ኣድማጭ ያጣ የሲዳማ ህዝብ የመልካም ኣስተዳደር እጦት እሮሮ

ተጻፈ በሀገሬሰላም ሆሮረሳ 
ምንጭ፦ የሲዳማ ኣርነት ግንባር( ሲነግ) ድህረ_ገጽ ፤ http://sidamaliberation-front.org/ 

የዓለም ህዘብ በስሱና የኢትዮጵያ ህዝብ በጥልቀት እንደሚያውቀው የሲዳማ ህዝብ በደል፣ህገመንግሥታዊ መብት መጣስና ድፍጠጣ፣ የሰብዓዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶች መካድና የሲዳማ ህዝብ ሀብት መበዝበዝ ረዥም ዘመናትን ያስቆጠረ መሆኑን በቅን ልቦና ለሚመለከት ለማንኛውም ሰው ግልጽ ነው፡፡የሲዳማ ህዝብም በሚፈጸምበት ግፍ መማረሩንና ሥራዓቱን ሊታገሠው አለመቻሉን ግልጽ በመድረግ ለነጻነቱ እየታገለ ይገኛል፡፡ 

ወቅቱን እየጠበቁ በሚፈራረቁ ካድሮች የሚሰቃየው የሲዳማ ህዝብ አሁን ደግሞ ኑሮ ውድነቱና ብልሹ አስተዳደር የህዝቡን አንድነት 
እያናጉ ይገኛሉ፡፡ 
 የኢህአዴግ ተላላኪዎች በሚያቀርቡት ‘በሬ ወለደ ፕሮፓጋንዳ’ የሲዳማ ህዝብ የመለያየት እርኩስ መንፈስ የተጠናወተውን ነገር ግን 
የማይበቅለውን ዘር እየዘሩም ይገኛሉ፡፡ እንደዚህ እንዲል ያነሳሳኝ ካለፈው ሁለት ዓመታት ጀምሮ ይበልጥ እየተጠናከረ የመጣውን 
የሲዳማ ህዝብ ትግል ያስፈራው ኢህአዴግ/ሕወኻት መንግስት በአቶ አድሱ ለገሰ በኩል የሲዳማ ክልል ለመጎብኘት ብቅ ብሎ ከክልሉ የተለያዩ ዞኖችንና ወረዳዎንች በመሄድ የነበረውን(ያለውን) የፖለትካ ውጥረት ለመቃኘትም ጭምር አብዛኞቻችን እናውቃለን፡፡ በዚህ ጉዞው የተለያዩ የሲዳማ ህብረተሰብ ክፍል ያነጋገሩ ሲሆን የጋጠማቸውም የሥርዓቱ ባዶነትን ቁልጭ አድርጎ እንዳሳየው ህደቱን በቅርበት ስከታተል ከነበረው ምንጫችን ለማወቅ ተችለዋል፡፡ 

ነገር ግን የተሰማውን የሲዳማ ህዝብ ዘርፈ ብዙ ችግሮች(multidimensional problems) ወደ ጎን ትተው ‘’የሲዳማ ህዝብ በራሱ 
ብሔርና ብሔረሰብ ስብስብ’’ ነው በማለት የኢህአዴግን የመሰነጣጠቅ አጀንዳውን ሹክ ያለው አፍትልኮ ወተው ነበር፡፡ ዳቦ ተጠይቆ ድንጋይ(ጥይት) ማቀበል የለመዱ የኢህአዴግ/ሕወኻት ተላላከ ካድሮች የሲዳማን ብሎም የሀገሪቱን ብሔሮች፣ብሔረሰቦችና ህዝቦች 
የማከፋፈል አጀንዳቸው የሚተገብሩበት ጊዜ የመጣ ይመስላል፡፡ ምክንያቱም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የሲዳማ ህዝብ እየተራመሰ ስለምገኝ 
ነው፡፡ የሲዳማ ህዘብ በጎሳ፣በቤተሰብ፣በታናሽና ታላቅ፣ በባልና ምስት እየተከፋፈሉ ይገኛሉ፡፡ 

ተጨማሪ ለማንበብ ይህንን ሊንክ ይጫኑ ኣድማጭ ያጣ

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር