በዚህ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚዬር ሊግ ጫዋታዎች የሲዳማ ክለቦች ድል ቀንቷቸዋል

ሃዋሳ ከነማ ደደቢትን 2 ለ 1 ፤ ሲዳማ ቡና ሐረር ሲቲ 3 ለ2
ዜናው የፋና ነው፦
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 29፣ 2006 (ኤፍ.ቢ.ሲ.) 23ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሜየር ሊግ መርሀግብሮች ትላንት ቀጥለው ሲካሄዱ ሙገርና ዳሽን ድል ቀንቷቸዋል።
በመውረድ ስጋት ውስጥ የሚገኙት ሙገርና ዳሽን ቢራ በአዲስ አበባ ስታዲዮም ተጋጣሚያቸውን በማሸነፍ ወሳኝ ድል አግኝተዋል፡፡
ትናንት ምሽት 11፡30 ላይ ኢትዮጵያ ቡናን ያስተናገደው ሙገር 1 ለ 0 በመርታት ነው ወሳኝ ሙሉ ሶስት ነጥብ ያገኘው፡፡
በመውረድ ስጋት ላይ የሚገኙት ዳሽን ቢራ እና መብራት ሀይል በአዲስ አበባ ስታዲዮም 9፡30 ላይ በተገናኙበት ጨዋታ ዳሽን 2 ለ 0 በመርታት የበላይነቱን ወስዷል፡፡
ዳሽን ቢራ እና ሙገር ሲሚንቶ ማሸነፋቸውን ተከትሎ በ23 ጨዋታዎች እኩል 27 ነጥብ በመሰብሰብ ደረጃቸውን ከፍ ማድረግ ችለዋል፡፡
የበለጠ በመውረድ ስጋት ውስጥ የሚገኘው ሐረር ከተማ በሲዳማ ቡና ሽንፈት በማስተናገዱ፥ በዳሽን ቢራ የተሸነፈው መብራት ሀይል የተለየ ስጋት የሚኖርበት አይሆንም፡፡
በክልል ከተሞች በተደረጉ ጨዋታዎች ሀረር ከተማ ወደ ይርጋለም ተጉዞ ከሲዳማ ቡና ጋር ያደረገውን ጨዋታ 3 ለ 2 በመረታቱ መድህንን ተከትሎ ወደ ብሔራዊ ሊግ ለመውረድ የተቃረበበትን ውጤት አስመዝግቧል፡፡
ሀረር ከተማ በ23 ጨዋታዎች 16 ነጥብ ብቻ ነው ማግኘት የቻለው፡፡
በሌላ ጨዋታ ኢትዮጵያ መድህን ቦዲቲ ላይ በወላይታ ድቻ የ3 ለ 0 ሽንፈት በማስተናገዱ በ23 ጨዋታ 10 ነጥብ ብቻ በመሰብሰብ  መውረዱን አረጋግጧል።
ይህን ተከትሎም መድህን ብሔራዊ ሊግን የተቀላቀለ የመጀመሪያው ወራጅ ቡድን ሆኗል፡፡
የሊጉ ሻምፒዮን ቅዱስ ጊዮርጊስ በአበበ ቢቄላ ስታዲዮም አርባ ምንጭን 2 ለ 0 በመርታት ነጥቡን ከፍ አድርጓል፡፡
በተመሳሳይ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ መከላከያን አስተናግዶ 1 ለ 0 በመርታት ሊጉን ሶስተኛ ሆኖ ሊያጠናቅቅ የሚችልበትን ውጤት አስመዝግቧል፡፡
ሀዋሳ ከነማም በሜዳው ደደቢትን 2 ለ 1 በመርታት ሙሉ ሶስት ነጥብ ወስዷል፡፡

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር