የአትሌቶቹ ሪዞርት ሆቴል በሐዋሳ ሥራ ጀመረ

የደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች መዲና የሆነችው ሐዋሳ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ የሆቴልና የሪዞልት መዳረሻ እየሆነች ትገኛለች፡፡ በከተማዋ በርካታ ደረጃቸውን የጠበቁ ሆቴሎችና ሪዞልቶች ተገንብተዋል፡፡
በመገንባት ላይ ይገኛሉ፡፡ባለፈው ቅዳሜ፣ ኅዳር 14 ቀን 2006 ዓ.ም. ተመርቆ ሥራውን የጀመረው የገዛኸኝና እልፍነሽ ሆቴልና ሪዞልት፣ ለከተማዋ ተጨማሪ በመሆን የሆቴሎችና ሪዞልቶችን ቁጥር ከመጨመሩም በላይ ለሐዋሳ አዲስ የቱሪስት መዳረሻ ሆኗል፡፡
በሲዲኒ ኦሊምፒክ አሸናፊዎቹ ገዛኸኝ አበራና በባለቤቱ እልፍነሽ ዓለሙ ባለቤትነት የተገነባው ይህ ሆቴልና ሪዞልት 25 ሺሕ ካሬ ሜትር ቦታ የሸፈነ ሲሆን፣ ግንባታው አጠናቅቆ አገልግሎት ላይ ለማዋል ብቻ 150 ሚሊዮን ብር ወጪ ተደርጐበታል፡፡ አጠገቡ በመገንባት ላይ የሚገኘው ባለ አራት ፎቅ ሆቴል ሲጠናቀቅ ደግሞ በአጠቃላይ 200 ሚሊዮን ብር እንደሚፈጅ በምረቃው ሥነ ሥርዓት ወቅት አትሌት ገዛኸኝ አበራ ተናግሯል፡፡
ሥራ የጀመረው የገዛኸኝና እልፍነሽ ሆቴልና ሪዞልት 40 መኝታ ክፍሎች ሲኖሩት፣ ከእነዚህ ውስጥ ራሱን የቻለ ቪላ፣ የራሱ ግቢ፣ ሳሎንና ዕቃ ቤት መመገቢያ ቤቶች አዳራሾችና በግቢው ውስጥ እንግዶች ለምግብነት የሚገለገሉባቸው የተለያዩ የአትክልና ፍራፍሬ እጽዋቶች ተተክለዋል፡፡ በአዘቦትና በበዓላት ቀኖች ኪራያቸው የሚለያይ ሆኖ፣ የአንዱ ቪላ ከፍተኛውና ዝቅተኛው የቀን ኪራይ ዋጋ ሁለት ሺሕ ብር ነው ተብሏል፡፡ ቀሪዎቹ ክፍሎች ጥንድና ነጠላ አልጋ ያላቸው ናቸው፡፡ በአጠቃላይ ዓለም አቀፍ ደረጃቸውን የጠበቁ ሆቴሎችና ሪዞልቶች ሊኖሯቸው የሚገቡትን ሁሉ አሟልቶ የያዘ መሆኑ ባለኰከብ ሆቴል መገንባቱ ተነግሯል፡፡
የምረቃ ሥነ ሥርዓቱ ላይ የውኃ፣ መስኖና ኢነርጅ ሚኒስትር አቶ አለማየሁ ተገኑ፣ የደቡብ ብሔር ብሔሰብና ሕዝቦች ምክትል ርዕሰ መስተዳደር አቶ መለስ ዓለሙና የሐዋሳ ከተማ ከንቲባ አቶ ዮናስ የሱፍ ተገኝተዋል፡፡ 

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር