ዩኒቨርስቲው የቆጮን ምርት በቀላል ዘዴ ጥቅም ላይ ለማዋል እየሰራ ነው


ዲላ ነሐሴ 4/2006 የቆጮን ምርት በቀላል ዘዴ ጥቅም ላይ ማዋል የሚያሰችል አዲስ ቴክኖሎጂ ለአርሶ አደሩ እያስተዋወቀ መሆኑን በሃዋሳ ዩኒቨርስቲ የቴክኖሎጂ ኢንሰቲትዩት ገለጸ፡፡
ኢንሰቲትዩቱ የቆጮ ማጠብያ ቴክኖሎጂ ማሽንና የአሰራሩ ዘዴውን ከሚገልጽ ሙሉ መረጃ ጋር ሰሞኑን ለዲላ ቴክኒክና ሙያ ኮሌጅ ሰጥቷል፡፡
የኢንስቲትዩት ሳይንቲፊክ ዳይርክተር ዶክተር ሞልቶት ዘውዴ እንደገለጹት የቆጮን ምርት በዘመናዊ መንገድ በቀላል ዘዴ ለማምረት የሚያስችል ቴክኖሎጂን በማስፋፋት በተለይ የሴት አርሶ-አደሮችን ድርብ ስራ ለመቀነስ እየሰሩ ናቸው፡፡�
ቴክኖሎጂው በአንድ ጊዜ ከሶስት ኪሎ በላይ ቆጮ በማጠብ ጥራቱን የጠበቀና ከብክነት የፀዳ ምርት ከመስጠቱም ባሻገር በሴቶች ላይ የሚደርሰውን የስራ ጫና ያቃልላል፡፡
ዶክተር  እንዳሉት ከዚህ በፊት ቆጮን አጥቦ ለመጠቀም የሚወሰደውን ጊዜ በግማሽ መቀነስ የሚያስችል አሰራር ነው፡፡
በእንሰት ምርት ላይ ችግር ፍቺ የሆኑ ምርምሮችን በማድረግ ቴክኖሎጂን በማስፋፋት የቆጮን ምርትና ምርታማነት ለመጨመር የቴክኖሎጂ ኢንሰቲትዩቱ ትኩረት መስጠቱን ተናግረዋል፡፡
ምርቱ በሚሰጠው ግልጋሎት ልክ ምርምር አልተደረገበትም ያሉት ዳይሬክተሩ በክልሉ ቆጮ አምራች የሆኑ በርካታ አካባቢዎች ቴክኖሎጂውን በመጠቀም እየደረሰ ያለውን የምርት ብክነትንና የአርሶ አደሩን ጉልበት ስለሚቀንስ ቴክኖሎጂውን በስፋት ለማዳረስ እየሰሩ ናቸው፡፡
የዲላ ቴክኒክና ሙያ ኮሌጅ ምክትል  ዲን አቶ ተሾመ እንግዳ በበኩላቸው ከሃዋሳ ዩኒቨርስቲ የቴክኖሎጂ ኢንሰቲትዩት ጋር በመተባበር የእውቀትና የቴክኖሎጂ ሽግግር ማደረጋቸው ኮሌጁ ላለበት አካባቢ ማህበረሰብ በርካታ ጠቀሜታ እንዳለው አስረደተዋል።
ቴክኖሎጂውንም በአጭር ጊዜ ውስጥ በዝቅተኛ ዋጋ በማምረትና በዘርፉ ለተሰማሩ ማህበራት በማከፋፈል ለቴክኖሎጂው ስርጸትና አርሶ አደሩን ተጠቃሚ ለማድረግ  ኮሌጁ ጥረት እንደሚያደርግ ገልጸዋል፡፡
የጌዴኦ ዞን አርሶ አደር አቶ ደረጀ ሃብተመስቀል በአካባቢያቸው እሳቸውን ጨምሮ አርሶ-አደሩ በስፋት የሚጠቀመው የቆጮ ምርትን መሆኑን ጠቁመዋል፡፡
ቴክኖሎጂውን በማሰተዋወቅ ላይ ከሚገኘው የሃዋሳ ዩኒቨርስቲ እንደተረዱት በተለይ ለሴት አርሶ-አደሮች ያለው ጠቀሜታ ከፍተኛ ነው፡፡
ቴክኖሎጂው በዘለልማድ ይከናወኑ የነበሩ አሰልቺ አሰራሮችን በመቀነስ ያለው አስተዋፀኦ ቀላል ባለመሆኑ እሳቸውም ተጠቅመው ሌሎችም እንዲገለገሉበት የበኩላቸውን ጥረት እንደሚያደርጉ ገልጸዋል፡፡
ምንጭ፦ ኢዜኣ
____________________________________________________________
We welcome comments that advance the story through relevant opinion and data. If you see a comment that you believe is irrelevant or inappropriate, please! inform us. The views expressed in the comments do not represent those of Bloggers.

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር