የሕፃናት ሽያጭና ወሲብ ቀስቃሽ ፊልሞችን ለመከላከል የወጣው ኮንቬንሽን ፀደቀ

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሕፃናት ሽያጭን፣ የሕፃናት የወሲብ ንግድና የሕፃናትን የወሲብ ቀስቃሽ ፊልሞችን ለመከላከል የወጣው ኮንቬንሽንን ማክሰኞ ዕለት አፀደቀ፡፡ 
የሕፃናት ሽያጭን፣ የሕፃናት የወሲብ ንግድና ወሲብ ቀስቃሽ ፊልሞች በማሳተፍ የሚፈጸሙ ወንጀሎች በዓለም አቀፍም ሆነ አገር አቀፍ ደረጃ አሳሳቢ እየሆኑ በመምጣታቸው፣ ኮንቬንሽኑን በማፅደቅ የሕፃናትና መብት ማስከበር ተገቢ ነው ተብሏል፡፡ አዋጁ እንዲፀድቅ የፓርላማው የሴቶች፣ የሕፃናትና የወጣቶች ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ያቀረበውን የውሳኔ ሐሳብ ፓርላማው ተቀብሎታል፡፡
የተጠቀሰውን ወንጀል ለመከላከልና የሕፃናትን መብት ለማስከበር ኢትዮጵያ ብቻዋን መንቀሳቀሷ ውጤታማ እንደማያደርጋት፣ ነገር ግን ኮንቬንሽኑን በማፅደቅ ከሌሎች አገሮች ጋር ተባብሮ በአጋርነት ወንጀሉን መከላከል እንደሚያስችላት ተገልጿል፡፡
በተመሳሳይም ሕፃናትን በጦርነት ማሳተፍን በሚመለከት የወጣውን የሕፃናት መብቶች ኮንቬንሽን ተጨማሪ ፕሮቶኮል ፓርላማው በማክሰኞ ውሎው አፅድቆታል፡፡ 
ም ንጭ፦ http://www.ethiopianreporter.com

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር