ሰሞኑን ሃዋሳ ላይ ልምምድ ሲያደርግ የሰነበተው የኢትዮጵያ ብሔራዊ እግር ኳስ ብድን ወደ ኣንጎላ ያቀናል


አዲስ አበባ ሐምሌ 21/2006 የወንዶች እግር ኳስ ብሔራዊ ቡድን የወዳጅነት ጨዋታ ለማድረግ በመጪው ረቡዕ ወደ አንጎላ እንደሚያቀና የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አስታወቀ።
የፌዴሬሽኑ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ወንድምኩን አላዩ እንደተናገሩት ብሔራዊ ቡድኑ የወዳጅነት ጨዋታውን ከአንጎላ አቻው ጋር የፊታችን እሁድ ያካሂዳል፡፡
ቡድኑ የአቋም መለኪያ የወዳጅነት ጨዋታውን የሚያደርገው በሚቀጥለው ዓመት ሞሮኮ በምታዘጋጀው የአፍሪካ ዋንጫ ላይ ለመካፈል እንደሆነ ጠቁመው በተጨማሪም ጨዋታው ኢትዮጵያ ከአልጄሪያ ጋር ለምታደርገው የማጣሪያ ውድድር ለቡድኑ ቅድመ ዝግጅት ይረዳዋል ብለዋል።
በፖርቱጋላዊው አሰልጣኝ ማሪያኖ ባሬቶ በሃዋሳ ልምምድ ሲያደርግ የሰነበተው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድኑ በአሁኑ ወቅት በአዲስ አበባ ይገኛል።
አስልጣኙ አገሪቱን በመወከል ከአንጎላ ብሔራዊ ቡድን ጋር የሚጫወቱ ተሰላፊዎችን ዛሬና ነገ ይፋ እንደሚያደርጉ ይጠበቃል።
ብሄራዊ ቡድኑ ከአንጎላ ጨዋታ መልስ ወደ ብራዚል በመጓዝ ከአምስት የብራዚል ክለቦች ጋር የወዳጅነት ጨዋታዎችን ያደርጋል ያሉት ኃላፊው  ዋልያዎቹ በብራዚል ለ17 ቀናት እንደሚቆዩ ገልጸዋል።
ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ጋር የወዳጅነት ጨዋታ ለማድረግ ከግብፅ፣ ቤኒን እና ከሌሎችም ብሔራዊ ቡድኖች ጥያቄዎች መቅረባቸውን አቶ ወንድምኩን ተናግረዋል።
ግብጽ በነሐሴ ወር ከኢትዮጵያ ጋር የወዳጅነት ጨዋታ ለማድረግ ያቀረበችው ጥያቄ ፌዴሬሽኑ እንደተቀበለውና በቀጣይ ለአገሪቱ እንደሚያሳውቅ ገልጸዋል።
ከቤኒን እና ከሌሎች ብሔራዊ ቡድኖች በኩል ለቀረበው ጥያቄ ግን ፌደሬሽኑ እስካሁን ምላሽ አልሰጠም።

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር