

የ2023ቱን የአፍሪካ ዋንጫ እንድታዘጋጅ ለጊኒ መስጠቱ ተገቢ እንዳልነበር የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ገለጸ።
የፌዴሬሽኑ ፕሬዝዳንት አቶ ጁነዲን ባሻ የአፍሪካ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በአዲስ አበባው ጉባዔው ላይ ከያዘው አጀንዳ ውጭ የ2023ቱን የአፍሪካ ዋንጫ አዘጋጅ መምረጡ ተገቢ አይደለም።
በዚህ ጉባዔው ላይ የጎርጎሮሳውያኑ 2019 እና 2021 የአፍሪካ ዋንጫ አዘጋጅ ሀገራትን መምረጥ ቢሆንም አጀንዳው የ2023ቱ ዋንጫ አዘጋጅ ሀገር ግን ምርጫ ተገቢ አለመሆኑን ተናግረዋል።
የአፍሪካ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አዲስ አበባ ላይ ባደረገው ጉባዔው የ2019 አፍሪካ ዋንጫ አዘጋጅ ካሜሩን እንዲሁም የ2021 ዋንጫን ደግሞ ኮቲዲቯር እንዲያዘጋጁ መርጧል።
ኢትዮጵያ የአፍሪካን ዋንጫ ለማዘጋጀት ፍላጎቱ ቢኖራትም አሁን ከሊቢያ የተነጠቀውን የ2017 ዋንጫ ለማዘጋጀት ያቀረበችው ጥያቄ ውድቅ ከሆነ ለረጅም ጊዜ መጠበቅ ይኖርባታል። 
ኢብኮ ስፖርት ኦንላይን

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር