ጃፓን ለኢትዮጵያ የልማት ስራዎች ጠንካራ ድጋፍ ከሚያደርጉ አገራት መካከል በ3ኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች-አምባሳደር ማርቆስ ተክሌ

አዲስ አበባ ጥር 9/2006 ኢትዮጵያ ለምታከናውናቸው የተለያዩ የልማት ስራዎች ጠንካራ ድጋፍ ከሚያደርጉ አገራት መካከል ጃፓን በ3ኛ ደረጃ ላይ እንድምትገኝ በጃፓን የኢትዮጵያ ልዩ መልእክተኛና ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር አስታወቁ።
የሁለቱ አገራት አመታዊ የኢኮኖሚና የንግድ ግንኙነት 153 ሚሊዮን ዶላር ደርሷል።
አምባሳደር ማርቆስ ተክሌ ከኢዜአ ጋር ባደረጉት ቃል ምልልስ እንዳሉት ጃፓን በኢትዮጵያ በሚካሄዱ የልማት ስራዎች ውስጥ ከፍተኛ ድጋፍ በማድረግ ረገድ ከአሜሪካና ቻይና በቀጠል በሶስተኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች።
የኢትዮ-ጃፓን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ከተጀመረ 80 አመታት ማስቆጠሩን የጠቆሙት አምባሳደሩ ግንኙነቱ በጋራ ጥቅሞች ላይ የተመሰረተና በጽኑ መሰረት ላይ እየተገነባ መምጣቱን ጠቁመዋል።
የአገሮቹ ግንኙነት በማህበራዊ መስኮች በተለይም በባህልና በህዝብ ለህዝብና ትብብሮች ረገድም በመልካም ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ አምባሳደሩ ተናግረዋል።
አምባሳደር ማርቆስ በአሁኑ ወቅት በሁለቱ አገራት መካከል ያለው አመታዊ የኢኮኖሚና የንግድ ግንኙነት 153 ሚሊዮን ዶላር መድረሱን ጠቁመዋል።
የጃፓን ባለሃብቶች  በኢትዮጵያ መዋእለ ንዋያቸውን በማፍሰስ ረገድ ከሌሎች አገራት አንጻር ሲታይ በዝቅተኛ ደረጃ ላይ እንደሚገኙ አምባሳደር ማርቆስ ገልጸዋል።
ባለሃብቶቹ በማእድን ልማት፤በንግድ፣በኮንስትራክሽንና በሌሎችም ዘርፎች በሰፊው የመሰማራት ፍላጎት እንዳላቸው ጠቁመዋል።
0፡40
የጃፓን መንግስት በሰው ሃይል ልማት፣በእውቀትና ቴክኖሎጂ ሽግግር ረገድም ለኢትዮጵያ በተግባር የታገዘ ስልጠና ለመስጠት ተጨባጭ እርምጃዎችን እየወሰደ መሆኑን አብራርተዋል።
ለአብነትም በመጪው ሚያዝያ ወር 150 ኢትዮጵውያን  ወደ ጃፓን በመሄድ በተለያዩ የሙያ ዘርፎች ስልጠና እንዲያገኙ የሚያስችል እድል ማመቻቸቱን አንስተዋል።
ከመጀመሪያ ደረጃ እስከ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ድረስ የአዳዲስ ቴክኖሎጂዎችና የፈጠራ ማእከል እንዲሆኑ ከፍተኛ እገዛ እያደረገ መሆኑንም አመልክተዋል።
አምባሳደሩ እንደተናገሩት በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኙ ሴቶች ህይወታቸው እንዲሻሻል ከተያዘው የፈረንጆች አመት ጀምሮ በቶኪዮ የስራ ፈጠራ ክህሎታቸውን ለማሳደግ የሚረዳ ስልጠና ለመሰጠት እቅድ ተይዟል።
http://www.ena.gov.et/index.php?option=com_k2&view=item&id=1008%3A%E1%8C%83%E1_%93%E1%8A%95-%E1%88%88%E1%8A%A2%E1%89%B5%E1%8B%AE%E1%8C%B5%E1%8B%AB-%E1%8B%A8%E1%88_%E1%88%9B%E1%89%B5-%E1%88%B5%E1%88%AB%E1%8B%8E%E1%89%BD-%E1%8C%A0%E1%8A%95%E1%8A%AB%E1%88%AB-%E1%8B%B5%E1%8C%8B%E1__-%E1%8A%A8%E1%88%9A%E1%8B%AB%E1%8B%B0%E1%88_%E1%8C%89-%E1%8A%A0%E1%8C%88%E1%88%AB%E1%89%B5-%E1%88%98%E1%8A%AB%E1%8A%A8%E1%88_-%E1%89%A03%E1%8A%9B-%E1%8B%B0%E1%88%A8%E1%8C%83-%E1%88%8B%E1%8B_-%E1%89%B5%E1%8C%88%E1%8A%9B%E1%88%88%E1%89%BD-%E1%8A%A0%E1%88_%E1%89%A3%E1%88%B3%E1%8B%B0%E1%88_-%E1%88%9B%E1%88_%E1%89%86%E1%88%B5-%E1%89%B0%E1%8A_%E1%88%8C&Itemid=260&lang=am

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር