መንግስት ለቦርቻ ወረዳ ህዝብ የንጽህ ውሃ ጥያቄ ኣፋጣኝ ምላሽ መስጠት ኣልቻለም

በሲዳማ ዞን ውስጥ በከፍተኛ የውሃ እጥረት የምታወቀው የቦርቻ ወረዳ ነዋሪዎች ለዘመናት የሚያነሱት የውሃ ጥያቄ እስከኣሁን ከምመለከተው ኣካል ኣጥጋቢ ምላሻ ማግኘት ኣልቻለም።
በወረዳው ውስጥ መንግስታዊ እና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች የንጽህ ውሃ ለወረዳው ህዝብ መስራታቸውን በተደጋጋሚ ቢገልጹም፤ የወረዳው የንጽህውሃ ሽፋን ከ19% ኣይበልጥም።
ሪፖርተራችን ጥቻ ወራና ከወረዳ የላከልን ዘገባ እንደምያመለክተው፤ በቦርቻ ወረዳ ውስጥ ያለውን ከፍተኛ የውሃ እጥረት ችግር ለመፍታት በቀዳሚነት ተሰፋ የተጣለበት የኣዋዳ_ቦርቻ ፕሮጄክት ሲሆን፤ የዚህ ፕሮጄክት ስራ ከተጀመረ ዘንድሮ ኣምስተኛ ኣመቱን ይዟል።
እስከ ኣሁን ድረስ ባለው የሰራ ህደት ወደ 120 ሚሊዮን ብር ወጪ የተደረገ ሲሆን የፕሮጄክቱ የመጀመሪያው ፈዝ የውሃ ማመንጨት መጀመሩ ታውቋል።
የውሃ ፕሮጄክቱ ሙሉ በሙሉ ሲጠናቀቅ 39 ቀበሌያት ያሉትን የቦርቻን ወረዳ ጨምሮ በኣባያ ሎካ ወረዳ ውስጥ ባሉ ቀበሌያት ያለው የውሃ ችግር ይቀርፋል ተብሎ ይጠበቃል።
በቦርቻ ወረዳ የከርሰምድር ውሃ እጥረት መኖሩ ውሃን ከኣዋዳ ለማምጣት እንዳስገደደ የሚነገር ቢሆንም፤ በወረዳው ውስጥ ውሃ ኣለ ተብሎ በጥናት በተረጋገጠባቸው ኣካባቢዎች የውሃ የማውጣት ፕሮጄክቶች እየተካሄዱ መሆናቸውን ለማወቅ ተችሏል።
እንደጥቻ ወራና ዘጋባ በወረዳው እየተካሄዱ ያሉት እነዚህ ወደ ኣምስት የምቆጠሩ የውሃ ፕሮጄክቶች ሲጠናቀቁ የወረዳውን የንጽህ ውሃ ሽፋን ወደ 25 % ያደረሳሉ ተብሎ ይጠበቃል።
የሆነ ሆኖ በወረዳው ውስጥ በመካሄድ ላይ ያሉት እነዚህ የውሃ ፕሮጄክቶች ከመጠን በላይ የዘገዩ እና የተለያዩ ችግሮች ያሉባቸው መሆናቸው ታውቋል። ለኣብነትም ያህል፦ የኣዋዳ ቦርቻ የንጽህ ውሃ ፕሮጄክት ከምገባው በላይ ከመኗተቱ በላይ የሙሲና ችግር ኣለበት ተብሎ ይጠረጠራል።
በኣጠቃላይ በቦርቻ ወረዳ ያለውን የንጽህ ውሃ ችግር ለመቅረፍ መንግስት ሆነ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ያደረጉት ወይም እያደረጉ ያሉት የስራ እንቅስቃሴ በውጤት ያልታጀበ እና የህዝቡን የውሃ ጥያቄ ለመመለስ ያልቻለ መሆኑን ሪፖርተራችን ጥቻ ወራና ከቦርቻ ዘግቧል።



Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር