ቅዱስ ጊዮርጊስ ወደ ይርጋለም ተጉዞ ሲዳማ ቡናን 1 ለ0 በማሸነፍ ነው የዋንጫ ባለቤት መሆኑን አስቀድሞ ኣረጋገጠ

ሀዋሳ ከተማ በሜዳው ኢትዮጵያ መድህንን አስተናግዶ 1 አቻ ሲለያይ ፥ በሊጉ ግርጌ የሚገኘው ኢትዮጵያ መድህን በበኩሉ ሶስት ነጥብ ከሀዋሳ ባለማግኘቱ በሊጉ ለመቆየት የመቆየቱ ነገር አጣብቂኝ ውስጥ እንዲገባ አድርጎታል

የዜና ምንጭ፦ www.fanabc.com
አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 19፣ 2006 (ፍ.ቢ.ሲ) የ21ኛው ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 5 ጨዋታዎች ትናንት በአዲስ አበባና በክልል ከተሞች ተካሂደዋል፡፡
5 ጨዋታዎች በቀሩት ሊጉ ቅዱስ ጊዮርጊስ ከወዲሁ የ2006 የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሻምፒዮን መሆኑን ያረጋገጠበትን ውጤት አስመዝግቧል፡፡
ቅዱስ ጊዮርጊስ ወደ ይርጋለም ተጉዞ ሲዳማ ቡናን 1 ለ0 በማሸነፍ ነው የዋንጫ ባለቤት መሆኑን አስቀድሞ ያረጋገጠው፡፡
ሀዋሳ ከተማ በሜዳው ኢትዮጵያ መድህንን አስተናግዶ 1 አቻ ሲለያይ ፥ በሊጉ ግርጌ የሚገኘው ኢትዮጵያ መድህን በበኩሉ ሶስት ነጥብ ከሀዋሳ ባለማግኘቱ በሊጉ ለመቆየት የመቆየቱ ነገር አጣብቂኝ ውስጥ እንዲገባ አድርጎታል።
ወላይታ ድቻ የወራጅ ስጋት የሚታይበትን ሙገር ሲሚንቶ በሜዳው አስተናግዶ 1ለ0 ማሸነፍ የቻለ ሲሆን ፥ የመውረድ ስጋት ያንዣበበበት ዳሽን ቢራ በበኩሉ ፤ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክን አዲስ አበባ ስታዲዮም ላይ 1 ለ0 በመርታት ሁለተኛ ተከታታይ ወሳኝ ድሉን አስመዝግቧል፡፡
የኢትዮጵያ ቡና እና አርባምንጭ ከነማ በአበበ ቢቄላ ስታዲዮም ከቀኑ 9 ሰዓት ጀምሮ ያደረጉት ጨዋታ ሊጠናቀቅ 20 ደቂቃዎች ሲቀሩት በጣለው ከፍተኛ ዝናብ ምክንያት ተቋርጧል ፡፡
በጨዋታው አርባምንጭ ከነማ ከእረፍት በፊት ባስቆጠራት ግብ አንድ ለዜሮ እየመራ መዝለቅ ችሏል።
በዚህ መሰረትም የሁለቱ ክለቦች ጨዋታ ዛሬ ከጠዋቱ 3፡00 በአበበ ቢቂላ ስታድየም የሚቀጥል ይሆናል፡፡
ሀረር ቢራ ከመብራት ሀይል የሚያደርጉት ጨዋታም በአዲስ አበባ ስቴዲየም 11:30 ላይ የሚደረግ ሌላ መርሃ ግብር ነው።
ሊጉን ቅዱስ ጊዮርጊስ በ21 ጨዋታ 58 ነጥብ በመያዝ ሻምፒዮን ሆኗል፡፡ ኢትዮጵያ ቡና በ20 ጨዋታና በ38 ነጥብ ሁለተኛ ደረጃን ይዞ ይገኛል።

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር