በሃዋሳ ከተማ ሀሰተኛ የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ማስረጃ ኣቅራቢዎች ቁጥር ለምን ጨመረ?

Photo@http://elmartyhawassa.blogspot.com/2012/06/home.html
በሃዋሳ ከተማ እና በሌሎች የደቡብ ኣከባቢዎች የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ማስረጃ ኣጭበርባሪዎች መበራከታቸው ተሰማ፤ ሲዳማን ጨምሮ በደቡብ ክልል በግማሽ ኣመት ውስጥ የሙያ ማረጋገጫ ፈተና ከወሰዱት19 862 ሙያተኞች መካከል ግማሾቹ ወድቀዋል።

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በተለይ ከቴክኒክ እና ሙያ ተቋማት ስልጥነው የምወጡ ሙያቸኞች የሙያ ማረጋገጫ ፈተና እንድወስዱ መገደዳቸውን ተከትሎ የሙያ ማረጋገጫውን ፈተና ውጤት የሚያጭበረብሩ ሙያተኞች ቁጥር መበራከቱ እየተነገረ ነው።

የወራንቻ ኢንፎርሜሽን ኔትዎርክ ሰሞኑን ከሃዋሳ እንደዘጋበው፤ ሲዳማን ጨምሮ በደቡብ ክልል ባለፉት ስድስት ወራት 19 862 ሙያተኞች የብቃት ማረጋገጫ ፈተና የወሰዱ ሲሆኑ ፈተናውን ያለፉት ግማሾቹ ብቻ ናቸው ።

የወኢኔት ሪፖርተሮች ያናገሯቸው እና ስማቸው እንድጠቀስ ያልፈለጉ በደቡብ ክልል የሙያ ብቃት ምዘናና ማረጋገጫ ማዕከል የምሰጠውን ፈተና የወሰዱ ተፈታኞች እንደተናገሩ፤ በማዕከሉ የምሰጠው የሙያ ብቃት ምዘና ከባድ መሆኑን በየተቋማቱ ያለውን የሙያ ትምህርት ጥራት ከግምት ውስጥ ያላስገባ ነው።

እንደኣስተያየት ስጪዎቱ ከሆነ፤ መንግስት በምዘና ፈተና ላይ ብቻ ትኩረት ከመሰጠት ወደየሙያ ተቋማቱ የምገቡ ሰልጣኞች በኣግባቡ የምገባውን ትምህርት እና የሙያ ክሎት እንድይዙ የሚያደርግ የትምህርት ስርዓት መዘርጋት ኣለበት ብለዋል።

ኣክለውም በየየሙያ ተቋማቱ ያለው የትምህርት ስርዓት ጥራት የሌለው መሆኑን ገልጸው፤ የሙያ ማረጋገጫ ከምወስዱት ከግማሽ በላይ የምሆኑት ምዘናውን ማለፈ ኣለመቻል ለትምህርቱ ጥራት ማነስ ማሳያ ነው ብለዋል ።

እንደ ሪፖርተሮቻችን ዘገባ ከሆነ፤የሙያ ምዘናው ፈተናው ከባድ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ በርካታ ተፈታኞች ሀሰተኛ የሙያ ማረጋገጫ ማስረጃዎችን እንድያቀርቡ ተገደዋል። 

በክልሉ ባለፉት ስድስት ወራት ብቻ ከተለያዩ ሴክተሮች ትክክለኛ የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ማስረጃ መሆኑ ይጣራልኝ ተብሎ ከቀረቡ 1 ሺህ 770 ማስረጃዎች መካከል 312 ማስረጃዎች ተመሳስሎ የተሰሩ ሀሰተኛ የሙያ ብቃት ማስረጃ መሆኑንሰሞኑን የመንግስት መገናኛ ብዘሃን ዘግበዋል።

በተለይ በሃዋሳ ከተማ በህገ-ወጥ መንገድ የሙያ ብቃት ማረጋገጫ የሚሰጡ ተቋማት መበራከታቸው የተገጸ ሲሆን፤ ማዕከሉ ከክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ጋር በመቀናጀት በሃዋሳ ከተማ ባደረገው አሰሳ ሀሰተኛ የሙያ ብቃት ማስረጃ ይዘው የተገኙ  ዘጠኝ  ግለሰቦች መያዙንና በሌሎች ከተሞችም ስራው ተጠናክሮ መቀጠሉን ተል፡፡


Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር