የባህል ስፖርቶች ውድድር ነገ በሃዋሳ ይጀመራል፤ መልካም እድል ለሲዴ ተወዳዳሪዎች!

ፎቶ ከ https://www.google.com.pe/url?sa=i&rct=j&q=&esrc=s&source=images&cd=&cad=rja&uact=8&docid=BrtdZFEjwpXJaM&tbnid=T_rvmxNsoecT6M:&ved=0CAQQjB0&url=http%3A%2F%2Fwww.skyscrapercity.com%2Fshowthread.php%3Ft%3D849248%26page%3D4&ei=CGh3U-fqB-irsQTVpICIAg&bvm=bv.66917471,d.aWw&psig=AFQjCNGDgRaNwr-ojorHu46ItlwzfrDbIw&ust=1400420733937651

አዲስ አበባ ግንቦት 9/2006 12ኛው የመላው ኢትዮጵያ የባህል ስፖርቶች ውድድርና ፌስቲቫል ነገ በሃዋሳ ይጀመራል።
የኢትዮጵያ የባህል ስፖርት ፌዴሬሽን እንዳስታወቀው ውድድሩ ከነገ ግንቦት 10 ቀን ጀምሮ እስከ ግንቦት 20 ቀን 2006 ዓም ድረስ ይካሄዳል።
የፌዴሬሽኑ ፕሬዝዳንት አቶ ከበደ ደስታ እንደተናገሩት በውድድሩ አዲስ አበባና ድሬዳዋን ጨምሮ ሁሉም ክልሎች በዘጠኝ የውድድር አይነቶች ይሳተፋሉ።
የባህል ስፖርት ውድድሩ አርሶና አርብቶ አደሩን ጨምሮ በርካታ የህብረተሰብ ከፍል የሚሳተፍበት ይሆናል።
ዝግጅቱ በተሳካ ሁኔታ ተጀምሮ እንዲፈጸም ፌዴሬሽኑ አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት ማድረጉን ፕሬዝዳንቱ ገልጸዋል።
ለ10 ቀናት በሚቆየው በዚህ ውድድርና ፌስቲቫል ላይ ከአንድ ሺህ በላይ ስፖርተኞች ይሳተፋሉ።
በየክልሎቹ የሚገኙ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች የባህል፣ የቋንቋና የታሪክ ልውውጥ እንደሚያደርጉም ይጠበቃል።
የደቡብ ክልል ስፖርት ኮሚሽነር አቶ መዘረዲን ሁሴን በበኩላቸው በሀዋሳ በሚካሄደው የባህል ስፖርቶች ውድድር ላይ ክልሉ ከተሳታፊነት በተጨማሪ ባለፉት ዓመታት ከተከናወኑ ውድድሮች በተሻለ ስኬታማ ለመሆን እየሰራ ነው ብለዋል።
ስፖርታዊ ውድድሩን በተሳካ ሁኔታና ያለምን የጸጥታ ችግር ለማጠናቀቅም ከፖሊስና ከሌሎችም ባለድርሻ አካላት የተውጣጣ ኮሚቴ በማዋቀር ቅድመ ዝግጅት መጠናቀቁን አስታውቀዋል።
በፌዴራል ስፖርት ኮሚሽን የስፖርት ተሳትፎና የውድድር ፌስቲቫል ዳይሬክተር አቶ ተስፋዬ በቀለ እንደገለጹት በውድድሩ የባህልና የቋንቋ ልውውጥ ከመካሄዱ በተጨማሪ በባህል ስፖርት ተተኪ ስፖርተኞችን ለማፍራትም ያስችላል።
ከዘጠኙ ባህላዊ የመወዳደሪያ የስፖርት አይነቶች መካከል የገና ጨዋታ፣ ትግል፣ ኩርቦ፣ ገበጣ፣ ፈረስ ጉግስና ፈረስ ሸርጥ ይገኙበታል።
ወንዶች በዘጠኙም የውድድር ዓይነቶች፣ ሴቶች ደግሞ ከገና ጨዋታ ውጭ በስምንቱ ተካፋይ ይሆናሉ።
12ኛው የመላው ኢትዮጵያ የባህል ስፖርቶች ውድድርና ፌስቲቫል በቆይታው ከስፖርታዊ ጨዋታዎች ባሻገር የፎቶ አውደርዕይ እና የባህል ምሽትንም ያካትታል።

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር