የሲዳማ ተማሪዎችን ህገ መንግስታዊ የመብት ጥያቄ በማንሳታቸው የተነሳ በመንግስት የጸጥታ ኃይሎ ታድነው በመታሰር ላይ ናቸው

ሪፖርተራችን ጥቻ ወራና ከሃዋሣ እንደዘጋበው ሰሞኑን በኣላሙራ እና ታቦር ከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህር ቤቶች ላለፉት ሁለት ኣመታት ውስጥ ለውስጥ ስቀጣጠል የነበረው የሲዳማ ተማሪዎች የመብት ጥያቄ ሰሞኑን ተባብሶ ተማሪዎች ከጸጥታ ኃይሎች ጋር እስከመጋጨት ደርሷል።
የኣገሪቱ ህገ መንግስት ብሄር፤ ብሄረሰቦች እና ህዝቦች በራሳቸው ቋንቋ መማር መብት የደነገገ ሲሆን፤ በዚሁ መሰረት በመላው የኣገሪቱ ክልሎች ውስጥ የምገኙ በኣከባቢው ቋንቋ በማስተማሪ ላይ ይገኛሉ። እስከ ኣሁን ባለው ልምድ መሰረት በየትኛውም የኣገሪቱ ክፍል ያለ ብሄር ልዩነት ተማሪዎች በኣከባቢው ቋንቋ በመማር ላይ ሲሆኑ በሃዋሳ ከተማ ግን እውነታው የቅል ነው።
ሰሞኑን የኣላሙራ እና ታቦር ትምህር ቤቶች የሲዳማ ተማሪዎች ካነሷቸው ጥያቄዎች መካከል፦
  • በየትምህርት ቤቶቹ በሲዳምኛ ቋንቋ የምሰጠው ትምህርት ሁሉንም ተማሪዎች ያሳተፈ ይሁን!
  • የሲዳምኛ ቋንቋ እንደማስተማሪያ ቋንቋነቱ ትኩረት ይሰጠው!
  • በትምህርት ቤቶች የሲዳምኛ ቋንቋ የመግባቢያ ቋንቋ ይሁን! የምሉ ሲሆኑ ከዚህም ባሻገር፦
  • በሲዳማ ውስጥ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሰ የመጣው የሰብኣዊ መብት ረገጣ ይቁም!
  • የክልል ኣስተዳደር መብት ጥያቄ ምላሽ ይሰጠው! የምሉት ይገኙበታል።
    በጉዳዩ ላይ የሃዋሳ ከተማ ኣስተዳደር ከንቲባ ካላ ዮናስ ዮሰፍ ተማሪዎቹን ያነጋገሩ ቢሆንም፤ ተማሪዎቹ ጥያቄዎች ከንቲባው ኣጥጋብ ምላሽ ሳይሰጡ ቀርተዋል ተብሏል።
    ለጥያቄዎቻቸው ኣጥጋብ ምላሽ ያጡት ተማሪዎች ህገ መንግስታዊ መብቶቻቸውን የማስከበር ተግባራትን የወሰዱ ሲሆን፤ የትምህርት ቤቶቻቸውን ስያሜ በሲዳምኛ ቋንቋ ጽፈዋል።
    ተማሪዎቹ የየትምህርት ቤቶቻቸውን ስያሜ በሲዳምኛ ቋንቋ በምጽፉበት ወቅት በትምህርት ቤቶቹ ኣስተዳደር እና በተማሪዎቹ መካከል የተፈጠረውን ኣለመግባባት ለመቆጣጠር የመንግስት ጸጥታ ኃይሎች ጠልቃ መግባታቸው ታውቋል።በጉዳዩ ጠልቃ የገቡት የከተማዋ ፖሊሲ እና የክልሉ ልዩ ኃይል ኣስለቃሽ ጭስ በተማሪዎቹ ላይ ከመርጨታቸው በላይ ኃይልን በመጠቀም ባካሄዱት ድብደባ በርካታ ተማሪዎችን ለኣካል ጉዳት መዳረጋቸው ተገልጿል።
እንደዘገባው ከሆነ 25 የምበልጡ ተማሪዎች በጸጥታ ኃይሎቹ በደረሰባቸው ጉዳት የተነሳ ሆስፒታሎች ተኝተው በመታከም ላይ ሲሆኑ፤ 220 የሚሆኑት በእስር ላይ ይገኛሉ።

ከዚህም ባሻገር በርካታ የኣላሙራ እና የታቦር ከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች በፖሊሶች በመታደን ላይ ናቸው።

ይህንን ዘገባ እስካጠናከርንበት ሰዓት ድረስ የሃዋሳ ከተማ ጭምብል ባጠለቁ ወታደሮች በመጠበቅ ላይ ሲሆን፤ ተማሪዎችን ወደ ትምህርት ገበታቸው እንዳልተመለሱ ታውቋል።



Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር