በሐዋሳ ከተማ ህዝባዊ ስብሰባዎችን ማድረግ ለተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች ኣስቸጋሪ እንደሆነ ቀጥሏል

-ኢራፓ በሐዋሳ ሊያደርገው የነበረው ስብሰባ እንዳይካሄድ መከልከሉን ገለጸ
-በወጣው መግለጫ የፓርቲው መሪዎች አልተግባቡም
የኢትዮጵያ ራዕይ ፓርቲ (ኢራፓ) ነሐሴ 11 ቀን 2006 ዓ.ም. እና በተለዋጭ በተያዘ ፕሮግራም ነሐሴ 18 ቀን 2006 ዓ.ም. በደቡብ ክልል ርዕሰ ከተማ በሐዋሳ ሊያደርገው የነበረው ሕዝባዊ ስብሰባ፣ በኢሕአዴግ ተፅዕኖ ፈጣሪነት ተገቢ ባልሆነ ምክንያትና ቢሮክራሲ መከልከሉን አስታወቀ፡፡
በፓርቲው የተሰጠው መግለጫ ስብሰባ እንዳናካሂድ ተከልክለናል ቢልም፣ የፓርቲው ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ ተሾመ ወልደ ሰማያት ግን መግለጫው የወጣው ‹‹የፓርቲው ሥራ አስፈጻሚ ሳይወያይበት›› ነው በማለት ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም ምክትል ፕሬዚዳንቱ፣ ‹‹ኢራፓ የፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት አባል ስለሆነ ጉዳዩን ወደዚያ መውሰድ እንጂ መግለጫ ለማውጣት መቸኮሉ አስፈላጊ አይደለም፤›› በማለት ገልጸዋል፡፡  
የፓርቲው ፕሬዚዳንት አቶ ተሻለ ሰብሮ በበኩላቸው፣ ‹‹›እያንዳንዱ ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ የፓርቲው ሥራ አስፈጻሚ አይወያይም፤›› ብለው፣ መግለጫውን በፓርቲው ማሕተም ማውጣታቸውን ገልጸዋል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም ‹‹በሁሉም ጉዳዮች ላይ መግለጫ ለመስጠት የግድ የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ መሰብሰብ አይኖርበትም፤›› በማለት የወጣው መግለጫ የፓርቲው አቋም ነው በማለት ምላሽ ሰጥተዋል፡፡
ፓርቲው በሐዋሳ ሊያደርገው የነበረው ሕዝባዊ ስብሰባ ዓላማ ሰላማዊና ዲሞክራሲያዊ የፖለቲካ ፕሮግራሙን ለማስተዋወቅ፣ በአገራዊና ሕዝባዊ መግባባት አስፈላጊነት ላይ ግንዛቤ ለማስጨበጥ፣ እንዲሁም የፖለቲካ ፓርቲዎችን የሥነ ምግባር ደንብን ለማስረዳት እንደነበር በመግለጫው ተጠቅሷል፡፡ 
ከዚህ በተጨማሪም መግለጫው፣ ‹‹ፓርቲያችን በያዘው የሕዝባዊ ስብሰባ ፕሮግራም መሠረት በሐዋሳ ከተማ በግል ሆቴሎችም ሆነ በመንግሥት አዳራሽ ስብሰባውን ለማካሄድ ያደረግነው እልህ አስጨራሽ ትግል ባለመሳካቱ በእጅጉ እናዝናለን፤›› በማለት ያትታል፡፡
‹‹ኢሕአዴግ በተለያዩ ጊዜያት በሚፈጽማቸው ተግባሮቹ በኢትዮጵያ ውስጥ የሚታየውን ጭላንጭል የፖለቲካ ምኅዳር ይጀስ እያጠፋው፣ የመድበለ ፓርቲ ሥርዓቱን በማፈን የነበረውን ተስፋ ይባስ እያቀጨጨ በመሄድ ላይ እንደሆነ አረጋግጠናል፤›› ይላል፡፡
ኢራፓ ገዥው ፓርቲ እየሄደበት ካለው አፍራሽ አካሄድ በመመለስ ለመድበለ ፓርቲ ሥርዓቱ መጐልበትና ለፖለቲካ ምኅዳሩ መስፋትኧ ከሕገ መንግሥቱ መሠረተ ሐሳብ አንፃር ኃላፊነቱን እንዲወጣ ፓርቲው ጠይቋል፡፡  
_____________________________________________________
We welcome comments that advance the story through relevant opinion and data. If you see a comment that you believe is irrelevant or inappropriate, please! inform us. The views expressed in the comments do not represent those of Bloggers. 

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር