ሲዳማ ባለፈው ሳምንት፦ ኬጂ ቻን በቦርቻ

ፎቶ ሮፖርተር ጋዜጣ
ታዋቂው የሆሊውድ አክተር ኬጂ ቻን ለሦስት ቀናት በኢትዮጵያ ውስጥ ጉብኝት አድርጓል፡፡ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የምግብና እርሻ ልማት ድርጅት (ፋኦ) ጋባዥነት ወደ ኢትዮጵያ የመጣው ተዋናዩ ፋኦ በደቡብ ክልል ያሉትን ፕሮጀክቶች ተዘዋውሮ ጐብኝቷል፡፡ 
ከጉብኝቱ መልስ ዓርብ መጋቢት 12 ቀን 2006 ዓ.ም. ጋዜጣዊ መግለጫ የሰጠው ቻን እንደገለጸው፣ ጉብኝቱ የግብርና ባለሙያዎችን፣ ሴቶችን፣ ሕፃናትን፣ ሠራተኞችንና ተማሪዎችን ለመመልከትና ከሚኒስትሮች ጋር ለመወያየት ዕድል ሰጥቶታል፡፡ ከጉብኝቱ በፊት ስለ ኢትዮጵያ የነበረው ዕውቀት በእውን ካለው የተለየ እንደነበር የገለጸው ቻን፣ የአጭር ጊዜ ዕርዳታ ከመስጠት በዘለለ ዘለቄታ ያለው ዕርዳታ ማቅረብ እንደሚገባው የተማረበት እንደሆነ ተናግሯል፡፡ 
ጄኪ ቻን በተለያዩ የዕርዳታ ሰጪ ቡድኖች የሚንቀሳቀስ ሲሆን ይህን ለየት የሚያደርገው ከ60ኛ ዓመት ክብረ በዓሉ ጋር በተያያዘ በተለይም ረሀብን ለማጥፋትና ሰላምን በዓለም ለማስፈን ጥሪ የሚያቀርብበት መሆኑ ነው፡፡
ለቻን 60ኛ ዓመት ልደት ከሃምሳ በላይ አገሮች የተወጣጡ ሙዚቀኞች ይሳተፉበታል የተባለ የሙዚቃ ኮንሰርት በቤጂንግ የሚካሄድ ሲሆን ‹‹ፒስ ኤንድ ላቭ›› (ሰላምና ፍቅር) በሚል የዕርዳታ ማሰባሰቢያም ይሆናል፡፡
በዕለቱ ተዋናዩ የሰው ልጅ እርስ በርስ በፍቅርና በሰላም ይኖር ዘንድ ጥሪውን ያቀረበ ሲሆን ‹‹ተፈጥሮአዊ አደጋ በሞላበት የሰው ልጅ ሰቆቃ በተንሰራፋበት ዓለም ሰው ሠራሽ ችግር በላይ በላዩ አይጨመር፤ ሁላችንም በሰላም እንኑር፤›› የሚል መልዕክቱን አድርሷል፡፡ 
ሐዋሳ ላይ በኃይሌ ሪዞርት ልደቱን አስመልክቶ የተጋበዘው ቻን በጉብኝቱ ወቅት በተለይ በኢትዮጵያ ባህላዊ እስክስታ በመደመም፣ የኢትዮጵያ ባህላዊ እስክስታ በዓለም መተዋወቅ ያለበት መሆኑን ሳይናገር አላለፈም፡፡ 

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር