በአዲስ አበባ ሊካሄድ የነበረው የምስራቅ አፍሪካ የታዳጊዎች አትሌቲክስ ሻምፒዮና ተሰረዘ


አዲስ አበባ ግንቦት 08/2006 በመጪው ቅዳሜና እሁድ በአዲስ አበባ ሊካሄድ የነበረው የምስራቅ አፍሪካ የታዳጊዎች አትሌቲክስ ሻምፒዮና ተሰረዘ።
ውድድሩ መቼ እንደሚካሄድ በቀጣይ እንደሚያሳውቅ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ገልጿል።
ውድድሩ የተሰረዘው ተወዳዳሪዎች በቦትስዋና ጋቦሮኒ ለሚካሄደው የወጣቶች ሻምፒዮና ዝግጅት ለማድረግ ጊዜው እንዲቀየር በመጠየቃቸው ነው።
የፌዴሬሽኑ ፕሬዝዳንት አቶ ዱቤ ጂሎ እንደገለጹት የምግብ እና የመጠለያ ወጪ በአዘጋጅ ሀገር፣ የትራንስፖርት ትኬት ወጪ ደግሞ በራሳቸው ይሸፈናል።
ተሳታፊዎቹም በውድድሮች መደራረብና የበጀት እጥረት አጋጥሞናል የሚል ምክንያት ለኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን አቅርበዋል፡፡ 
አትሌቶቹ ቦትስዋና ለሚካሄደው የወጣቶች ሻምፒዮና ውድድር በመመረጣቸው የሰው ሀይል እጥረት እንዳጋጠማቸውም ገልፀዋል፡፡
ሻምፒዮናው በሩጫ፣ በውርወራና ዝላይ ሁሉንም የምስራቅ አፍሪካ ሀገራት ሲያሳትፍ በተለይም በሩጫው ዘርፍ ኢትዮጵያ እና ኬኒያ ትልቅ ግምት ይሰጣቸዋል፡፡

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር