ሲአን በሀዋሳ ጽ/ቤቱ ግንቦት 16/1994 ዓ/ም በሎቄ የተጨፈጨፉ ንጹሓን የሲዳማ ልጆች 12ኛ ዓመት የመታሰቢያ ቀን በተለያዩ ዝግጅቾች አክብሮ ውለዋል



ምንጭ፦ Selamu Bulado
ሲአን በሀዋሳ ጽ/ቤቱ ግንቦት 16/1994 ዓ/ም በሎቄ የተጨፈጨፉ ንጹሓን የሲዳማ ልጆች 12ኛ ዓመት የመታሰቢያ ቀን በተለያዩ ዝግጅቾች አክብሮ ውለዋል!!!!
በዕለቱ የተከናወኑ ድርጊቶች፦
1ኛ) በተሳታፊዎች የህሊና ፀሎት ተደርጓል፤
2ኛ) የእንኳን ደህና መጣችሁ እና የመክፈቻ ንግግር በዶ/ር አየለ አሊቶ ተደርጓል፤
3ኛ) አጠቃላይ ባሁኑ ጊዜ በኢት/ያ ዘጎች ላይ በገዢው ፓርቲ እየተፈፀሙ ያሉ ኢ-ሰብዓዊና ኢ-ዴሞክራሲያ ድርጊቶች ላይ በዕለቱ እንግዳ አቶ ደጉ ደነቦ (ደቡብ የመድረክ ተወካይ) ገለጻ ተደርጓል፤
4) የግንቦት 16/1994 ዓ/ም የሎቄ ጭፍጨፋ በማስመልከት በአቶ ለገሰ ዋንሳሞ ዋቃዮ በስፋት ገለጻ ተደርጓል፤
5)የሲአን ትግል አመሠራረት እና ታሪካዊ አመጣጥ ላይ የቀድመው የሲአን መስራች ታጋይና ያሁኑ አመራር በአቶ አርጋታ ጉንሳ (አዱርማን) አጭር ገላጻ ተደርጓል፤
6)በወቅቱ ሰዎች ስጨፈጨፍ አካል ጉዳተኛ ሆነው በአሁኑ ጊዜ በህይወት ያሉ አንዳንድ ግለሰቦች በገዢው ፓርቲ ላይ ያላቸውን ጥላቻ ለተሳታፊዎች ገልጸዋል፤
7) በደምሴ ሱካሬ Qaangeemmo'ne በሚል ርዕስ የተዘጋጀ ግጥም ለተሳታፊዎች ቀርበዋል፤
በመጨረሻም የሲዳማ አርነት ንቅናቄ(ሲአን) ግንቦት 16/1994 ዓ/ም ንጹሓን የሲዳማ ልጆችን በሎቄ ያስጨፈጨፉት ግለሰቦች ለፍርድ የሚቀርቡበት ጊዜ ቅርብ እንደሆነ በአቶ ደሳለኝ መሳ ለተሳታፊዎች ተገልጾ የሻማ ማብራት ስነ-ስርዓት ተካሂዶ ፕሮግራሙ ተጠናቋል።

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር