ኢትዮጵያ በናንጂንግ ኦሎምፒክ ከአፍሪካ ቀዳሚ ሆነች

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 19፣ 2006 ፣ 2006 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ኢትዮጵያ በቻይና ናንጂንግ እየተካሄደ ባለው የታዳጊ ወጣቶች የኦሎምፒክ ጨዋታ ቅዳሜና ትናንት በተደረጉ የአትሌቲክስ የፍጻሜ ውድድሮች ከአፍሪካ አንደኛ ከአለም የ21ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች።
በሴቶች ኮከብ ተስፋዬ በ1 ሺህ 500 ሜትር 4 ደቂቃ ከ15 ሰኮንድ ከ38 ማይክሮ ሰከንድ ውድድሩን በአንደኝነት በማጠናቀቅ የወርቅ ሜዳሊያ አስመዝግባለች።
በ8 መቶ ሜትር ሴቶች የፍጻሜ ውድድርደግሞ ሀዊ አለሙ በ2 ሰዓት ከ6 ደቂቃ ከ01 ማይክሮ ሰከንድ ሁለተኛ ሆና ስትጨርስ፥ በሴቶች የ3 ሺህ ሜትር ብርሃን ደምሴ ውድድሩን በሶስተኝነት አጠናቃለች።
በወንዶች ዮሚፍ ከጀልቻ በ3 ሺህ ሜትር ፍጻሜ በ7 ደቂቃ ከ56 ሰከንድ ከ20 ማይክሮ ሰከንድ ውድድሩን በአንደኝነት በማጠናቀቅ የወርቅ ሜዳሊያ አስገኝቷል።
በወንዶች 1 ሺህ 500 ሜትር ደግሞ ሙሉጌታ አሰፋ በሁለተኝነት ማጠናቀቅ ችሏል።
ውድድሩ በመጪው ረቡዕ ፍጻሜውን የሚያገኝ ሲሆን፥ ኢትዮጵያውያን ወጣት ታዳጊ ስፖርተኞች ጥሩ ፉክክር እያደረጉ ይገኛሉ።
ዛሬ ከሰዓት በኋላ የ2 ሺህ ሜትር መሰናክል በሁለቱም ጾታና በ800 ሜትር ወንዶች ኢትዮጵያውያን በርቀቱ ተካፋይ ይሆናሉ ።
ምንጭ፦ ኤፍ/ቢ/ሲ

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር