የኢትዮጵያ ሴቶች እግር ኳስ ፕሪሚየር ሊግ የፍፃሜ ጨዋታ ነገ በሀዋሳ ከተማ ይጀመራል

የሲዳማ ቡና የሴቶች ብድን
ከሰኔ 8 እስከ ሰኔ 22 ቀን 2006 ዓ.ም በሚካሄደው በዚህ ጨዋታ ተወዳዳሪ ክለቦች፣ የውድድር ባለሙያዎች ደጋፊዎችና ሌሎች እንግዶች ይገኛሉ ተብሎ ይጠበቃል።
የኢትዮጵያ ዜና ኣገልግሎት እንደዘጋበው፤ ለፍጻሜ ውድድር በወጣው ደንብ መሰረት ሀዋሳ ከነማና ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የየምደቡ አሸናፊ በመሆናቸው የምድብ አንድና ሁለት አባትነት ደረጃ ሲያገኙ የቀሩት ክለቦች ግን በደረጃቸው መሰረት ድልድል ይደረግላቸዋል።
ከ2ኛ እስከ 4ኛ ደረጃ ባለው የምድብ ተራ ቁጥር ያሉት ደግሞ በዕጣ የሚወሰኑ ይሆናል።
ከየምደቡ አንደኛና ሁለተኛ የሚወጡት ቡድኖች ለጥሎ ማለፍ ውደድር የሚያልፉ ሲሆን ተሸናፊዎች ለሶስተኛ ደረጃ፣ አሸናፊዎች ደግሞ ለዋንጫ ፍልሚያ የሚያደርጉ ይሆናል።
ቀደም ሲል ባስመዘገቡት ውጤት መሰረት ከማዕከላዊ ሰሜን ዞን ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፣ ደደቢት፣ ቅዱስ ጊዮርጊስና ዳሽን ቢራ ሲገኙ ከደቡብ ምስራቅ ዞን ደግሞ ሀዋሳ ከነማ፣ ሲዳማ ቡና፣ አርባ ምንጭና ድሬድዋ ከተማ ለፍፃሜ ውድድር ያለፉ ናቸው።
ሀዋሳ ጨዋታውን ለማካሄድ አስፈላጊውን ዝግጅት ማድረጓንና የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽንም ውድድሩ የተሳካና ያማረ እንዲሆን አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት ማደረጉን ገልጿል።
ፈዴሬሽኑ ለሸናፊዎቹ የዋንጫና የሜዳሊያ ሽልማት እንዲሁም ለኮከብ ተጫዋቾች፣ ለአሰልጣኞችና ለዳኞች የማበረታቻ ሽልማት እንደሚያደርግ ማሰታወቁን ኢዜኣ ዘግቧል።

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር