የሲዳማ ዘመን መለወጫ ፊቼ በኣል በዩኔስኮ ጊዜያዊ መዝገብ መመዝገቡ ተሰማ፤ በኣሉ ከትናንትና ጀምሮ በተለያዩ ዝግጅቶች በመላው ኣለም በመከበር ላይ ነው

ፎቶ: ከመብራቴ መለሰ የፌስቡክ ገጽ ላይ የተገኘ 
የፊቼን በኣል በዩኔስኮ በኣለም ቅርስነት ለማስመዝገብ ከጫፍ መደረሱን  ድረሳቸውን የሲዳማ ዞን የባህል ቱሪዝምና የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ገለፀ።
የመምሪያው ሀላፊ ካላ ወርቅነህ ፍላቴን ጠቅሶ ፋና እንደዘጋበው፥ የፊቼን በኣል በዩ ኔስኮ በማስመዝገቡ እንቅስቃሴ የመሪነቱን ሚና በመጫዎት ላይ ያለው የሲዳማ ዞን በአሉ በዩኔስኮ ጊዜያዊ መዝገብ ላይ መመዝገቡን የምገልጽ ደብዳቤ እንደደረሰው ኣስታውቋል።
ኣገሪቱን የማይዳሰሱ ቅርሶች በዩኔስኮ በኣለም ቅርስነት ለማስመዝገብ በተደረገው እንቅስቃሴ እስከኣሁን የመስቀልን በኣል በኣለም ቅርስነት ለማስመዝገብ የተቻለ ሲሆን፤ ከመሰቀል በኣል ውጭ የፊቼን እና ሌሎች የማይዳሰሱ የኣገሪቱን ብርቅዬ ባህላዊ ቅርሶች በዩኔስኮ  የማስመዝገቡ ህደት ተጠናክሮ  መቀጠሉ ታውቋል።
የፊቼ በኣል በዩኔስኮ በኣለም ቅርስነት መመዝገብ በኣሉን ለማሳደግ ብሎም ለመንከባከብ ከማስቻሉ በላይ የሲዳማን ህዝብ ባህላዊ ቱፊቶችን ለኣለም ህዝብ ለማስተዋወቅ ያስችላል።
በኣሉ ከትናንትና ጀምሮ በመላዋ ሲዳማ በተለይ በሲዳማ መዲና በሃዋሳ ከተማ በታላቅ ድምቀት በተለያይ ዝግጅቶች በመከበር ላይ ሲሆን፤ጠዋት ላይ የአርድና የትንበያ ስነስርአት በብሄረሰቡ አባቶች ተከናውኗል።
በትንበያው ዘመኑ የሰላም የፍቅርና ወጣቱ ለስራ የሚነሳሳበት ዘመን ይሆናል ብለዋል።
በዛሬው እለት የጨንበላላ በአል በመከበር ላይ ነው።
በተያያዘ  ዜና የፊቼ በኣል ከሲዳማ ውጭ በኣሜሪካ፤ በኣውሮፓ እና በደቡብ ኣፍሪካ በሚገኙ የሲዳማ ዳይስፖራ ኣማካይነት በኣለም ኣቀፍ ደረጃ በመከበር ላይ ነው።
የወራንቻ ኔትወርክ ያሰባሰባቸው መረጃዎች እንደምያመለክቱት፤ በተለያዩ ኣገራት የምኖሩ የሲዳማ ኮሚኒት ኣባላት የፊቼን በኣል በግል  እና በቡድን በመሆን የሲዳማን ባህላዊ ኣልባሳትን በመልበስ በማክበር ላይ ናቸው።

ከሬድዮ ፋና የተገኘውን መረጃ ለማየት እዚህ ይጫኑ ኤፍ.ቢ.ሲ

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር