በዚህ ኣመት በሲዳማ ዞን 21 ኣዲስ የተሽከርካሪ ስምሪት መስመሪ መከፈቱ ተሰማ



በተጠናቀቀው የበጀት ዓመት በሲዳማ ዞን ኣዳዲስ የተሽከርካሪ ስምርት መስመር መከፈቱን የክልሉ ትራንስፖርት ቢሮ  ገለጸ።

የቢሮውን ኃላፊ አቶ ላጫ ጋሩማ ጠቅሶ ኢዜአ እንደዘጋበው፤ በዞኑ 21 ኣዲስ የሰምሪት መስመር ከፍቷል።


አዲስ በተከፈቱ የስምሪት መስመሮች ቋሚ የህዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪዎችን በመመደብና ታሪፍ በማውጣት የትራንስፖርት አገልግሎት ሳይቆራረጥ እንዲቀጥል መደረጉንና በዚህም አርሶ አደሩ ምርቱን ገበያ ለማቅረብና በእግር ረዥም መንገድ ከመጓዝ እንዳላቀቀው እኙሁ ኃላፊ ተናግረዋል።

በሀዋሳ ዙሪያ ወረዳ የዶሬ ባፈና ነዋሪ አርሶ አደር ብርሀኑ ባጢሶና አርሶ አደር ይፍሩ ይማም ቀደም ሲል ከሀዋሳ እስከ ወረዳ ከተማ  ካልሆነ ወደ ገጠር ቀበሌ ለመጓዝ የፈረስ ጋሪና የጭነት መኪና ይጠቀሙ እንደነበር አስታውሰው አሁን በሳምንቱ አብዛኛው ቀናት መለስተኛ አውቶብሶች በበመደባቸው መደሰታቸውን ገልጸዋል።

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር